Thursday, February 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኮሌራ የሚከሰተውን ሞት 90 በመቶ ለመቀነስ ያለመው ዕቅድ በ118 ወረዳዎች ሊተገበር ነው

በኮሌራ የሚከሰተውን ሞት 90 በመቶ ለመቀነስ ያለመው ዕቅድ በ118 ወረዳዎች ሊተገበር ነው

ቀን:

በኮሌራ ምክንያት የሚከሰተውን የሞት ምጣኔ 90 በመቶ ለመቀነስ የታለመው  ብሔራዊ የኮሌራ በሽታን የማስወገድ ዕቅድ፣ ኮሌራ በተደጋጋሚ በሚከሰትባቸው 118 ወረዳዎች እንደሚተገበር ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

 ከ15.9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው ዕቅድ፣ በኮሌራ ምክንያት የሚከሰተውን የሞት ምጣኔ እ.ኤ.አ. በ2028 ቢያንስ በ90 በመቶ ለመቀነስ እንደሚረዳም የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ወረርሽኞችንና የድንገተኛ የኅብረተሰብ የጤና ችግሮችን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ የማኅበረሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽና ቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከር በሁለተኛው የጤና ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ እንደ አንድ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሠራበት ይገኛልም ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ በተደጋጋሚ ሲከሰት መቆየቱንና የወረርሽኙን ምላሽ አሰጣጥ ለማጠናከርና የጉዳት መጠኑን ለመቀነስ ከክልሎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የኮሌራ ክትባትን ለበርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች መሰጠቱን ሊያ (ዶ/ር) አስታውሰዋል፡፡

ወረርሽኙን ለመግታት ሰፊ፣ ዘላቂና ቅንጅታዊ ሥራ እንደሚጠበቅ በመግለጽም፣ ማኅበረሰቡና ባለድርሻ አካላት ዕቅዱ ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አስፋው ዲንጋሞ በበኩላቸው፣ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቀነስ ሚኒስቴራቸው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን በተለይ በንፁህ ውኃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዙሪያ የተለያዩ ሥራዎችን እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

ከ15.9 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተጠቃሚን ደርጋል የተባለው ዕቅድ ከያዛቸው ነጥቦች ውስጥ የኮሌራ መከላከያ ክትባትን በስፋት መስጠት፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትን፣ የአካባቢና የግል ንፅህና አጠባበቅን ማሻሻል ይገኙበታል፡፡ ወረርሽኙ በሚከሰት ጊዜ አፋጣኝ የሕክምና አገልግሎት መስጠትና ተጋላጭ ወረዳዎችን ከወረርሽኙ ለመታደግ ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይሉ (ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ ኮሌራ ‹ቫይብሮ ኮሌራ› በተባለ ተህዋስ አማካይነት የሚከሰትና አንጀትን የሚያጠቃ በሽታ ነው። በተበከለ ምግብና ውኃ አማካይነት የሚመጣው ተህዋሱ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) ምልክቶቹ ናቸው። ኮሌራ በሰውነት ውስጥ ያለውን ፈሳሽ ስለሚያሟጥና አቅም ስለሚያሳጣ ፈጥነው ካልታከሙት በሰዓታት ውስጥ ለሞት ሊዳርግ ይችላል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጥቁር የመልበስ ውዝግብና የእምነት ነፃነት በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኅዳር ወር ላይ በፓርላማ...

የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጠጠር ገለልተኛ ተቋም ለመመሥረት እንቅስቃሴ ተጀመረ

ከ70 በላይ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት ዘርፉን ሊቀላቀሉ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

እስቲ አንገፋፋ!

እነሆ መንገድ። ጊዜና ሥፍራ ተጋግዘው በውስንነት ይዘውናል። መፍጠን ያቃተው...