Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናመንግሥት ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ሕገወጥ እሥራትን እንዲያስቆም ኢሰመጉ ጥሪ አቀረበ

መንግሥት ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ሕገወጥ እሥራትን እንዲያስቆም ኢሰመጉ ጥሪ አቀረበ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኢትዮጵያ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ሕገወጥ እስራት እንዲቆም ለመንግሥት ጥሪ አቀረበ፡፡

ኢሰመጉ ታኅሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ዓርብ አመሻሹ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ አዲስ አባባን ጨምሮ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈጸሙ ያላቸውን የሕግና የመብት ጥሰቶች አስመልከቶ መንግሥት ማስተካከያ እንዲወስድባቸው ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኢሰመጉ በአዲስ አበባ ባሉ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ መሰቀሉንና መዝሙር መዘመሩን ተከትሎ ስለደረሱ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ማብራሪያ እንዲሰጠው፣ ለአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ለሚመለከታቸው ትምህርት ቤቶች በደብዳቤ መጠየቁን አስታውሷል፡፡

- Advertisement -

ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ትምህርት ቤቶች ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት ምላሽ አለመስጠታቸውን ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡

በከተማው በተነሳው ግጭት ምክንያት ሁከት አስነስታችኋል ተብለው የተጠረጠሩ ዘጠኝ ተማሪዎች፣ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ምድብ ችሎት ቀርበው፣ ፍርድ ቤቱም እንዲፈቱ ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም ፖሊስ ውሳኔውን ወዲያውኑ ለመፈጸም ፈቃደኛ አለመሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከፍተኛ አመራር የሆኑት መምህር ዘመነ ጌቴ፣ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳትና ንብረት ማውደም በሚል በቁጥጥር ሥር ውለው በተጠረጠሩበት ወንጀል፣ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ወንጀል ችሎት ቀርበው በአምስት ሺሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ ውሳኔ የተሰጠ ቢሆንም፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ከእስር እንዳልፈታቸው ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ከታኅሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ አምስት የኢዜማ ፓርቲ የምርጫ ክልሉ አባላትና አመራሮች በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዳቸውንና ያሉበት እንደማይታወቅ ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ የተወሰዱትንና ያሉበት የማይታወቀውን አምስት የኢዜማ አባላትን የሚመለከተው አካል፣ የታሰሩበትን ቦታ እንዲያሳውቅና በሕግ አግባብ ጉዳያቸው በግልጽ እንዲታይ እንዲሁም ይህንን እገታ ያደረጉ አካላት ተጠያቂ እዲሆኑ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

የተለያዩ ጉዳዮችን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ በደብዳቤ የሚጠየቁ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አፋጣኝ የሆነ ምላሽ በመስጠት መረጃ የማጋራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

መንግሥት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ወስኖ እያለ ለመፍታት ፈቃደኛ ባለ መሆን፣ ተማሪዎችና ወላጆች እንዲንገላቱ ምክንያት የሆኑ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ እንዲያደርግና ኅብረተሱ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ አመኔታ ይኖረው ዘንድ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ መከበሩንና መፈጸሙን እንዲያረጋግጥ ኢሰመጉ አክሎ ጠይቋል፡፡

በሌላ በኩል በፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስር የፖለቲካ ምኅዳሩን የሚጎዳ በመሆኑ፣ መንግሥት ይህን በማስተካከል ፍትሐዊነት እንዲሰፍን ማድረግ እንደሚገባውና በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ኢዜማን በመወከል የክልሉ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታረቀኝ ደግፌ፣ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን በማክበር የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች በመግለጫው ጠይቋል፡፡

በጋዜጠኞች፣ በፖለቲካ ፓርቲ አባላት እንዲሁም በማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ የሚፈጸም ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስር የፖለቲካ ምኅዳሩን የሚያጠብ፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን የሚገድብ እንዲሁም የፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ድርጊት በመሆኑ፣ መንግሥት ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...