Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሕዝብ ሚዲያዎች ላይ የፓርቲ አባላት ሹመት እንዲቆም ኢዜማ ጠየቀ

በሕዝብ ሚዲያዎች ላይ የፓርቲ አባላት ሹመት እንዲቆም ኢዜማ ጠየቀ

ቀን:

የሕዝብ የሚዲያ ተቋማት እንዲያስተዳድሩ ከሙያው ጋር ምንም ዓይነት ትውውቅ የሌላቸውን የፓርቲ አባላት መሾም እንዲቆም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ጠየቀ፡፡

በሕዝብ ገንዘብ እየተዳደሩ በዘመናት ሒደት እንደስማቸው የሕዝብ መሆን ያልቻሉ ተቋማት፣ ኢሕአዴግ የአመራር ለውጥ አምጥቶና ስሙን ወደ ብልፅግና ቀይሮ ‹‹የለውጥ ሒደት ተጀምሯል›› ከተባለ በኋላ፣ ተስፋዎችን ያሳዩ የነበረ ቢሆንም፣ በዘላቂነት ይህ ነው የሚባል የመፍትሔ ዕርምጃዎች አለመወሰዳቸውን ፓርቲው ታኅሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ይባስ ብሎም ገለልተኛ ሊሆኑ የሚገባቸውን እነዚህን ተቋማት እንዲያስተዳድሩ ከሙያው ጋር ምንም ዓይነት ትውውቅ የሌላቸውን የፓርቲውን አባላት በመሾም፣ ነፃ ሆነው የሕዝብን ጥቅም እንዳያስከብሩ እንዳደረጋቸው በመግለጫው አትቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በየክልሎቹ የተቋቋሙት የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ የፖለቲካ ስሪት የሆነው ቋንቋና ብሔርን መሠረት ያደረገው ፌደራሊዝም ነፀብራቅ በመሆናቸው፣ በአካባቢው ቋንቋ መረጃዎችን የማድረስ መልካም ዕድልን በመጠቀም እውነተኛ መረጃዎችን ከማድረስ ይልቅ የተዛቡ መረጃዎችን ሲያደርሱ እንደሚስተዋሉ አትቷል፡፡

ፓርቲው አካሄድኩት ባለው የዳሰሳ ጥናት፣ የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን አሁንም ድረስ ከገዢው ፓርቲና ከመንግሥት ተፅዕኖ ነፃ አለመውጣታቸውን ተረድቻለሁ ብሏል፡፡

በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሠረት ለመገናኛ ብዙኃን ግዴታዎች በሚያብራራው አንቀጽ መገናኛ ብዙኃን በአገሪቱ ሕገ መንግሥትና የምርጫ ሕግ መሠረት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወይም ድርጅቶችን በፍትሐዊነት የማገልገል ግዴታ አለባቸው የሚል ቢሆንም፣ በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. የተደረገውን የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ አስመልክቶ በአጠቃላይ ኢቢሲ፣ ፋናና ዋልታ ሚዲያዎች 405 መረጃዎችንና የ80 ሰዓታት ዘገባዎችን፣ የቀጥታ ሥርጭቶችንና ቃለ ምልልሶችን ማሰራቸታቸውን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ኢዜማ በሒደቱ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ ለአብዛኞቹ አስተማሪ የሆነ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም. ላይ ያካሄደ ቢሆንም፣ እነዚህ የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን ቅንጫቢ ዜና በመሥራት ብቻ ሲያልፉት መታዘቡንና  ይህ አሠራር የተጠቀሰውን ሕግ በግልጽ የሚጥስ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከኦሮሚያ ባንዲራና መዝሙር ጋር በተከሰተው ችግር ላይ በሕዝብ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩ መረጃዎች፣ ከተጨባጩ እውነታ የራቁ የሕዝብን ድምፅ ያላሰሙ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪክ ማኅበራትና ከዕውነታው ጋር የቆሙ የመንግሥት ተቋማትን ሐሳብ በምንም መልኩ ያላካተቱ፣ የመንግሥት ኃላፊዎችን ሐሳብ ብቻ የሚያስተናግዱ መሆናቸውን መግለጫው አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የተዛባ መረጃ በማሰራጨት ለዘመናት በሰላም አብሮ የኖረን ሕዝብ የማጋጨት አደገኛ አዝማሚያ ስለመታየቱና እየተጠየቀ ያለው ጥያቄ ከክልል ዓርማና መዝሙር ጋር የተያያዘ ሆኖ ሳለ፣ ጉዳዩን ከአፍ መፍቻ ቋንቋና ከማንነት ጋር አያይዘው ያቀረቡ የመንግሥት ኃላፊዎችን ሐሳብ ደጋግሞ ማስተጋባት አባዜ ላይ መውደቃቸውን መግለጫው አትቷል፡፡

የመንግሥት ኃላፊዎችም ቢሆኑ ቋንቋና የማኅበረሰብ ማንነትን የተመለከተ ጥያቄ ባልቀረበበት ሁኔታ፣ የቋንቋ ጥላቻ እንዳለ አድርጎ ከፓርላማ ጀምሮ እስከ መገናኛ ብዙኃን ስቱዲዮዎች ድረስ ደጋግሞ ማስተጋባት ግጭት መቀስቀስ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በሩዋንዳ የደረሰውን የዘር ፍጅት ሚዲያዎች እንደቀሰቀሱት ያስታወሰው መግለጫው፣ ከሕዝብ ማንነት ጋር የተገናኙና ስሜታዊ የሚያደርጉ የሐሰት ዘገባዎችን በስፋት ማሰራጨት ከባድ ወንጀል መሆኑም ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

በሕዝብ ሚዲያዎች ባለፉት ሳምንታት በዜና፣ በዜና ትንታኔና በፕሮግራም መልክ ከአሥር ጊዜ በላይ ይህንኑ የአዲስ አበባ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጉዳይ በተመለከተ አሳሳች መረጃዎች መሠራጨታቸውን አስታውቋል፡፡

ከሕግም፣ ከሞራልም ውጪ በሆነ አሠራር የሕዝብ ተቋምን ከዘላቂ የአገር ጥቅም በተፃራሪው የአንድ ቡድንን ፍላጎት ማስተናገጃ ማድረግ በአስቸኳይ ካልተስተካከለም ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደሩ የሕዝብ ሚዲዎች በፓርላማ የተጣለበትን ሕግ የማስከበር ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆኑትን የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን የአንድን ወገን ፍላጎት ብቻ ማስፈጸሚያ መሆናቸውን እንዲያቆሙ አስቸኳይ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ፓርቲው ጠይቋል፡፡

በሌላ በኩል በሕወሓት ኢሕአዴግ ዘመን የፓርቲ ንብረት የነበሩና አሁን ይዞታቸው በምን ሕጋዊ መሠረት ላይ እንደቆመ ግልጽ ያልሆኑት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት እንዲሁም ዋፋ ባለቤትነታቸው ለሕዝብ ግልጽ እንዲደረግና ኦዲት ተደርገው ወደ ሕዝብ ሀብትነት እንዲዛወሩ ኢዜማ ጠይቋል፡፡

መንግሥት የሕትመት መገናኛ ብዙኃን በወረቀት፣ የሕትመትና ሌሎችም የሕትመት ግብዓት ዋጋ መናር ከገበያ እየወጡ በመሆኑ የዘርፉን ችግሮች የሚቀርፉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንዲያደርግ ፓርተው ጠይቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...