Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየራያ ጉዳይ በሕገ መንግሥቱ ይታያል መባሉን እንደሚቃወም የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ገለጸ

የራያ ጉዳይ በሕገ መንግሥቱ ይታያል መባሉን እንደሚቃወም የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ገለጸ

ቀን:

  • ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ሊጠይቅ ነው

በኢዮብ ትኩዬ

በትግራይና በአማራ ክልል ወሰን አካባቢ የሚገኘው ራያ የማንነት ጉዳይ፣ በሕገ መንግሥቱ ይታያል መባሉን እንደማይቀበለው የአላማጣ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

መንግሥት በራያና በወልቃይት በኩል ለዘመናት እየተነሱ ያሉ የወሰን ጥያቄዎች ‹‹በሕገ መንግሥቱ ይታያሉ›› ማለቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ግን ጉዳዩን እንደሚቃወምና ሕዝበ ውሳኔ መደረግ እንዳለበት እየገለጸ ነው፡፡

- Advertisement -

የራያ ጉዳይ በሕገ መንግሥቱ ይታያል መባሉን እንደማይቀበሉትና ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን፣ የአላማጣ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሞገስ እያሱ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የማንነት ጥያቄ ላላቸው አካባቢዎች የራሴን ሕጋዊ የሆነ አካሄድን እከተላለሁ ማለቱን የጠቀሱት የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊው፣ ‹‹እኛ እንደ ሕዝብ ሕገ መንግሥቱ ከመፅደቁ (ከ1987 ዓ.ም.) ጀምሮ ግፍ እየደረሰብን ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ሕገ መንግሥቱ ከመውጣቱ በፊት ወደ አማራ ክልል ስለተከለልን፣ አሁን ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርገን አናስተናግድም፡፡ ስለዚህ ወደ ወሎ መጥተናል የሚለው ውሳኔ የአብዛኛው ሕዝብ ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተያያዘም ከሕግ ውጪ መሄድ ተገቢ ስላልሆነ ውሳኔ ሕዝብ (ሪፈረንደም) ሊካሄድ ይችላል የሚል አቋሞች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

‹‹እስካሁን በአማራ ክልል እንደተከለልነውና አሁን ባለው ቢሆንም ይቻላል፡፡ ካልሆነ ደግሞ ሪፈረንደም የሚደረግ ከሆነ ለሪፈረንደሙ ዝግጅት እያደረግን ነው፤›› ሲሉ ነው አቶ ሞገስ የገለጹት፡፡

‹‹በሕገ መንግሥቱ መሠረት መታየትም መጠየቅ የለብንም፤›› ያሉት አቶ ሞገስ ምናልባት ይህ አሁን ላለው መንግሥት አሳማኝ ሆኖ ካልቀረበና ወደ ሪፈንረደም የሚካሄድ ከሆነም ሙሉ ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

የማንነት ጥያቄ ለዓመታት ቢቀርብም ሳይፈልጉ ወደ ትግራይ ክልል ተገደው ተካለው እንደቆዩ፣ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ነበሩበት ወደ አማራ ክልል ወሎ እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

‹‹ከ2013 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥትም አምኖበት በአማራ ክልል ሥር ሆነን እየተዳደርን ነበር፡፡ አሁንም በዚያ ሥር ነው እየቀጠልን ያለው፤›› ያሉት አቶ ሞገስ፣ የራያ ጉዳይ እንደገና በሕገ መንግሥቱ ነው የሚታየው መባሉን ግን እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በአማራና በትግራይ ክልል ወሰን አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተቀስቅሶ በነበረውና አሁን በሰላማዊ መንገድ እየተፈታ ባለው ጦርነት፣ ነዋሪዎቹ ወደ ትግራይ ክልል መሆን አለባቸው በመባሉ የከፋ ሁኔታ እንዳሳለፉ ተጠቅሷል፡፡

አቶ ሞገስ በአላማጣ ከተማና በራያ አካባቢ የሚገኙ ከአሥር ሺሕ በላይ ወጣቶች የእስርና የድብደባ ሰቆቃ ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡

አቶ ሞገስ የራያን ጉዳይ በሕገ መንግሥቱ ማየት ተቀባይነት እንደሌለው፣ በወሰን አካባቢ የሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹ምላሹን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት እንሰማለን፤›› ያሉት አቶ ሞገስ፣ ስድስት አካባቢዎች ማለትም ኮረም ከተማ ኦፍላ ወረዳ  (በጥራሪ ድንበር የሚገኘው ዛታ ወረዳ)፣ እንዲሁም በራያ አላማጣ በኩል ራያ ባላ፣ አላማጣ ከተማና መኾኒ በሕገ መንግሥቱ ሳይሆን በሕዝበ ውሳኔ መታየት እንዳለባቸው ነው የተናገሩት፡፡

በወልቃይትና በራያ በኩል ከ30 ዓመታት በላይ የማንነት ጥያቄ ሲነሳ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሁለቱ አካባቢዎች በሚነሳው የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ታይቶ እንደሚፈታ መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...