Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትፌዴሬሽኑ ለቻን ውድድር ከጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ 20.8 ሚሊዮን ብር ብቻ ተለቀቀለት

ፌዴሬሽኑ ለቻን ውድድር ከጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ 20.8 ሚሊዮን ብር ብቻ ተለቀቀለት

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአልጄሪያ በሚዘጋጀው የአፍሪካ አገሮች ሻምፒዮና (ቻን) ለመካፈል ለአስተዳደራዊ ወጪዎች 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ከመንግሥት ጠይቆ 20.8 ሚሊዮን ብር እንደተለቀቀለት ተገለጸ፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሐሙስ ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ስለብሔራዊ ቡድኑ አጠቃላይ ዝግጅትና ስለፌዴሬሽኑ አስተዳደራዊ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፣ ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አቅርቦት የነበረውን የገንዘብ ጥያቄ ማግኘቱን ገልጾ፣ በሻምፒዮናው ላይ ለመካፈል ወደ ሥፍራው እንደሚያቀና ገልጿል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ማብራራያ የሰጡት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን፣ ፌዴሬሽኑ የጠየቀው የገንዘብ መጠን በቂ ነው ማለት እንደማይቻልና ፌዴሬሽኑ የጎደለውን ለመሙላት የተለያዩ አማራጮችን እንደሚከተል አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

የተለያዩ አገሮች ለብሔራዊ ቡድናቸው በጀት እንደሚያፀድቁ የጠቆሙት የጽሕፈት ቤት ኃላፊው፣ መንግሥት ብሔራዊ ቡድኑን በገንዘብ መደገፍ ግዴታ አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‹‹ውድድሩ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ለስፖርትና ባህል ሚኒስቴር የ50 ሚሊዮን ብር ጥያቄ አቅርበናል፤›› በማለት አቶ ባህሩ አስረድተዋል፡፡

እንደ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ማብራሪያ ከሆነ፣ ብሔራዊ ቡድኑ በውድድር እስከ መጨረሻው ተሳትፎ ለማድረግ መታቀዱንና በዚያም መሠረት በቂ ስሌት ተደርጎ 50 ሚሊዮን ብር መጠየቁን አስታውሰዋል፡፡

‹‹50 ሚሊዮን ብር ስንጠይቅ መንግሥትም ግዴታ ስላለበት ነው፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚወክለው ብሔራዊ ቡድኑ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ በጀት ስላጠረው ብቻ የገንዘብ ጥያቄው ድጋፍ እየጠየቀ ማስመሰል ተገቢ አይደለም፤›› ሲሉ የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አክለዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ አራት ጨዋታዎችን በቻን ማጣሪያው ያደረገ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ ሁለቱን በሜዳው ማድረግ ሲገባው በባዕድ አገር ማድረጉ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተብራርቷል፡፡

ከፊፋና የተለያዩ ስፖንሰሮች ድጋፍ የሚያገኘው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ ጨዋታውን በአገር ውስጥ ማድረግ አለመቻሉ ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉን ጠቅሰዋል፡፡  ከዚህም ባሻገር በዓለም ዋንጫ ምክንያት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የቀጥታ ሥርጭት በመቋረጡ፣ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞች በድሬዳዋ ከትመው የተጫዋቾች ምልመላ እንዳደረጉና ሙሉ ወጪው መሸፈኑን ፌዴሬሽኑ አብራርቷል፡፡

‹‹መንግሥት ካለበት ጫና አንፃር ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን እንደሚቸገር ገልጾ፣ 20.8 ሚሊዮን ብር ብቻ መሸፈን እንደሚችል አሳውቆናል፤›› በማለት አቶ ባህሩ አስረድተዋል፡፡

የተፈቀደው ገንዘብ በቂ ባይሆንም ፌዴሬሽኑ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ቀሪ ወጪዎችን ለመሸፈን ማቀዱን አቶ ባህሩ ገልጸዋል፡፡ ከዚያም ባሻገር ፌዴሬሽኑ  ወጪ ቆጣቢ ዝግጅቶችን እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

በዚህም አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሞሮኮ ጋር የጋራ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ፣ ብሔራዊ ቡድኑ በሞሮኮ ዝግጅት ሊያደርግ የሚያስችለውን ሁኔታ ሲያመቻች መቆየቱን የጽሕፈት ቤት ኃላፊው ያስረዳሉ፡፡

በዚህም የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ላይ ስለነበረው ፌዴሬሽኑ ቶሎ ምላሽ አለመስጠቱን የጠቀሱት የጽሕፈት ቤት ኃላፊው፣ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአውሮፕላን ትኬት ወጪ ያሉትን ወጪዎች ማለትም የሆቴል፣ የልምምድ ፋሲሊቲ፣ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ማመቻቸትና ዳኛ በመመደብ ዝግጅት ለማድረግ ሙሉ ወጪ ለመሸፈን ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተጠቁሟል፡፡

ጥሪውን ተከትሎም ከብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ጋር በመወያየት፣ በሞሮኮ ዝግጅቱን ለማድረግ የተወሰነ ሲሆን፣ ብሔራዊ ቡድኑ ከታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ወደ ሞሮኮ ያቀናል፡፡

‹‹ብሔራዊ ቡድኑ ለምን በአልጄሪያ ዝግጅት አያደርግም፤›› የሚል አስተያየት ሲሰጥ መክረሙን የሚያነሱት የጽሕፈት ቤት ኃላፈው፣ ከአልጄሪያ ይልቅ ሞሮኮ የአቋም መከላከያ ጨዋታ አማራጭ በመኖሩ ተመራጭ እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል፡፡

በዚህ ጉዞ ላይ 41 ልዑካን የሚጓዙ ሲሆን፣ 26 ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች የሚጓዙ ይሆናል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ ካቀረቡ በኋላ፣ ጌታነህ ከበደ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሉን ተከትሎ፣ ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱ ይታወሳል፡፡ ውዝግቡን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች ሲቀርቡ የሰነበቱ ሲሆን፣ የዋሊያዎቹ አሠልጠኝ በበኩሉ፣ ተጫዋቹ ጥሪ በተደረገላቸው ዕለት ጀምሮ ወደ 26 ተጫዋቾች ወደ ሆቴል የገቡ ሲሆን፣ ጌታነህ ከስብስቡ ውስጥ ባለመገኘቱ እንደተቀነሰና የግሉ ውሳኔ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡

ታኅሣሥ 18 ቀን 26 ተጫዋቾች ወደ ሆቴል መግባታቸውን የጠቀሱት አሠልጣኙ፣ አንድ ተጫዋች የቤተሰብ ጉዳይ ስላጋጠመው፣ እንዲሁም አንድ ተጫዋች ደግሞ አርፍዶ በመምጣቱ ከስብሰቡ ውጪ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በሞሮኮ ቆይታው ከሞሮኮ የቻን ቡድን ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደሚያደርግ ተነግረዋል፡፡ ዋሊያዎቹ በሞሮኮ ስምንት ቀናት ቆይታ ካደረጉ በኋላ ወደ አልጄሪያ እንደሚጓዙ ገልጸዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...