በዓለም እግር ኳስ ታሪክ፣ ሦስት ጊዜ የዓለም ዋንጫን (1958፣ 1962፣ 1970) ለአገሩ ብራዚል ያስገኘው፣ በዚህም በዓለም ብቸኛው የሆነው፣ እጅግ አስደናቂ በነበረው አጨዋወቱ ዝንተ ዓለም የሚነሳው ፔሌ፣ ባደረበት ሕመም ምክንያት ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በ82 ዓመቱ አርፏል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ፣ ከሁለት አሠርታት በላይ ባስቆጠረው የአግር ኳስ ሕይወቱ1363 ጨዋታዎችን አድርጎ 1281 ጊዜ ኳስን እና መረብን በማገናኘት ክብረ ወሰኑን ጨብጧል። ለብሔራዊ ቡድኑ 92 ጊዜ ተሰልፎ 77 ጎሎችን አስቆጥሯል። በሚሌኒየሙ በዓል ላይ የፊፋ የክፍለ ዘመኑ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ መመረጡ ይታወሳል። በአንድ ወቅት የብራዚል ስፖርት ሚኒስትር ስለነበረው ፔሌ ሐዘኑን የገለጸው የብራዚል እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን፣‹‹ፔሌ ከምንጊዜውም ምርጥ የስፖርት ሰውም በላይ ነው፤›› ሲል አሞካሽቶታል። ዜና
ዕረፍቱን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ የሦስት ቀናት ሐዘን አውጀዋል። ሥርዓተ ቀብሩ
በእናት ክለቡ ሳንቶስ አማካይነት ማክሰኞ ታኅሣሥ 25 ቀን ይፈጸማል።
- Advertisement -
- Advertisement -