Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊጉንፋን መሰሉ ወረርሽኝና የኮቪድ-19 ክትባት ጥሪ በታደሰ ገብረማርያም

ጉንፋን መሰሉ ወረርሽኝና የኮቪድ-19 ክትባት ጥሪ በታደሰ ገብረማርያም

ቀን:

በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች መሰንበቻውን የተከሰተው ጉንፋን መሰል ወረርሽኝ በርካቶችን ለሕመም ዳርጓል፣ ብዙ ሰዎች ታመዋል፡፡ ተህዋሱ ከሰው ሰው ልዩነት ያለው የሕመም ምልክቶችን ያሳያል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በብሔራዊ የኢንፍሉዌንዛ ላቦራቶሪ በናሙናዎች ላይ ምርመራን ካደረገ በኋላ ወረርሽኙ የዝናብ ወራት ማለፍን ተከትሎ የተከሰተና የተስፋፋ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡

የጉንፋን ወረርሽኙ ከኮቪድ-19 ጋር ይያያዝ ይሆን የሚለውም ሥጋት መፍጠሩ አልቀረም፡፡ በአገሪቱ የኮቪድ-19 በአሁን ጊዜ የመጨመር አዝማሚያ ቢያሳይም በጉንፋን ወረርሽኙ የተያዙ ሁሉ በኮቪድ የተያዙ ናቸው የሚል መደምደሚያ አለመኖሩን ኢንስቲትዩቱ በሰጠው መግለጫ ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ  በተለይም ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች የጤና ባለሙያዎችን ቀረብ ብለው እንዲያማክሩ አሳስቧል፡፡

ወረርሽኙ ኮቪድ-19ን ጨምሮ የበርካታ መተንፈሻ አካላት በሽታዎች ምልክት ሊሆን እንደሚችል፣ ኮቪድ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን ይወሳል፡፡

- Advertisement -

እንደ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጫ ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ የሰሞኑ ጉንፋን የሚያስከትላቸው ሕመሞች ብርድ ብርድ ማለት፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ሳል፣ ኃይለኛ የራስ ምታት፣ የመገጣጠሚያ ሕመም፣ ቁርጥማት፣ የምግብ ፍላጎትና የማጣጣም ስሜት መቀነስ ናቸው፡፡

እንዴት መከላከል ይቻላል?

በሕክምና ባለሙያዎች ምክር መሠረት የመከላከያ መንገዶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም፣ ንክኪዎችን መቀነስና መጠንቀቅ፣ በማስነጠስና በማሳል ጊዜ አፍና አፍንጫን በአግባቡ መሸፈን፣ ተመርምሮ መታከም፣ የተመጣጠነ ምግብ መውሰድ፣ የአመጋገብን ሥርዓት ማስተካከል ናቸው፡፡

 በተጨማሪም የቤት ውስጥ ሕክምናን ማለትም ትኩሳትና ራስ ምታትን የሚቀንስ መድኃኒት እንክብል በመዋጥ፣ ትኩስ ፈሳሾችን በመጠጣት፣ ንፅሕናን በመጠበቅና ዕረፍት በማድረግ ጤናን መጠበቅ ይቻላል፡፡

የኮቪድ መከላከያ ክትባት ጥሪ

የኮቪድ-19 በሽታ ሥርጭትን ለመግታት ኅብረተሰቡ የመከላከያ ክትባቱን እንዲከተብ የኢትዮጵያ የሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኮቪድ-19 በየክትባት ሁኔታና አጠቃቀም ላይ ባተኮረውና ኅብረተሰቡ እንዲከተብ ጥሪ የቀረበበት የምክክር መድረክ ላይ የማኅበሩ ዳይሬክተር ትዕግሥት መኰንን እንዳስታወሱት፣ ኮቪድ-19 መከሰቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ለውስብስብ የጤና ጉዳቶችና ለሞት ተዳርገዋል፡፡

ወረርሽኙን ለመግታት በተለያዩ አገሮች የተመረቱ የተለያዩ ዓይነቶች የኮቪድ-19 ክትባቶች መዳረሳቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሯ፣ ኢትዮጵያም የወረርሽኙን ሥርጭት ለመግታትና የወገኖችን በኮቪድ የመያዝ ምጣኔን ለመቀነስ ክትባቶቹን በግዥና በዕርዳታ አስገብታ ማዳረሷን ገልጸዋል፡፡

ኅብረተሰቡ ስለክትባቱ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ በመሆኑ ክትባቱ በሚፈለገው መልኩ ተግባር ላይ እንዳልዋለ የጠቀሱት ዳይሬክተሯ፣ በተለይም ወረርሽኙ ዓይነቱን እየቀያየረ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ መሆኑንና ክትባቱን ባልተከተቡ ወገኖች ስለሚባባስ ያልተከተቡ እንዲከተቡ ጥሪ አድርገዋል፡፡

በአዲስ አበባ ለአራት ጊዜ የክትባት ዘመቻ ማድረጉን የሚገልጸው የከተማዪቱ ጤና ቢሮ፣ አሁንም የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻው እየተካሄደ በመሆኑ ኅብረተሰቡ እንዲከተብ አሳስቧል፡፡

የኮቪድ-19 ወቅታዊ አገራዊ መረጃን በተመለከተ ከጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ባወጡት መረጃ፣ ካለፈው ሰኞ ታኅሣሥ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. አንስቶ እስከ ሐሙስ ታኅሣሥ 20 ድረስ 637 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በፅኑ የታመመ አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 497,840 ሲደርስ፣ ከበሽታው ያገገሙት ደግሞ 479,171 ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...