Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየዓለም ኢኮኖሚ በ2023 ምን ያጋጥመዋል?

የዓለም ኢኮኖሚ በ2023 ምን ያጋጥመዋል?

ቀን:

የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ‹‹በጣም ጨለማ ጊዜ›› ይለዋል የ2023ን ኢኮኖሚ ሲተነብይ፡፡ ከሦስት ዓመታት በላይ የዘለቀው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላም በሩሲያና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ እንዲያሽቆለቁል ከፍተኛውን አበርክቶ አድርገዋል፡፡

አይኤምኤፍ እንደሚለውም፣ የዓለም ኢኮኖሚ በ2022 ካስመዘገበው የ3.2 በመቶ ዕድገት በ2023 ወደ 2.7 በመቶ ያሽቆለቁላል፡፡ ይህም እ.ኤ.አ. ከ2001 ወዲህ ዝቅተኛ ነው፡፡

የድርጅቱ ዋና ኢኮኖሚስት ፔሪ ኦሊቨር ‹‹አሁን ላይ ቀውስ ውስጥ ባይገባም ዓመቱ ጥሩ አይሆንም፤›› ሲሉ 2023 ከ2022 የባሰ ከባድ እንደሚሆን ይገልጹታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የዓለም ሲሶ ኢኮኖሚ ያሽቆለቁላል ያሉት ደግሞ የአይኤምኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂቫ ናቸው፡፡ በዓለም ኢኮኖሚ ቀዳሚ ሚና ያላቸው አሜሪካ፣ ቻይናና  አውሮፓ ኅብረት ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያስመዘግቡ መሆኑም ዓመቱን ያከብዱታል፡፡

ሦስቱ ቀዳሚ የዓለም ኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች በተመሳሳይ ጊዜ የኢኮኖሚ ዕድገታቸው እየቀነሰ የሚሄድ መሆኑንም በመግለጽ፣ በዩክሬን ያለው ጦርነትና የወለድ ምጣኔ እየጨመረ መምጣቱ ለዘንድሮ የዓለም ኢኮኖሚ ማሽቆልቆል እንደ ምክንያት አንስተዋል፡፡

በዓለም በኢኮኖሚ ከበለፀጉ አገሮች በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠችው ቻይና ከ40 ዓመታት ወዲህ በዓለም ካስመዘገበችው ዕድገት ያነሰ ታስመዘግባለች ተብሎም ተገምቷል፡፡ በተለይ ኮቪድ-19ን ዜሮ ለማድረግ እየተገበረችው ያለው ‹‹ዜሮ ኮቪድ›› ፖሊሲ የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለመቀነስ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

የቻይና ኢኮኖሚ በ2023 ማብቂያ ላይ እያደገ እንደሚመጣም ተገምቷል፡፡ ቻይና ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት  34 በመቶ፣ 35 በመቶና 40 በመቶ ያህል ለዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ታበረክት የነበረ ቢሆንም፣ ዘንድሮ ይህን ማሳካት ከባድ ይሆንባታል፡፡ ይህ ደግሞ ለእስያ ኢኮኖሚ ጫና የሚፈጥር ነው፡፡

የአውሮፓ ኅብረት አገሮች በተለይ በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ምክንያት ኢኮኖሚያቸው ክፉኛ ተመትቷል፡፡ በመሆኑም ከኅብረቱ አባል አገሮች ግማሽ ያህሉ ኢኮኖሚያቸው የሚያሽቆለቁል (Recession) ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡ የአሜሪካ ኢኮኖሚ ደግሞ ያለውን ችግር ተቋቁሞ ይቀጥላል፡፡

የዓለም ኢኮኖሚ ቢያሽቆለቁልም የሠራተኛና አሠሪ ግንኙነት ጠንካራ መሆኑ በመልካም ጎኑ እንደሚወሰድ ጆርጂቫ ገልጸዋል፡፡

የዓለም ኢኮኖሚ ከማሽቆልቆል አልፎ ቀውስ ውስጥ ይገባል የሚል ትንበያ አሁን ላይ ባይኖርም፣ በዩክሬንና ሩሲያ መካከል ያለው ጦርነት እየከፋ ከሄደና  በቻይናና ታይዋን መካከል ያለው ውጥረት ካልረገበ የአቅርቦት ሰንሰለቱን የሚያውከው ይሆናል፡፡ ይህ የምግብና የሌሎችም አቅርቦቶች እጥረትና የዋጋ ግሽበት የሚያስከትል በመሆኑ የኢኮኖሚ ቀውሱን ሊያመጣው ይችላል፡፡

የዓለም ኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ይበልጡኑ የሚጎዳው ደግሞ በላቲን አሜሪካ መካከለኛ ገቢ እንዲሁም በአፍሪካ ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን አገሮች ነው፡፡

የወለድ ምጣኔ መጨመር፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና የገንዘብ ፖሊሲዎች እየጠነከሩ መሄድም ለ2023 የዓለም ኢኮኖሚ መዳከም ምክንያት ሲሆኑ፣ በሁሉም የንግድ መስኮች የገንዘብ ዝውውርና የሸማች ወጪ መቀነስ ተጠባቂ የ2023 ክስተቶች ናቸው፡፡

በ2023 የትኞቹ የንግድ ዘርፎች ኢኮኖሚ ይጎዳል?

   መቀመጫውን በፊሊፒንስ ያደረገው አማካሪ ድርጅት (ኬሲዲአይ) በድረ ገጹ እንዳሰፈረው፣ የችርቻሮ ዘርፍ በኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ከሚገዱ ዘርፎች አንዱ ነው፡፡

በኢኮኖሚው መዳከም ምክንያት ሸማቹ ከመሠረታዊ ነገሮች በስተቀር ይሸምታል ተብሎ ስለማይጠበቅ፣ በተለይም በጣም ወሳኝ ያልሆኑ ምርቶችን የሚቸረችሩ ተቋማት ፈተና ውስጥ ይገባሉ፡፡

ምግብ ቤቶችም (ሬስቶራንት) የችግሩ ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ፡፡ ምግብ ቤቶች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያም ለችግር የተጋለጡ እንደነበር ያስታወሰው ኬሲዲአይ፣ በ2023ትም ለችግር እንደሚጋለጡ ጠቁሟል፡፡

በኮቪድ-19 ምክንያት በጣም የተጎዳው የቱሪዝም ዘርፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት የሁለት ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ ገጥሞታል፡፡ በ2022 ማገገም ጀምሮ የነበረው ዘርፉ በ2023 በሚከሰተው የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ምክንያት የሚጎዳ ይሆናል፡፡ በኢኮኖሚው ምክንያት የጎብኚዎች የመጓዝ ፍላጎት የሚቀንስ በመሆኑም አየር መንገዶችንና ሆቴሎችን እንደሚጎዳ ተገምቷል፡፡

ሪል ስቴትና የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍም የኢኮኖሚ ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ በተለይ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በአቅርቦት ሰንሰለት፣ በሠራተኞችና በጥሬ ዕቃ ዋጋ መዋዠቅ የሚፈተን ይሆናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...