የዕውቋ ድምፃዊት አስቴር አወቀ አዲስ አልበም በጥምቀት በዓል ዋዜማ በከተራ (ጥር 10 ቀን) እንደሚለቀቅ ሰዋስው መልቲ ሚድያ አስታውቋል፡፡ ‹‹ሶባ›› የሚል መጠርያ የተሰጠውና አሥር ዘፈኖችን የያዘው አልበም በሰዋስው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች የሚደርስ ይሆናል፡፡
ለዚህም ዕውንነት ድምፃዊቷ ከሰዋስው መልቲ ሚድያ ጋር ታኅሣሥ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. መፈራረሟን ተቋሙ በድረ ገጹ ገልጿል፡፡ አስቴር አወቀ በድምፃዊነት ዘመኗ አዲሱን ሶባ ጨምሮ 25 አልበሞች አቅርባለች፡፡