Tuesday, April 16, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[የሚኒስትሩ ባለቤት ለማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠውን ገለጻ በቴሌቪዥን እየተከታተሉ ሳለ ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ገቡ]

 • ጎሽ እንኳን መጣህ።
 • ምነው?
 • እኔማ ሕዝቡ ብቻ ነበር የተማረረ የሚመስለኝ።
 • በምን?
 • በዋጋ ንረት።
 • ዋጋ ንረትን ምን አመጣው?
 • ይኸው አለቃችሁ አስሬ የፖለቲካ ማርኬት፣ የፖለቲካ ሸቀጥ እያሉ በምሬት ሲያወሩ አትሰማም እንዴ።
 • እ… እሱን ነው እንዴ?!
 • በእርግጥ ፖለቲካ እንደሚሸጥ አላውቅም ነበር። ግን ስንት ቢገባ ነው እንዲህ የተማረሩት?
 • ኧረ ተይኝ… በጣም ንሯል።
 • የምርት እጥረት ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለው?
 • ሁለቱም ነው።
 • ምን እና ምን?
 • የምርት እጥረቱ እንደኛው ነው።
 • ሌላውስ?
 • ሌላውማ ሕገወጥ ደላላውና በአቋራጭ ለመክበር የሚጥሩ ነጋዴዎች መኖራቸው ነው።
 • እዚያም እንደዚህ አለ?
 • ኧረ እንደውም ዋናዎቹ እዚህ ነው ያሉት።
 • ታዲያ ከውጭ ለምን አታስመጡም?
 • አይ እሱማ አይሆንም። ምንዛሬውም የለም።
 • ካልሆነ ቢያንስ ዋጋውን ለማረጋጋት አልሞከራችሁም?
 • እንዴት ብለን? ተቸገርን እኮ?
 • እንዴት? ቢያንስ ማቋቋም ያቅታችኋል?
 • ምን ማቋቋም?
 • የእሑድ ገበያ!

[ለቀናት ከቢሮ የጠፉት የሰላም ስምምነቱን አተገባበር የሚከታተሉት ክቡር ሚኒስትር ወደ ቢሮ ተመልሰዋል። አማካሪያቸውም በተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ሪፖርት ማቅረቡን ትቶ ስለ ሰላም ስምምነቱ አተገባበር እየጠየቃቸው ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር እውነት ይህ የሰላም ስምምነት የሚሳካ ይመስሎታል?
 • ለምን ተጠራጠርክ?
 • የሰላም ስምምነቱን ተቀብለው ቢፈርሙም የታጠቀ ኃይላቸውን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር አቅም ያላቸው አልመሰለኝም።
 • ለምን እንደዛ አልክ?
 • ከአንዳንድ የውጭ ተቋማት ጓደኞቼ ከምሰማው መረጃ እንደዚያ የሚሆን አልመስል አለኝ። በተጨማሪም…
 • እ… በተጨማሪ ምን?
 • የተወሰኑ ታጣቂዎች አፈንግጠዋል የሚል ወሬ ሰምቻለሁ።
 • በእርግጥ የሰላም ስምምነቱን ያልተቀበሉ ታጣቂዎች እንዳሉ ይታወቃል። በሌላ በኩል ደግሞ….
 • አየሰማሁ ነው… ይቀጥሉ
 • የተወሰኑ ኃይሎች ትጠቃቸውን እንደያዙ እየተበተኑና አንዳንዶቹም መሣሪያ እንደያዙ ወደ ቤተሰባቸው እየሄዱ መሆኑን ሰምተናል።
 • እንዴ! ታዲያ ይኼ ትክልል ነው?
 • እኛም እርስ በርሳቸው እንዳይጋጩና በነዋሪዎች ላይ ውንብድና እንዳይፈጽሙ ሠግተናል።
 • ክቡር ሚኒስትር ምሽግ የሚቆፍሩ እንደሆነም እኮ እየተወራ ነው?
 • አሱንም ሰምተናል።
 • ታዲያ ይኼ ልክ ነው?
 • እኛም ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ በታዛቢዎች ፊት ማብራሪያ ጠይቀናል።
 • ምን ምላሽ ሰጡ?
 • የታጠቀ ጦርን ካልተዋጋ ችግር ሊፈጥር ይችላል ነው የሚሉት።
 • ስለዚህ?
 • እኛ ሌላ ፍላጎት የለንም ነው የሚሉት።
 • ታዲያ ምሽግ የሚያስቆፍሩት ለምንድን ነው?
 • ከውጊያ ቀጠና በድንገት የወጣ ወታደር በሥራ ካልተጠመደ ያልተገባ ነገር ሊያስብ ስለሚችል ምሽግ እንዲቆፍሩ ማድረጋቸውን ነው የገለጹልን።
 • በታዛቢዎች ፊት እንደዚያ ያሉት?
 • አዎ።
 • እና እናንተ ይህንን አምናችሁ ተቀበላችሁ?
 • እኛ ሙሉ እምነት ባይኖረንም ምንም እንደማያመጡ ስለምናውቅ ብዙ አልተጨንቀንም። ግን …
 • እየሰማሁ ነው… ይቀጥሉ ክቡር ሚኒስትር?
 • በተወሰነ ደረጃ ምክንያታቸው ትክክል እንደሆነ እናምናለን።
 • ለምን?
 • ምክንያቱም ሥጋት አላቸው።
 • የምን ሥጋት?
 • እሱን መገመት ትችላለህ።
 • ገባኝ ገባኝ።
 • ምንድነው የገባህ?
 • ሥጋታቸው ምን እንደሆነ።
 • ምንድነው?
 • ታጣቂዎቹ አንድ ነገር ይሞክራሉ ብለው ፈርተዋል።
 • ምን ሊሞክሩ ይችላሉ?
 • ፈንቅል!

 

 

 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እየተከታተሉ አንዳንዴም በመገረም እየሳቁ አገኟቸው]

አንዴ? ምን አገኘሽ? ምን አገኘሽ ማለት? ለብቻሽ የሚያስቅሽ ማለቴ ነው? እ... ምን ላድርግ ብለህ ነው? ወዶ አይስቁ ሆኖብኝ ነው። እንዴት? ምንድነው ነገሩ? በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን እያዳመጥኩ ነዋ? አለቃ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር...