Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጥ መንገድ እየተወረሩ መሆናቸው ተገለጸ

በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጥ መንገድ እየተወረሩ መሆናቸው ተገለጸ

ቀን:

በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጥ መንገድ እየተወረሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ሽፈራው ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ታኅሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የቀረበ ሲሆን፣ ሪፖርቱን ለመታደም ከመጡ ተቋማት ከቀረቡ አቤቱታዎች መካከል የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት ክፍት የሆኑ ቦታዎች ሕገወጥ ወረራን ይመለከታል፡፡  

ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች እየተወረሩ መሆኑን፣ በታችኛው ዕርከን የሚገኙ አመራሮች የግብር ደረሰኝ እየሰጧቸው ያላግባብ ቦታዎቹ እየተሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የቤቶች ልማት ቢሮ በዚህ ጉዳይ ሁለትና ሦስት ቦታዎች ላይ ችግር እንዳጋጠመው በመግለጽ፣ ለአረንጓዴ ልማት የሚውሉ ቦታዎች ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎች መበራከታቸውን ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡

ቦታዎቹን በሕገወጥ መንገድ ወስደው በክረምት ወቅት ጤፍ የሚዘሩ ግለሰቦች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ የፍትሕ ቢሮው በጉዳዩ ላይ በቂ ትኩረት ማድረግ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በበኩላቸው፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት ተብለው የተተው ቦታዎችን ከሕገወጦች መከላከል እንደሚገባ በመግለጽ፣ ቦታዎቹን በባለቤትነት እንዲያስተዳድሩት የተሰጣቸው ተቋማት ተገቢውን ማስረጃ በመያዝ ሕገወጥ ወረራውን መከላከል እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

ለአረንጓዴ ልማት ከተተው ቦታዎች መካከል አንዱ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ፈይሳ፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጦች እንዳይያዙ የሚያስተዳድራቸው ተቋም ኃላፊነት እንደተሰጠው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሊኖረው ይገባል፡፡

በጋራ መኖሪያ ቤቶችና በማኅበር ቤቶች አካባቢ ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጦች ተወረዋል የሚሉ ክሶች እንደሚቀርቡ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

እነዚህን ቦታዎች አንዳንድ ጊዜ የሚያስተዳድሩ አካላት ማስረጃ እንደሌላቸውና በዚህም ሳቢያ የሚመጡ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ለአብነትም በአያት አካባቢ 10,000 ካሬ ሜትር ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች መያዛቸውን አክለዋል፡፡

ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ለአረንጓዴ ልማት ክፍት የተደረጉ ቦታዎችን የሚያስተዳድረው አካል ይዞታው በሥሩ እንደሚገኝ የሚገልጽ ማስረጃ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፣ ማስረጃው በሌለበት ግን ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ እውነታው ሌላ ሆኖ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ፣ ፍርድ ቤቶች በተቃራኒው የሚፈርዱበት ሁኔታ አለ ብለዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...