Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናቻይና ለኢትዮጵያ የዕዳ ስረዛ ለማድረግ ስምምነት ፈረመች

ቻይና ለኢትዮጵያ የዕዳ ስረዛ ለማድረግ ስምምነት ፈረመች

ቀን:

ሚኒስትሩ አፍሪካን ከክትባት ዕርዳታ ለማላቀቅ ታስቦ የተገነባው ማዕከል ይመርቃሉ

ከተሾሙ ገና አንደኛ ወራቸውን ያስቆጠሩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ በማድረግ፣ ከኢትዮጵያ አቻቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር የዕዳ ስረዛን ጨምሮ የተለያዩ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራረሙ።

የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ የሥራ ጉብኝታቸውን በተመረጡ አምስት የአፍሪካ አገሮች ለማድረግ ጉዟቸውን የጀመሩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ኢትዮጵያን የጉብኝታቸው ቀዳሚ መዳረሻ በማድረግ ማከሰኞ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም. አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ በቅድሚያም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በመቀጠልም ከኢትዮጵያ አቻቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝው፣ በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ ጉዳዮችና በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ዙሪያ መምከራቸው ታውቋል።

ከአቶ ደመቀ መኮንን ጋር ከተወያዩ በኋላም ኢትዮጵያ ከቻይና ከተበደረችው ውስጥ የተወሰነውን ዕዳ ለመሰረዝ የሚያስችል ስምምነት በሁለቱ ሚኒስትሮች መካከል እንደተፈረመ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ከዕዳ ስረዛው ስምምነት በተጨማሪም በሁለቱ አገሮች መካከል የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትም ሀሉቱ ሚኒስትሮች መፈራረማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቢሮ አስታውቋል።

ይሁን እንጂ በዕዳ ስረዛ ስምምነቱ ቻይና ምን ያህል የዕዳ ስረዛ እንደምታደረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቢሮ ያለው ነገር የለም። 

ኢትዮጵያ ባለፉት አስርና ከዚያ በላይ ዓመታት ከቻይና መንግሥት ተበድራ ያልከፈለችው ከ14 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕዳ እንዳለባት የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህም ኢትዮጵያ ካለባት አጠቃላይ 27.9 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ውስጥ ወደ ግማሽ የሚጠጋ ነው። 

የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱን የውጭ ዕዳ ጫና ለመቀነስ የጂ 20 አገሮች ባስቀመጡት የማገገሚያ አማራጭች ለመጠቀም ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ አሜሪካንን ጨምሮ የኢትዮጵያ አበዳሪ አገሮች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በምክንያት፣ እንዲሁም ቻይና ለኢትዮጵያ የሰጠችውን ብድር በግልጽ የሚያስረዳ የብደር ውል ሁኔታዎችን ማቅረብ አለባት በሚል ምክንያት፣ ኢትዮጵያ ያቀረበችው የውጭ ብደር ማቅለያ ጥያቄን ውሳኔ እንዳያገኝ ማድረጋቸውን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የወጡ መረጃዎች ያመለከታሉ። 

ቻይና ለኢትዮጵያ ከሰጠችው ብድር ውስጥ የተወሰነውን ለመሰረዝ መስማማቷ፣ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የውጭ ብድር ጫናን ለማቅለል የሚኖረው አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳዋ እንዲሸጋሸግላትና የመክፈያ ጊዜውም እንዲራዘምላት ለምዕራባዊያኑና ለፓሪስ ክለብ አባል አገሮች ያቀረበችው ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኝ ሊረዳ እንደሚችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት ዛሬ ረቡዕ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ በዚሁ ዕለት ሚኒስትሩ በቻይና መንግሥት ሙሉ ወጪ በአዲስ አበባ የተገነባውን የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል እንደሚመርቁ ታውቋል፡፡

ማዕከሉ አፍሪካን ከበለጸጉ አገሮች የክትባት ዕርዳታ ለማላቀቅ ታስቦ የተገነባ ሲሆን፣ የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሲሸፍን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ኃይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰፊ መሬት ከሊዝ ነፃ አቅርቧል።

ቻይና በዚህ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ላይ ተሳትፎ እንዳይኖራትና የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫም ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆን ምዕራባውያኑ አገሮች ከፍተኛ ጫና ሲያደርጉ እንደነበር አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ይህ ጥረት እንደማይሳካ ሲረዱ ደግሞ በእጅ አዙር በማዕከሉ ግንባትና ቀጣይ ተልዕኮ ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማዕከሉ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ብለው፣ በእጅ አዙር 1.3 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለአፍሪካ ኅብረት እንዳቀረቡ ዲፕሎማቱ ገልጸዋል። 

በአፍሪካ ኅብረት የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል የፖሊሲና ጤና ዲፕሎማሲ ኃላፊ የሆኑት ቤንጃሚን ጁዳልባይ (ዶ/ር) የአፍሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) ግንባታ ዕውን እንዲሆን የቻይናና የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ አስተዋጽ ማበርከታቸውን በቅርቡ ገልጸው ነበር።

የአፍሪካ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከሉ በበለጸጉ አገሮች ዕርዳታ ላይ የተመሠረተውን የአፍሪካ የክትባት ፍላጎት በራስ አቅም እንዲመረት ማድረግ ትልቁ ሥራው እንደሚሆን ቤንጃሚን (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ በአፍሪካ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን የሚያጠኑ ባለሙያዎችን ማፍራት፣ ክትባቶችን በራስ አቅም ማምረት፣ በክፍለ አኅጉራትና በሁሉም የአፍሪካ አገሮች የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከላትን ማቋቋምና ከተለያዩ አኅጉሮችና ሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት ጋር ትብብርን ማጠናከር እንደሆነም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ማዕከሉ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር፣ አፍሪካ በየዓመቱ እያጋጠማት ያለውን ከ100 በላይ ተላላፊ በሽታዎችና ወረርሽኞች በራሷ አቅም መቆጣጠር ያስችላታል ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...