Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለሁለት ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው የተራራቁት የሻምፒዮናዎቹ የመቐለ ጉዞ

ለሁለት ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው የተራራቁት የሻምፒዮናዎቹ የመቐለ ጉዞ

ቀን:

  • ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለክልሉ አትሌቲክስ ማቋቋሚያ ሁለት ሚሊዮን ብር ረዳ

ከሁለት ዓመታት በፊት በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ ተቋርጠው ቆይተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የነበሩ ክለቦች ልምምድ ማቆማቸውን ተከትሎ፣ ተጫዋቾች የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመው ወደ አዲስ አበባ መሸሻቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህም ባሻገር በክልሉ የተለያዩ ክለቦች ውስጥ የሚገኙ አትሌቶችን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ዝግጅት ለማድረግ ሽርጉድ የሚሉበት ወቅት በመሆኑ ማቄን ጨርቄን ሳይሉና ቤተሰቦቻቸውን እንኳን በቅጡ ሳይሰናበቱ ነበር ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ማግሥት የትራንስ ኢትዮጵያ፣ የመሶቦ ሲሚንቶና ሌሎች የትግራይ ክልል አትሌቶች ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

በዚህም መሠረት ዝግጅታቸውን አጠናቀው በብሔራዊ ቡድን ውስጥ የተካተቱ አትሌቶች ዝግጅታቸውን ሲያደርጉ ቀላል የሚባል ጊዜ አላሳለፉም ነበር፡፡ አትሌቶቹ ዝግጅት ሲያደርጉ አንድም በአገሪቱ እየተከናወነ ያለው ጉዳይ ሐሳብ ውስጥ የጣላቸው ሲሆን የነበረባቸው ጫናም የፀና ነበር፡፡

 ከዚህም ባሻገር አትሌቶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የነበረው የስልክ ግንኙነት መቋረጥ ችግሩን የከፋ አድርጎት ነበር፡፡

በወቅቱ አትሌቶቹን ለብሔራዊ ቡድን ከማሠለፍ ጋር ተያይዞ ከአገር ውስጥ እንዲሁም ከአገር ውጪ ከፍተኛ ጫና ሲደርስባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

አትሌቶቹ በብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በግል ሲያደርጉት በነበሩ ውድድሮች ላይ ሲሳተፉ፣ አንድም የቤተሰብ ጉዳይ በሌላ በኩል የአገሪቱ ሁኔታ ሌላ ፈተና ነበር፡፡ በዚህ ጫና ውስጥ የነበሩት አትሌቶቹ በኦሊምፒክ እንዲሁም በዓለም ሻምፒዮና ወርቅ፣ ብርና ነሐስን ከማሳካት በላይ የተለያዩ የዓለም ክብረ ወሰኖችን መስበር መቻላቸው የሚያስደንቅ ነበር፡፡

 አትሌቶቹም ይህንን ጫና ተቋቁመውና የአገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ማውለብለብ ቢችሉም ደስታቸው ጎዶሎ ነበር፡፡ አትሌቶቹ ላይ በነበረው ጫና ምክንያት አሠልጣኞቹም ሆኑ አትሌቶቹ ሐሳባቸውን ለሚዲያ መስጠት ታቅበው ለመቆየት ተገደው ነበር፡፡

በአንፃሩ በቅርቡ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ አትሌቶቹ ወደ ሚዲያው እያቀረቡ ሲመጡ ተስተውሏል፡፡ የዓለም 10 ሺሕ ሜትር ሻምፒዮናዋ፣ የዓለም 5,000 ሜትር፣ 10 ሺሕ ሜትር እንዲሁም ግማሽ ማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይ ለዚህ በማሳያነት ትጠቀሳለች፡፡ አትሌቷ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ሚዲያ ብቅ ብላ አስተያየቷን ስትሰጥ ተስተውሏል፡፡

አትሌቷ በ40ኛው የጃንሜዳ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ካሸነፈች በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ሚዲያ ቀርባ አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡

የትራንስ ኢትዮጵያ ክለብ አትሌት የሆነችው ለተሰንበት፣ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ክለቧን ወክላ መወዳደሯን ጠቅሳ፣ በተደረገው የሰላም ስምምነት ደስተኛ እንደሆነች ገልጻ፣ በዚህም ምክንያት በሚዲያ ቀርባ አስተያየት ለመስጠት አጋጣሚ እንደፈጠረላት አንስታለች፡፡

ማክሰኞ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ይዞ ወደ መቐለ ያቀናው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በመመራት ነው፡፡

በዓለም ሻምፒዮናና በኦሊምፒክ የተሳተፉ የብሔራዊ ቡድን አትሌቶች አሠልጣኞች እንዲሁም የሥራ አስፈጻሚ አባላት በጉዞው ተካተዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ አሉላ አባነጋ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሲደርስ በትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ ገብረ እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ)፣ የክልሉ አመራሮችና በአትሌቶች ቤተሰቦች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ለሁለት ዓመታት ተቆራርጠውና ተነፋፍቀው የቆዩ ቤተሰቦች በዕንባ እየተራጩ ሰላምታ ሲለዋወጡ ታይተዋል፡፡

በልዑካን ቡድኑ ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረሥላሴ፣ በሪሁ አረጋዊና ፍሬወይኒ ኃይሉ የመሳሰሉ አትሌቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ሥፍራው ማቅናት ከቻሉ አትሌቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ ለተሰንበት መቐለ ስለተደረገው ጉዞ አስተያየቷን የሰጠች ሲሆን፣ ‹‹ዛሬ የተሰማኝ ስሜት ሪከርዶችን ስሰብር ከተሰማኝ የሚልቅ የደስታ ስሜት ነው፤›› በማለት ተናግራለች፡፡ የአንድ ቀን ቆይታ የነበረው የመቐለው ጉዞ የተወሰኑ አትሌቶች እዚያው የሚቆዩ ሲሆን፣ ግማሹ የልዑካን ቡድን አባል ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስ ታውቋል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ዳግም ለማቋቋም የሚረዳ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ በፕሬዚዳንቷ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አማካይነት አበርክቷል፡፡

የጉዞ የመጀመርያ ግብ ለሁለት ዓመታት ያልተገናኙትን አትሌቶችንና ቤተሰቦችን ማገናኘት ሲሆን፣ ከዚያም ባሻገር በክልሉ ተቋርጦ የነበረውን የአትሌቲክስ እንቅስቃሴ ዳግም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ እንደሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

እንደ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ከሆነ፣ በክልሉ የሚገኙ ክለቦች ዳግም ወደ አትሌቲክሱ እንቅስቃሴ እንደሚመለሱና የክልሉ አትሌቲክስ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴው እንደ እንደሚመለስ ፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሠረት በክልሉ የሚገኙ መሶቦ ሲሚንቶ፣ ትራንስ ኢትዮጵያና የመሳሰሉ ክለቦች ወደ ቀድሞ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...