Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበኢትዮጵያ  ከወሊድ ጋር በተያያዘ በየቀኑ 38 እናቶች እንደሚሞቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ  ከወሊድ ጋር በተያያዘ በየቀኑ 38 እናቶች እንደሚሞቱ ተገለጸ

ቀን:

በኢትዮጵያ በዓመት 14 ሺሕ፣ በየቀኑ ደግሞ 38 እናቶች ከእርግዝና ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ የጤና ችግሮች ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለእናቶች ሞት መንስኤ የሆኑት ከወሊድ በኋላ በሚከሰት የደም መፍሰስ ከእርግዝና ጋር ተያይዞ በሚከሰት የደም ግፊት፣ በኢንፌክሽን፤ በረጅም ምጥና በደም ማነስ ምክንያት እንደሆነ  ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በጥር ወር የሚከበረውን ጤናማ የእናትነት ወርን አስመልክቶ ሚኒስትሯ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓመት ከ295 ሺሕ በላይ እናቶች በእርግዝና፣ በወሊድና ከወሊድ በኋላ በሚከሰቱ የጤና ችግሮች ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡

- Advertisement -

ከነዚህም ውስጥ 94 በመቶ የሚሆነው የእናቶች ሞት በታዳጊ አገሮች እንደሚከሰት  የገለጹት ሚኒስትሯ፣ ጤናማ የእናትነት ወር የመከበሩ ዋነኛው ዓላማ የእናቶችን ሕመምና ሞትን ለመቀነስ በሚደረገው አገራዊ ተግባራት ባለድርሻ አካላት የየበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ለማድረግ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የእናቶችን ጤና ለማሻሻል የሚያግዙ ተግባሮችም በሚከናወኑበት በዘንድሮው የጤናማ እናትነት ወር በጦርነት ቀጣናና በሌሎች የግጭት አካባቢዎች ውስጥ የነበሩ እናቶችን በማሰብ፣ አገልግሎት ያቋረጡ የጤና ተቋማትን መልሶ ሥራ እንዲጀምሩ እንደሚደረግ የሕክምና ግብዓቶችና መድኃኒቶችን ለማዳረስ እንደሚሠራም  ጠቁመዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሰው ሠራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች በተከሰተባቸው የተለያዩ ክፍላተ ሀገር እናቶችና ሕፃናት በመጀመሪያ ደረጃ የችግሮቹ ተጋላጭ መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ በእነዚህ አካባቢዎች የጤና አገልግሎት ተደራሽነት አለመኖር ወይም በተደራጀ ሁኔታ አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ በሁለቱ ላይ የሚደርሰው የጉዳት መጠን ከፍ ማለቱንም  ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

የእናትነት ወር ወሩን ሙሉ በተለያዩ መርሐ ግብሮች የሚከበረው፣ የማኅበረሰብ ንቅናቄ በመፍጠርና በየደረጃው ያሉ ባለድርሻና የውሳኔ ሰጪ አካላትን በእናቶች ጤና በይበልጥ በማሳተፍ፣ የተለያዩ ማስገንዘቢዎች በመሥራት እንደሆነ የገለጹት በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ሕፃናት ጤና ዳይሬክተሯ መሠረት ዘለዓለም (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በ1998 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መከበር የጀመረው ጤናማ የእናትነት ወር፣ ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን የሚከበረው ‹‹መከላከል በምንችላቸው ምክንያቶች የሚከሰቱ የእናቶች ሞት በጋራ እንግታ›› በሚል መሪ ቃል ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...