የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክርቤቶች በንብረት ላይ ሊጣል የታሰበውን ታክስ(Property Tax) ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሰበስቡ ዛሬ ጥር 3 ቀን2015 ዓም ባደረጉት የጋራ ውይይት ወሰኑ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ከፌደሬሽን የድጎማ፣ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ጋር በጋራ ባቀረቡት “የንብረት ታክስን የመሰብሰብ ስልጣን የፌደራል መንግስት ወይስ የክልል መንግስታትና ከተማ አስተዳደሮች?” በሚለው ላይ በተሰጠ ድምጽ፣ ታክሱን የመሰብሰብ ስልጣን የክልል መንግስታትና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሆን በአብላጫ ድምጽ ተወስኗል።