Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናቻይና ለአፍሪካውያን ባዶ ተስፋ እንደማትሰጥና ከፍላጎታቸው ውጪ ጣልቃ እንደማትገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ...

ቻይና ለአፍሪካውያን ባዶ ተስፋ እንደማትሰጥና ከፍላጎታቸው ውጪ ጣልቃ እንደማትገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስታወቁ

ቀን:

  • በመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ አገሮች ውክልና ማደግ አለበት አለች

የቻይና-አፍሪካ ትብብርን ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት ያላት ቻይና፣ ለአፍሪካውያን ባዶ ተስፋ እንደማትሰጥና ከአገሮች ፍላጎት ውጪ ጣልቃ እንደማትገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ቺን ጋንግ አስታወቁ፡፡

የውጭ ጉዳዩ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ሙሉ የግንባታ ወጪው በቻይና መንግሥት ተሸፍኖ፣ የመጀመርያ ምዕራፍ ግንባታው የተጠናቀቀውን የአፍሪካ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት (ሲዲሲ አፍሪካ) በተመረቀበት ሁነት ነው፡፡

‹‹ቻይና ባዶ ተስፋዎችን አትሰጥም፤›› ከአገሮች ፍላጎት ውጭ ጣልቃ እንደማትገባና ጫና እንደማታደርግ ያስረዱ ሲሆን፣ አፍሪካውያን ለአብነትም የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና መሥሪያ ቤትን ተጠናቆ ሲረከቡ፣ ተቋሙ ሙሉ  በሙሉ በአፍሪካ ኅብረት የሚመራና ምንም ዓይነት የቻይና ጣልቃ ገብነት የማይኖርበት ተቋም እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ የአፍሪካ ኅብረት ድጋፍ በጠየቀ ጊዜ ቻይና የተቻላትን ሁሉ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

ቻይና ከአፍሪካ የልማት ስትራቴጂ ጋር እንዴት በላቀ ሁኔታ ራሷን ታዛምዳለች በሚለው ላይ ጥናት እንደምታደርግ የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ በተለይም በአኅጉሪቱ የመሠረተ ልማት መርሐ ግብር፣ እንዲሁም የተቀናጀ የአፍሪካ ግብርና ልማት ፕሮግራሞችን እንዴት በተሻለ ሁኔታ መደገፍ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ድጋፏን እንደምታጠናክር አስታውቀዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤትም ሆነ በሌሎች ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች፣ የአፍሪካ አገሮች ውክልና ማደግ እንዳለበትም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

እንደ ቺን ጋንግ ገለጻ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የታዳጊ አገሮች፣ በተለይም የአፍሪካ አገሮች ውክልናና ድምፅ ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመው፣ ለዚህም ቻይና ጥረት ታደርጋለች ብለዋል፡፡

በአሜሪካና በቻይና መንግሥታት፣ እንዲሁም በሞሮኮና በኢትዮጵያ መንግሥታት መካከል ከመገንባቱ በፊት ውዝግብ ፈጥሮ የቆየው የአፍሪካ በሽታ አጠባበቅና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ)፣  ከ25 ወራት ግንባታ በኋላ የመጀመርያው ምዕራፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማኅመትን ጨምሮ፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ፣ እንዲሁም የበርካታ አፍሪካ አገሮች አምባሳደሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተመርቋል፡፡

የሲዲሲ አፍሪካ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ የአኅጉሪቱን የጤና አደጋ ምላሽ ለማፋጠን ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን፣ በሕንፃው ውስጥ የሚገኙ የሙከራ ማዕከላት ከአኅጉሪቱ በሙሉ ናሙናዎችን በመውሰድና ምርመር በማድረግ የምላሽ መስጠት ሒደቱን ያፋጥናሉ ተብሏል፡፡

የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከሉ አፍሪካን ከበለፀጉ አገሮች የክትባት ዕርዳታ ለማላቀቅ ታስቦ የተገነባ ሲሆን፣ የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሲሸፍን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ዘጠኝ ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት ከሊዝ ነፃ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...