Wednesday, February 1, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ለከተማ አስተዳደሩ እንድ ሹም በቢሮ ስልካቸው ላይ ደጋግመው ቢደውሉም ሊያገኟቸው ስላልቻሉ ወደ እጅ ስልካቸው ሞከሩ] 

 • ጤና ይስልጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ትላንት የቢሮ ስልክዎ ላይ ብደውል ለሥራ ወጥተዋል ተባልኩ፣ ዛሬም ስደውል ለሥራ ወጥተዋል ተባልኩ።
 • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር ቢሮ አልገባሁም ነበር።
 • እኔ ሳላውቅ የጀመሩት ነገር አለ እንዴ?
 • እርሶ ሳያውቁ ምን እጀምራለሁ ክቡር ሚኒስትር?
 • ለሌላ ከተማ መሥራት?
 • ትላንትም ዛሬም የመስክ ጉብኝት ፕሮግራም ነበረኝ ክቡር ሚኒስትር። ለአስቸኳይ ጉዳይ ፈልገውኝ ነው?
 • ሁለት ቀን ሙሉ ጉብኝት?
 • ባለፈው የከተማውን ካቢኔ ሰብስበው የሰጡትን ማሳሰቢያ ዘነጉት እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • የምን ማሳሰቢያ?
 • ብልፅግና የሚመጣው ቢሮ ቁጭ ብሎ በመዋል ወይም ቪኤይት እየነዱ በመዝናናት አይደለም፣ ፒክ አፕ እየነዱ ነው አላሉም?
 • ስለዚህ?
 • ስለዚህ ያለፉትን ሁለት ቀናት ፒክ አፕ እየነዳን ጉብኝት ላይ ነበርን።
 • ከተማ ለመጎብኘት ገዛን እንዳይሉኝ?
 • ምን?
 • ፒክ አፕ?
 • ወጪ ለመቆጠብ ብለን ከፌዴራል ተቋማት ለመዋስ ነበር ዕቅዳችን ነገር ግን
 • ግን ምን?
 • የፌዴራል ተቋማትም ለጉብኝት ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ በማመን…
 • ገዛን እንዳይሉኝ?
 • ገዛን!
 • ለከተማ ጉብኝት ፒክ አፕ?
 • ብልፅግና የሚመጣው ፒክ አፕ እየነዱ ነው አላሉም እንዴ?
 • ቆይ እሱ ይቆየንና ጉብኝት ላይ ነበርን ሲሉ ሙሉ ካቢኔውን ማለትዎ ነው?
 • አዎ። ሁላችንም በመስክ ጉብኝት ላይ ነበርን።
 • ምንድነው ስትጎበኙ የነበረው?
 • ሁሉም የካቢኔ አባል የተመደቡለትን ፕሮጀክቶች በየክፍለ ከተማው እየተዘዋወረ ሲጎበኝ ነበር።
 • ይህን ያህል ሰፊ ፕሮጀክት በከተማው አለ እንዴ?
 • ሰፊ ባይሆንም፣ ፕሮጀክቶች አሉን።
 • ሁሉንም የካቢኔ አባል ለጉብኝት የሚያስወጣ?
 • በተናጠል አይደለም ለጉብኝት የወጣነው።
 • እ…?
 • ጥንድ ጥንድ ሆነን ነው።
 • የባሰ አታምጣ አሉ!
 • ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • እስኪ እርስዎ የጎበኙትን ፕሮጀክት ይንገሩኝ?
 • እኔ የመረጥኩት የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ነው።
 • ፕሮጀክቶቹ ምንድናቸው?
 • እርስዎ ከካቢኔያችን ጋር በተወያዩበት ወቅት እንዲተገበሩ ያዘዟቸውን ፕሮጀክቶች ነው የጎበኘሁት።
 • ዘነጋሁት፣ ምን ነበሩ?
 • የ90 ቀን ፕሮጀክቶች፡፡
 • እህ… ታዲያ ይኼንን መቼ ነበር ያዘዝኩት?
 • እ… አዎ… አሁን ስድስተኛ ወሩን ጨርሶ ወደ ሰባተኛ ወሩን ይዟል።
 • እናንተ ግን የፕሮጀክት ስም አደረጋችሁት?
 • ምኑን?
 • በ90 ቀን ይፈጸም ያልኩትን?
 • እ… እንደዚያ ነበር እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • እርስዎን ጨምሮ ከካቢኔዎ ጋር አንድ ዙር ሳያስፈልገን አይቀርም።
 • ምን?
 • ውይይት!
 • ጥሩ። ጎብኝቱን ስንጨርስ መገናኘት እንችላለን።
 • ጎብኝቱም ይወስድባችሁ ይሆን?
 • ምን?
 • 90 ቀን!

[ክቡር ሚኒስትሩ የጎርጎራ ፕሮጀክትን ጎብኝተው ከተመለሱት ወዳጃቸው የቀድሞ ሚኒስትርና አምባሳደር ጋር እየተጨዋወቱ ነው]

 • ጉብኝቱ እንዴት ነበር አምባሳደር?
 • አምባሳደር ብለህ ባትጠራኝ ደስ ይለኛል?
 • ለምን?
 • በስሜ እንድትጠራኝ ነው የምፈልገው።
 • እንደዚያማ ትክክል አይሆንም?
 • ምን ችግር አለው?
 • አገርዎትን በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ ቆይተው?
 • ቢሆንም በስሜ እንድትጠራኝ ነው የምፈልገው ካልሆነ ግን…
 • እ… ካልሆነ ምን?
 • ካልሆነ እኔም አንተን ክቡር ሚኒስትር ብዬ አልጠራህም፡፡
 • ታዲያ ምን ብለው ሊጠሩኝ ነው?
 • የወደፊት አምባሳደር!
 • ኪኪኪኪ… ተጫዋች እኮ ነህ። ግን እንዴት ነበር?
 • ምኑ?
 • ለአምባሳደሮች የተዘጋጀው ጉብኝት?
 • እኔ ለምን እንዳስጎበኙንም አልገባኝም።
 • እንዴት?
 • ብዙዎቻችን ሚኒስትር እያለን የምናውቃቸውን ፕሮጀክቶች ነው የጎበኘነው።
 • ቢሆንም ፕሮጀክቶቹ አሁን የደረሱበትን ደረጃ መመልከቱ ችግር ያለው አልመሰለኝም። አለው እንዴ?
 • አብዛኞቻችን ፕሮጀክቶቹን እናውቃቸዋለን። በዚያ ላይ ደግሞ እኔ ብዙም አይገባኝም።
 • ምኑ?
 • የፕሮጀክቶቹ ፋይዳ፡፡
 • እንዴት እንደዚያ ይላሉ አምባሳደር?
 • ወደፊት ፋይዳ ይኖራቸው ይሆናል ነገር ግን አሁን ላይ ካለው የአገሪቱ ሕዝብ ፍላጎት አንጻር የረባ ፋይዳ ይኖራቸዋል ብዬ አላምንም።
 • እንዴት?
 • በአጭሩ ልግለጽልህ?
 • እሺ…
 • የፓርኮቹ ግንባታና በአንድ ወቅት በመላ አገሪቱ የተገነቡ የእግር ኳስ ስታዲየሞች አንድ ናቸው ወይም ለእኔ ይመሳሰሉብኛል።
 • ሁለቱን ደግሞ ምን ያመሳስላቸዋል?
 • ሁለቱም ከሚፈለጉበት ጊዜ ቀድመው መገንባታቸው።
 • አልገባኝም?
 • የእግር ኳስ ስታዲየሞች በሁሉም ክልሎች ቢገነቡም አገልግሎታቸው ግን ሌላ ሆኗል።
 • ምን ሆኗል?
 • የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ማክበሪያ!
 • ፓርኮቹ ግን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ማክበሪያ አይሆኑም።
 • ብሔር ብሔረሰቦችማ ቀናቸውን ማክበሪያ ቦታ አግኝተዋል።
 • ፓርኮቹ ግን የቱሪስቶች መዳረሻ ይሆናሉ።
 • መቼ?
 • አገሪቱ ስትረጋጋ።
 • ለዚያ እኮ ነው ለዚህ ትውልድ የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶች አይደሉም የምልህ።
 • እና ለዚህ ትውልድ የሚጠቅሙት ፕሮጀክቶች ምንድናቸው?
 • ፓርኮቹን አቆይቶ ፋብሪካዎቹን መጨረስ፡፡
 • የትኞቹን?
 • ብዙ የቆሙ ፋብሪካዎች አሉ አይደለም እንዴ?
 • እስኪ አንዱን ይንገሩኝ?
 • ስኳር ፋብሪካዎቹ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

በኦሮሚያ ክልል በስድስት ከተሞች የተዋቀረውን ሸገር ከተማን የማደራጀት ሥራ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ስድስት ከተሞች የተዋቀረው ሸገር ከተማን...

ኢትዮጵያ በትክክለኛ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሕገ መንግሥት ማበጀት እንደሚገባት ማሳሰቢያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ለተለያዩ ጥያቄዎችና ሐሳቦች...

የድሬዳዋን ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች ለመመለስ ሪፈረንደም እንዲካሄድ አማራጭ ሐሳብ ቀረበ

የድሬዳዋ አስተዳደር ራሱን የቻለ ክልላዊ መንግሥት እንዲሆን ወይም ከሶማሌና...

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ተግዳሮቶችና እየቀረቡ ያሉ መፍትሔዎች

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ግንባታዎችን በሚያካሂዱና በግንባታው ባለቤቶች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች...
- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...

የፀረ ሙስና ትግሉ ጅማሮና የመንግሥት ሠራተኛው

በንጉሥ ወዳጅነው   በኢትዮጵያ ሁኔታ የመንግሥት ሠራተኛ ወይም በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ...

በማይታይ መጠን ያለው ክፋታችንና መልካምነታችን!

በበድሉ አበበ አንዳንዶች እንደዚህ ይሉኛል፡፡ እገሌ እኮ በጣም ጤነኛ ነው፡፡...

ዳግም የተመለሰው የኢትዮጵያዊነት ድርጅት

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበርያ ድርጅት በምኅፃረ ቃል ‹‹ኢትዮጵያዊነት›› በመባል...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ምን ገጥሞህ ነው? ስምምነቱን ጥሰውታል ክቡር ሚኒስትር? ኧረ ተውው ተረጋጋ፡፡ እሺ ክቡር ሚኒስትር ይቅርታ... ደንቆኝ እኮ ነው። ስምምነቱን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ጋር ስለ ጫካ ፕሮጀክት እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ላቀረብነው የውይይት ጥያቄ ፈቃደኛ ስለሆኑና በአጭር ቀጠሮ በመገናኘታችን ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በጭራሽ ምስጋና አያስፈልገኝም። ተቃዋሚ ፓርቲ ስትባሉ ብትቆዩም እኛ ስንመጣ ተፎካካሪ ያልናችሁ...

[የሚኒስትሩ ባለቤት ለማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠውን ገለጻ በቴሌቪዥን እየተከታተሉ ሳለ ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ገቡ]

ጎሽ እንኳን መጣህ። ምነው? እኔማ ሕዝቡ ብቻ ነበር የተማረረ የሚመስለኝ። በምን? በዋጋ ንረት። ዋጋ ንረትን ምን አመጣው? ይኸው አለቃችሁ አስሬ የፖለቲካ ማርኬት፣ የፖለቲካ ሸቀጥ እያሉ በምሬት ሲያወሩ አትሰማም እንዴ። እ... እሱን...