Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኮሚሽኑ የመክሰስና የመመርመር ሥልጣኑን በመቀማቱ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ጠቋሚ መጥፋቱ ተገለጸ

ኮሚሽኑ የመክሰስና የመመርመር ሥልጣኑን በመቀማቱ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ጠቋሚ መጥፋቱ ተገለጸ

ቀን:

በሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ አዋጅ 668/2002 ዜጎች ‹‹አዋጅ ጥሷል›› በሚሉት ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥት ሠራተኛ ላይ ጥቆማ በማቅረብ ከፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ ቢቀመጥም፣ በአዋጁ መሠረት ምንጩ ያልታወቀ ሀብት የሚጠቁም ሰው እየጠፋ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሀብትን ማሳወቅና ማስመዝገብ የመንግሥት አሠራርን በግልጽነትና በተጠያቂነት ላይ ለመመሥረት፣ የሀብት ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከልና ዜጎች ምንጩ ያልታወቀ ሀብት እንዲጠቁሙና የሕግ ከለላ እንደሚደረግላቸው በዚህ አዋጅ ተቀምጧል፡፡

ይሁን እንጂ በ2008 ዓ.ም. በወጣው አዋጅ ለሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ተሰጥቶት የነበረው ክስ የመመሥረትና ምርመራ የማድረግ ሥልጣን ተቀምቶ፣ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከተሰጠ ወዲህ፣ ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን የሚጠቁሙ ሰዎች መጥፋታቸውን በሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ውስጥ የሚገኙ አንድ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር ተናገሩ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተመሳሳይ ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን ለሚጠቁሙ ሰዎች በምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ የወጣ አዋጅ ቁጥር 699/2002 የሕግ ከለላ እንደሚያገኙ ተቀምጧል፡፡

በዚህም የክስና የምርመራ ሥልጣን ከኮሚሽኑ ተቀምቶ ወደ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከሄደ ወዲህ በፍትህ ሚኒስቴር፣ በፖሊስና በፀረ ሙስና ኮሚሽን መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሠራር ዝቅተኛ በመሆኑ፣ እምብዛም ጥቆማ አለመቅረቡንና አልፎ አልፎ ጥቆማ ቢቀርብም በሥርዓቱ አስተባብሮ ማስኬድ አለመቻሉን ተገልጿል፡፡

በአዋጁ መሠረት ጥቆማ የሚያቀርብ ግለሰብ ከደጋፊ ማስረጃ ጋር በጽሑፍ ለኮሚሽኑ ወይም አግባብ ላለው የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል እንደሚቀርብ ተቀምጧል፡፡ በዚህም በቀረበው ጥቆማ መሠረት የተገኘው መረጃ፣ በወንጀል ሕጉ መሠረት የሀብት መውረስ ውሳኔ ለማሰጠት ካስቻለ የተወረሰው ሀብት ከሚያስገኘው ገቢ ውስጥ 25 በመቶ ለጠቋሚው እንደሚከፈል ተደንግጓል፡፡

አንድ ግለሰብ ያካበተውን ምንጩ ያልታወቀ ሀብቱ በዜጎች ተጋልጦና በፍትህ ሥርዓቱ አልፎ ውሳኔ ሲሰጥ የጠቋሚው ማንነት እንደተደበቀ ለሕዝብ ይፋ ቢደረግ፣ ለጠቋሚዎች በሕግ የተቀመጠውን የ25 በመቶ ድርሻና ለምንጩ ሙሉ ከለላ ስለመደረጉ ለማሳያነት ቢቀርብ፣ ዜጎች በየአካባቢያቸው የሚያውቁትን ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ለማጋለጥ የማምረቻው ተነሳሽነት ይጨምራል ተብሏል፡፡

የሥነ ምገባርና ፀረሙና ኮሚሽን ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ሙስናን ለመከላከል ላለው ፋይዳ በሚል በቅርቡ በሰመራ ከተማ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህ ውይይት በፍትህ ተቋማት፣ በኮሚሽኑና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካካል ያለው የጋራ ቁርጠኝነት አናሳ በመሆኑ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኮሚሽኑ የሥራ አመራር አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ እንደሚሉት ሕዝቡ በአዋጁ በተቀመጠው መሠረት ተጠቃሚ ለመሆን ሀብት ያከማቹ አካላትን የማጋለጥ ባህል አነስተኛ መሆንና የሚመለከታቸው አካላት መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሠራር ትምህርት በመስጠት ረገድ ዝቅተኛ በመሆኑ የሚታሰበውን ለውጥ ለማምጣት አሁንም ብዙ ይቀራል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...