Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአዲስ አበባ ከተማና ሸገር ከተማ በአዲሱ የአስተዳደር ወሰን መሠረት የሰነድ ርክክብ አደረጉ

አዲስ አበባ ከተማና ሸገር ከተማ በአዲሱ የአስተዳደር ወሰን መሠረት የሰነድ ርክክብ አደረጉ

ቀን:

የአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ተብሎ ይጠራ የነበረውና በቅርቡ ከአዲስ አበባ ጋር ከተካለለ በኋላ፣ የአዲስ አበባ ከተማና ልዩ ዞኑን የተካው የሸገር ከተማ አስተዳደሮች የሰነድ ርክክብ መፈጸማቸው ተገለጸ።

በዚሁ መሠረት ወደ አዲስ አበባ ከተማ የተካለሉ በቀድሞ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ የነበሩና በአዲሱ የአስተዳደር ወሰን መሠረት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዲካለሉ የተደረጉ አካባቢዎችን የተመለከቱ መረጃዎችና ሰነዶችን፣ አጎራባች ለሆኑ የአዲስ አበባ ክፍላተ ከተሞች ማስረከቡን የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጉግሳ ደጀኔ ገልጸዋል።

በተመሳሳይም በአዲስ አበባ ከተማ ሥር ሲተዳደሩ የነበሩና በተካለለው የአስተዳደር ወሰን መሠረት በቅርቡ ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ወይም ወደ ሸገር ከተማ እንዲካለሉ የተደረጉ አካባቢዎችን የተመለከቱ ሰነዶችንም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስረከቡን ገልጸዋል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹የባለቤትነት መብት የተፈጠረላቸው ላይ የሚቀየር ነገር የለም፤›› በማለት ያስረዱት ምክትል ከንቲባው፣ ወደ ኦሮሚያ የመጡትም እንዲሁ ፋይላቸው ዞሮ ርክክብ መፈጸሙን አብራርተዋል፡፡

በዚህም መሠረት ግንባታቸው ተጠናቆ ዕጣ የወጣባቸው የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶች የተገነቡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲሆን፣ የቤቶቹ ባለቤቶችም የተመዘገቡ ቆጣቢዎች በመሆናቸው ቤቶቹ ለቆጣቢዎች መተላለፋቸውን ጠቁመዋል፡፡

እንደ ምክትል ከንቲባው ገለጻ ከሆነ፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር በቤቶቹ ላይ የሚፈጥረው አዲስ ባለቤትነት አይኖረውም፡፡ ወደ ሸገር ከተማ አስተዳደር ሲተላለፉ የባለቤትነት መብት ተፈጥሮላቸው መሆኑን አክለዋል፡፡

ስለሆነም የሸገር ከተማ ኃላፊነት ከዚህ በኋላ ያለውን ሁኔታ ማስተዳደር ብቻ እንደሚሆን አቶ ጉግሳ ገልጸዋል፡፡

‹‹የቤቶቹ ባለቤቶች መብታቸውን ይዘው በሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር ይተዳደራሉ። የመሸጥ፣ የመለወጥና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው በሸገር ከተማ አስተዳደር የሚከናወን ይሆናል፤› ሲሉ አቶ ጉግሳ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በሚገኙ ስድስት ከተሞች የተዋቀረው ሸገር ከተማን የማደራጀት ሥራ መጀመሩን ተከትሎ፣ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ማቋቋሙ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት የምክር ቤቱ ማቋቋሚያ ጉባዔ አቶ ተሾመ አዱኛን የሸገር ከንቲባ፣ አቶ ቃባቶ አልቤን የከተማው ምክር ቤት አፈ ጉባዔ፣ እንዲሁም ወ/ሮ ፀሐይ ደበሌን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መሾሙ አይዘነጋም፡፡

የሸገር ከተማ አስተዳደር ያፀደቃቸውን ሹመቶች ተከትሎ ከተመራጮቹ ውክልና ጋር ተያያዞ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን፣ የምክር ቤቱ አባላት ከዚህ ቀደም በነበረው አገራዊ ምርጫ ተመርጠው ውክልና ያገኙና በልዩ ዞኑ በነበሩት ቢሮዎች ሥር ኃላፊነት ተረክበው ሲያገለግሉ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ልዩ ዞን ከተሞች ውስጥ የነበሩ የቢሮ ሠራተኞች በሙሉ፣ በተዋረድ በሸገር ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች ኃላፊነት ወስደው እንደሚያገለግሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

ክልሉ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ስድስት ከተሞችን በአንድ ከተማ አስተዳደርና በአንድ ከንቲባ እንዲመራ መደረጉን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ገላንና መናገሻ በሥሩ የሚገኙ ከተሞች ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...