Wednesday, December 11, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንበሩ ካለመወረሱ በስተቀር መፈንቅለ ሲኖዶስ መደረጉን ቤተ ክህነት አስታወቀ

መንበሩ ካለመወረሱ በስተቀር መፈንቅለ ሲኖዶስ መደረጉን ቤተ ክህነት አስታወቀ

ቀን:

spot_img
  • ቅዱስ ሲኖዶስ ከነገ ጀምሮ ውይይት እንደሚጀምር ተነገረ
  • ‹‹እኛ ወታደርም ሆነ ፖሊስ የለንም ያለን መስቀላችን ብቻ ስለሆነ ፀጥታን ማስጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት ነው››

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (/)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በማያወቀውና የቤተ ክርስቲያንን ሕግ ባልጠበቀ መንገድ “በእነ አቡነ ሳዊሮስ” ተሰጠ በተባለው ሕገ ወጥ የጵጵስና ሢመትን በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ለዛሬ ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በፀሎት ጀምሮ፣ ነገ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት እንደሚጀምር ቤተ ክህነት አስታወቀ፡፡ የቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃምና የሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ አቡነ ጴጥሮስ እንደተናገሩት፣ መንበሩ ካለመወረሱ በስተቀር መፈንቅለ ሲኖዶስ መደረጉን ቤተ ክህነት አስታወቀ፡፡

ምልዓተ ጉባዔው የተጠራው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባስተላለፉት ጥሪ መሠረት እንደሆነ የታወቀ ሲሆን፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት እንደሚታደሙ ተገልጿል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ትናንት ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተላለፈው መልዕክት፣ መንግሥት ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔው ጥበቃ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በወሊሶ ከተማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀኖና ውጭ ተፈጽሟል የተባለውን ‹‹የፓትሪያርክና የ26 ጳጳሳት ሹመት›› ተከትሎ በዕለቱ ቅዱስ ሲኖዶስ በአገር ውስጥና በውጪ አገር ያሉ ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ለአስቸኳይ ስብሰባ ወደ መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት እንዲመጡ ማሳሰቡ ይታወሳል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) እንዲሁም ብፁዕ አቡነ አብርሃም በሰጡት መግለጫ፣  ‹‹የመንግሥት አካላት በተለይም ፀጥታን በሚመለከት እስካሁን ድረስ እንደምናየው በበሩም፣ በእያንዳንዱ አካባቢ የፖሊስ ጥበቃዎች ነበሩ፣ አሁን ግን ከዛሬ ጀምሮ (ጥር 16 ቀን 2015) በማን እንደሆነ ሳይታወቅ ተነስተዋል፤›› በማለት ያስረዱት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)፣ ‹‹መንግሥትን የሚመለከት ስለሆነ፣ በየትኛውም ሁኔታ ፀጥታን የማስጠበቅ የመንግሥት ግዴታም ኃላፊነትም ስለሆነ በዚህ አጋጣሚ ፀጥታ እንድታስከብሩ በቤተ ክርስቲያን ስም እንጠይቃለን፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

‹‹እኛ ወታደር የለንም፣ ፖሊስ የለንም፣ እኛ ያለን መስቀላችን ብቻ ነው፣ ፀጥታን ማስጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት ስለሆነ በተለይም የአዲስ አበባና የፌደራል ፖሊስ፣ በየቦታው ያላችሁ የፖሊስና የፀጥታ አባላት ይህን እንድታስጠብቁ አደራ እንላለን፤›› በማለት አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አሳስበዋል፡፡

ይህን ምክንያት አድርጎ ምንም ዓይነት ነገር ቢፈጠር ምዕመኑ በፀጥታና በፀሎት በትህትና እንዲጠብቅ የተጠየቀ ሲሆን፣ መናደድ፣ መበሳጨት እንዲሁም የኃይለ ቃል ንግግርን ትቶ ቤተ ክርስቲያንን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በበኩላቸው ‹‹ተቋምን የመጠበቅ ኃላፊነት የመንግሥት ነው፣ ከዚህ መቼውኑም መሸሽ አይቻልም፡፡ በዛሬው ዕለት ያየነውም የሰማነውም ነገር ቢኖር በሙሉ ጥበቃ ያደርጉ የነበሩና ሲተባበሩ የነበሩ ሁሉ ‹‹በቃ ተዋቸው›› ተብሎ አዛዡ ማን እንደሆነ በማናውቀው ሄደዋል፤›› በማለት የተናገሩ ሲሆን፣ ‹‹ይህ ማለት ችግር ቢፈጠር እንደፈለገ ይሁኑ የሚል የሚያስመስል ስለሆነ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷን ወደ ቀደመ ክብሯ በመጠበቅና በማስጠበቅ ሰላሙን በማስፈን መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ዛሬም ደግመን እንጠይቃለን፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ ተፈጽሟል የተባለውን የፓትሪያርክና ‹‹የኤጲስ ቆጶሳት›› ሹመት ተከትሎ የተለያዩ አገረ ሰብከቶች ጽሕፈት ቤቶችን ጨምሮ የማኅበረ ቅዱሳን ጽሕፈት ቤት ድርጊቱን ባወጡት መግለጫ ማውገዛቸው ይታወሳል፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመናድና ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለመከፋፈል በማቀድ ‹‹26 መነኮሳትን ሾመናል›› በማለት መግለጫ አውጥተዋል ያላቸውን ‹‹የአቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ኤዎስጣቴዎስንና የአቡነ ዜና ማርቆስን›› በአዲስ አበባ የሚገኘውን ማረፊያ ቤት ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዳሸገ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከምክክርና ከድርድር ውጪ ምን ዓይነት አማራጭ ይኑረን?

በዘውዳለም መንገሻ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ነፃነትና ሰንሰለት

(ክፍል አንድ) በታደሰ ሻንቆ 1) ‹‹ውስጣዊ ሰንሰለቶች እንዳሉ ሁሉ ውጫዊ ሰንሰለቶችም...

ገበያውን ሊያረጋጉ የሚችሉ አዳዲስ መፍትሔዎችን ማምጣት ያስፈልጋል!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎንፌ (ዶ/ር) በሕዝብ...

አዲሱ የሕንፃ አዋጅ ‹ድርጅት ተኮር› ሳይሆን ‹ባለሙያ ተኮር› ተደርጎ መዘጋጀት አለበት የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር በቀድሞ የሕንፃ አዋጅ የነበረውን ‹‹ባለሙያ ተኮር››...