Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለሦስት ዓመታት የተቋረጠው የሠራተኛው ሻምፒዮና ዳግም ተመልሷል

ለሦስት ዓመታት የተቋረጠው የሠራተኛው ሻምፒዮና ዳግም ተመልሷል

ቀን:

በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በአንጋፋነት ከሚጠቀሱ ዓመታዊ የስፖርት መድረኮች አንዱ በሠራተኞች መካከል የሚካሄደው ውድድር ነው። በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አማካይነት በየዓመቱ በሦስት የተለያዩ መድረኮች የሚካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በርካታ ቁጥር ያላቸውን አሳትፎ ከፍተኛ ፉክክር እያስተናገደ ለዘመናት መዝለቅ ችሏል፡፡

ዓመታዊው መድረክ ያቀፈው የበጋ ወራት ውድድሮች፣ አገር አቀፍ የሠራተኞች ውድድርና ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን ጠብቆ የሚከናወነው (ሜይ ዴይ) ውድድርን ነው፡፡ በውድድሮቹ ላይ የተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸውን ሲያሳትፉ ከርመዋል፡፡

የሠራተኛው ስፖርታዊ መድረክ ጤናማ፣ ንቁና አምራች ዜጎችን ከመፍጠርና ሠራተኛው እርስ በርስ ከማቀራረብ አንፃር የጎላ ሚና እንዳለው የሚነገርለት ዓመታዊ ስፖርታዊ ውድድሩ፣ በመድረኩ የሚደረገው ፉክክር የበርካቶችን ቀልብ የሚገዛ ነው፡፡ ለዘመናት የዘለቀው ዓመታዊው የሠራተኞች ውድድር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከመጋቢት 2012 ዓ.ም. በኋላ ባለፉት ሦስት ዓመታት ሳይከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ለሦስት ዓመታት ተቋርጦ የቆየውና በኢሠማአኮ ከሚሰናዱ ውድድሮች አንዱ የሆነው የበጋ ወራት ውድድር ከጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በውድድሩ ላይ ከ40 በላይ የሠራተኛ ስፖርት ማኅበራት ተሳታፊ እንደሆኑ የኢሠማኮ የማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊና የስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፍሥሐ ጽዮን ቢያድግልኝ አስታውቀዋል፡፡

እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በሚዘልቀው ውድድር ላይ ከተለያዩ ማኅበራት የተውጣጡ 830 ወንዶችና 246 ሴቶች በድምሩ 1,076 በአሥር የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች እንደሚፎካከሩ ይጠበቃል።

በአካዴሚው የሚከናወነው የሠራተኞቹ ውድድር ላይ ሠራተኞችም እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበት፣ የሚዝናኑበት መድረክ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ተመልካቾችም በውድድር ሥፍራዎች በመገኘት ፉክክሮችን እንዲመለከቱ አቶ ፍሥሐ ጽዮን ጥሪ አስተላልፈዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር ያወጣውን ክልከላና መመሪያ ተከትሎ ውድድሮች ተቋርጠው ቢቆዩም፣ ሠራተኞች በያሉበት አካባቢ በማኅበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ ሲደረግ መቆየቱን አቶ ፍሥሐ ጽዮን ያብራራሉ፡፡

እንደሳቸው ማብራሪያ ከሆነ የኢሠማኮ ስፖርት ክፍል ለስፖርታዊ ውድድሮቹ የተለያዩ መመርያዎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በርካታ አሠልጣኞች ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ሲሠራ መቆየቱንም አስረድተዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር አሠልጣኞች ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከተለያዩ የስፖርት ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተለያዩ ሥልጠናዎችን ሲወስዱና ሠራተኞችን ማኅበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሲያሠሩ እንዲሁም ወረርሽኙን በስፖርት እንዲከላከሉ ሲያደርጉ መሰንበታቸው አቶ ፍሥሐ ጽዮን ጠቁመዋል፡፡

ኢሠማኮ ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ፣ ከአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ ከአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅትና ሌሎች ተቋማትም ጋር በቅርበት በርካታ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን እንዲሁም ገልጸዋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽን ከመከሰቱ አስቀድሞ ሲከናወኑ የነበሩት ስፖርታዊ ውድድሮች የበርካታ ተቋማት ሠራተኞች ሲያቀራርብ እንደነበረና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በተቋረጠበት መራራቅን መፍጠሩ ተገልጿል፡፡

በአንፃሩ የሠራተኛው ስፖርት መድረክ በወረርሽኙ ምክንያት ተቋርጦ በቆየበት ጊዜ አንድ አንድ ተቋማት የስፖርትን ተቋማዊና አገራዊ ፋይዳ በመረዳት ሠራተኞቻቸውን በተለያዩ አማራጭ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ  ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡

በዚህም መሠረት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተቋማዊና አገራዊ ፋይዳ እንዳለው በመረዳት ሌሎችም ተቋማት ተመሳሳይ ተግባሮች መከተል እንደሚገባቸው ጥሪ ቀርቧል፡፡

በዚህ ዘመን ሠራተኛው በስፖርት የሚያደርገው ተሳትፎ ለሚሠራበት ድርጅት ውጤታማነት የሚኖረውን አስተዋጽኦ የጎላ አንደሆነ አሠሪዎች እንደሚረዱት ይታመናል፡፡ በመሆኑም ስፖርቱ የሠራተኛውን አንድነትና ለጋራ ጉዳይ አብሮ የመቆም ባህሉን እንደሚያጠናክር ይነገራል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛው መካከልም ጥሩ ግንኙነት እንዲዳብር በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ለኢንዱስትሪ ሰላም መስፈን የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች ይገልጻሉ፡፡

‹‹ኢሠማኮ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ለሠራተኛው የራሴ የሚለው ስፖርታዊ ውድድሮችን ማዘጋጀት ነው። በዚህም የበጋ ወራት ውድድር፣ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን መታሰቢያ የሜይ ዴይ ውድድር እንዲሁም የአገር አቀፍ የሠራተኞች ውድድሮችን በስፖርት ኮሚቴው አማካይነት እንቅስቃሴ ያደርጋል፤›› በማለት አቶ ፍሥሐ ጽዮን ስለ ሠራተኛው ስፖርት እንቅስቃሴ ያብራራሉ፡፡

አንበሳ ከ1943 ዓ.ም. ጀምሮ በሠራተኛው ስፖርት በመሳተፍ በብሔራዊ ቡድኖች ጭምር መጫወት የቻሉ ስፖርተኞችን ማበርከቱ ይነገራል፡፡ ሆኖም በየጊዜው የድርጅቱ አመራሮች ሲቀያየሩ ለስፖርት ያላቸው ግንዛቤ ዝቅተኛ በመሆኑ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ላይ መቀዛቀዙ ይነገራል፡፡ ችግሩ አሁንም እንዳለ የሚያስረዱት የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የሠራተኛ ስፖርት ቡድን መሪ አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ፣ ችግር ቢኖርም ሠራተኛው የስፖርት ኮሚቴ ስላለው ለስፖርት ብሎ ከደመወዙ የሚያዋጣው ገንዘብ ስላለ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመጠኑም ቢሆን ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ያስረዳሉ፡፡

በአንፃሩ የሠራተኛው ለስፖርቱ ያለው ተነሳሽነት የሚደነቅ ሆኖ ድርጅቱ የተሻለ ውጤት ማምጣት የሚችለውና በሠራተኛው መካከል የበለጠ የመቀራረብ ልምድ የሚኖረው  የድርጅት አመራሮች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ሲችሉ እንደሆነ አቶ አብዱላዚዝ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የወጪ ንግድ ፖሊሲያችን አገርን የሚጠቅምና ሕገወጥነትን የሚነቅል ሆኖ እንደ አዲስ ሊቀረጽ ይገባል!

ኢትዮጵያ ያልተቋረጠ የውጭ ምንዛሪ ችግር ውስጥ እንድትገባ ካደረጓት የተለያዩ...

የኢትዮጵያ ከአጎአ የገበያ ዕድል መታገድ በኢንዱስትሪዎች ላይ ያስከተለው ጉዳት

የአሜሪካ መንግሥት እ.ኤ.አ. በ2000 መገባደጃ ላይ ያፀደቀው የአፍሪካ ዕድገትና...

የአብዮቱ ያልተዘጉ ዶሴዎች

‹ዳኛው ማነው› ሒሳዊ ንባብ - ሐሳብና ምክንያታዊነት በዚያ ትውልድ...