Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበፅኑ ሕሙማን ክፍል የተኙ ታካሚዎችን ለመታደግ ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

በፅኑ ሕሙማን ክፍል የተኙ ታካሚዎችን ለመታደግ ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ቀን:

በኢትዮጵያ በፅኑ ሕሙማን ክፍል የሚገኙ ታካሚዎች ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የካፕኖግራፊ መሣሪያዎችን ለሦስት የሕክምና ተቋሞችን ማቅረቡን ‹‹ስማይል ትሬን ላይፍ ቦክስ ሴፍ ሰርጀሪ አንስቴዥያ›› የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡

የላይፍ ቦክስና የስማይል ክሊኒክ ቡድን መሪ ትህትና ንጉሡ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በፅኑ ሕክምና ክፍል የተኙ ሕሙማን ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ከሚያስፈልጉ የሕክምና መሣሪያዎች መካከል የካፕኖግራፊ መሣሪያ አንዱ ነው፡፡

የከንፈርና የመንጋጋ መሰንጠቅ ችግር ገጥሟቸው በፅኑ የሕክምና ክፍል ውስጥ የሚገኙ አብዛኛው ሕሙማን ጥንቃቄ የተሟላበት ቀዶ ሕክምና እንደማይደረግላቸው፣ ለሕክምናው የሚሆነው መሣሪያ ዋጋ ከፍተኛ በመሆኑም በተለይ ባላደጉ አገሮች ችግሩ እንደሚጎላ አክለዋል፡፡

በዓለም ላይ የሚከናወኑ ቀዶ ሕክምናዎች በጥንቃቄ እንዲፈጸሙ ስማይል ትሬንና ላይፍ ቦክስ ድርጅቶች ለተለያዩ አገሮች መሣሪያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለከንፈርና ለመንጋጋ መሰንጠቅ ችግር የተጋለጡ ሕሙማንን ለመታደግ ሁለቱ ተቋሞች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑንም ትህትና (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

በተለያዩ አገሮች እየቀረበ ያለው የካፕኖግራፊ መሣሪያ ዋና ጥቅም ትቦ ገብቶላቸው የሰመመን መድኃኒት የተሰጣቸው ሕሙማን ወይም ደግሞ የሰመመን መድኃኒት ወስደው ሊታከሙ ያሰቡ ሕሙማን የራሳቸውን አየር መቆጣጠር ስለማይችሉ ከመጀመርያ ጀምሮ የሕክምና ሁኔታቸውን ለመቆጣጠር የሚረዳ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

መሣሪያው አንድ ሕመምተኛ ሕክምናውን በሚያገኝበት ወቅት 50 በመቶ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል፣ ይህ ግብዓት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

‹‹ስማይል ትሬን ላይፍ ቦክስ ሴፍ ሰርጀሪ አንስቴዥያ ኢንሼቲቭ›› ለአንዱ መሣሪያ 1,000 የአሜሪካ ዶላር ማውጣቱን፣ አንዱ መሣሪያም ከ100 በላይ ለሚሆኑ ሕሙማን አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ስድስት ካፕኖግራፊ መሣሪያዎች ለየካቲት 12፣ ለካዲስኮና ለዘንባባ ሆስፒታል በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸውን፣ ሆስፒታሎቹ በቅድሚያ የተመረጡበት ዋነኛ ምክንያትም የከንፈርና የመንጋጋ መሰንጠቅ የሕክምና ስለሚሰጡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የሕክምና መሣሪያ በተሰጣቸው ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ የዘርፉ ባለሙያዎች ሥልጠናዎች እየተሰጡ ነው፡፡ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለሚገኙ 50 ባለሙያዎችም ለሰባት ቀናት የሚቆይ ሥልጠና ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጀምሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...