Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከሥራ የተሰናበቱ 1,500 ሠራተኞች  ቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ

ከተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከሥራ የተሰናበቱ 1,500 ሠራተኞች  ቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ

ቀን:

  • ኢሠማኮ ጉዳዩን እየተከታተልኩ ነው ብሏል

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ 1,500 በላይ ሠራተኞች ከታኅሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ በመሰናበታቸው ከስምንት ሺሕ በላይ የሚሆኑ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ጨምሮ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

ከሥራ የተሰናበቱት ሠራተኞች ‹‹በአፋር ክልል ባህል መሠረት›› ከሁለት በላይ ሚስቶች ማግባት ስለሚፈቀድና ከሥራ የተባረሩት ሠራተኞች በርካታ የቤተሰብ አባል ስላላቸው ከ8,000 በላይ ሰዎች ችግር ላይ ወድቀዋል ሲሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

እንደ ሠራኞቹ ገለጻ ከሆነ፣ ፋብሪካው ከሥራ ገበታ ያባረራቸው ከሕግ አግባብ ውጪ መሆኑን ነው፡፡ ፋብሪካው ሠራተኞቹን ሳያወያይ ከሥራ እንዳሰናበታቸውና በኢትዮጵያ ካሉት የስኳር ፋብሪካ ኢንዱስትሪዎች በተለየ ላልተለመደ ውሳኔ  በመደረጋቸው ቅሬታ እንዳደረባቸው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት በፋብሪካው ውስጥ ሲሠሩ የነበሩ ሌሎች ሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ተደርጎላቸው እየሠሩ መሆኑን የጠቀሱት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ የሠራተኛ ማኅበሩም ሆነ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከሕግ አግባብ ውጪ ከሥራ አሰናብቶናል ብለዋል፡፡

ከሥራ በመባረራቸው የቤተሰብ አባሎቻቸውን ጨምሮ በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የገለጹት ሠራተኞቹ፣ ለሪፖርተር በላኩት መልዕክት፣ ‹‹በአሥር ስኳር ፋብሪካዎች ላይ ያልተሠራ በተንዳሆ ፋብሪካ ተሠርቷል፤›› ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ውሳኔው አካል ጉዳተኞችንና እርጉዝ ሴቶችን ጨምሮ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ከመሆኑም ባሻገር፣ የሠራተኛ ማኅበሩም ቢሆን ለውይይት እንዳልጋበዛቸው ሠራተኞቹ   አስረድተዋል፡፡

ሠራተኞች ከሥራ መሰናበታቸው የብዙ ሰዎችን ሕይወት ችግር ውስጥ ይከታል ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ የሚመለከተው አካል ማስተካከያ ካላደረገ ከሥራ የተባረሩት ሠራተኞችና የቤተሰብ አባሎቻቸው ጎዳና ለመውጣት እንደሚገደዱ ተናግረዋል፡፡

መሥራት እየተቻለ፣ ውኃ እያለ፣ ገንዘብ እያለ ሠራተኞችን ከሥራ አሰናብቶ ለችግር መዳረግ ደግሞ ከአንድ ተቋም የሚጠበቅ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ለመንግሥት ኩራቱ ሕዝቡ ነው፡፡ ሕዝቡን ሜዳ ላይ መጣል ተገቢ ስላልሆነ የሚዲያ ተቋማት ችግራችንን በመዘገብ መንግሥት ደግሞ መፍትሔ በመስጠት ሠራተኛውን ሊታደግ ይገባል፤›› ሲሉ በመልዕክታቸው አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በበኩሉ፣ ውሳኔው ከሕግ አግባብ ውጪ መሆኑን አለመሆኑን እየተከታተለ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ሠራተኞቹ በቀጥታ ለማኅበሩ ቅሬታቸውን እንዳቀረቡና ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን፣ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በተንዳሆ ፋብሪካ የሚገኘው የሠራተኞች ማኅበር ከሥራ የተሰናበቱትን ሠራተኞች ሳያወያያቸው ምደባ መደረጉ አግባብነት የሌለው መሆኑን ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ለኢሠማኮ ማስታወቃቸውን አስረድተዋል፡፡

በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የሚገኙ ሠራተኞች ምደባውን በሕግ ሥርዓት እንደፈጸሙትና እንዳልፈጸሙት አረጋግጦ፣ ከሕግ አግባብ ውጪ ሆኖ ከተገኘ ለሠራተኞቹ ተገቢ ድርድር ይደረግላቸዋል፡፡

የእርሻ ሠራተኛ ማኅበራት ፌዴሬሽንን የተፈጠረውን ቅሬታ በተመለከተ እንደሚያነጋግሩም አቶ ካሳሁን ጠቁመዋል፡፡

ድርጅቱ ሠራተኞቹን የመቅጠር መብት ቢኖረውም፣ በሕግ አግባብ መሆኑና አለመሆኑ ግን መጣራት አለበት ብለዋል፡፡

ሠራተኛ ሲቀነስና ቀሪው በሥራ ገበታ ላይ ሲቆይ የሕግ አግባብ አለው ያሉት አቶ ካሳሁን፣ ጉዳዩን ተከታትለው ውሳኔ ላይ እንደሚደርስ ገልጸዋል፡፡

ከሥራ የተባረሩት ሠራተኞች ያቀረቡትን ቅሬታ መሠረት በማድረግ ጉዳዩን ማረጋገጥ እንዳለባቸው፣ ድርጊቱ ከሕግ አግባብ ውጪ ሆኖ ከተገኘ የሠራተኞቹን ቅሬታ ለሚመለከተው አካል እንደሚቀርብ የተናገሩት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሕዝብ ግንኙነት ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ አቶ ረታ ደመቀ፣ በሕጉ መሠረት የሁለት ወራት የሕግ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ግን ገልጸዋል፡፡ ተቋሙ ለሰባት ዓመታት 24 ሚሊዮን ብር ነፃ ክፍያ ሲፈጽም መቆየቱንም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...