Thursday, February 29, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በቲማቲም ድልህና ሶስ ምርቶች ላይ የሚጣለው የጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ ከፍ እንዲል ተደረገ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽን ታኅሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ የታሪፍ ምጣኔያቸው ከ35 በመቶ ወደ 15 በመቶ ዝቅ ተደርገው የነበሩት የቲማቲም ድልህና ሌሎች የቲማቲም ሶስ ምርቶች፣ የሚጣልባቸው የጉምሩም ቀረጥ ምጣኔ በድጋሚ ከፍ እንዲል መደረጉን ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ለኮሚሽኑ በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ፡፡

ሪፖርተር የተመለከተውና የገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ሙላይ ወልዱ ለጉምሩክ ኮሚሽን በተመራው ደብዳቤ እንደተገለጸው፣ ባለፈው ወር በተጠቀሰው የምርት ዓይነት ላይ የተደረገውን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያ ጠቅሶ፣ ይሁንና በታሪፍ ቁጥር 2103.2000 ላይ የሚመደበውን የቲማቲም ድልህና ሌሎች የቲማቲም ሶስ የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች በአገር ውስጥ በመኖራቸው ከለላ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ መገኙቱን አስታውቋል፡፡

ስለሆነም የገንዘብ ሚኒስቴር ዳግም ባደረገው የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያ፣ የቲማቲም ድልህና ሌሎች የቲማቲም ሶስ ዓይነቶች ላይ በኪሎ ግራም የሚጣለውን የጉምሩክ ቀረጥ ልክ ዳግም ወደ 35 በመቶ ከፍ እንዲል መወሰኑን ተገልጿል፡፡

የጉምሩም ኮሚሽን በበኩሉ የቀረጥ ማሻሻያ ውሳኔውን ተከትሎ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ለሚፈጸምባቸው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በሙሉ በጻፈው ደብዳቤ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ውሳኔውን ተፈጻሚ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ በዋለው የታሪፍ ማሻሻያ ሳጥን ውስጥ በታሪፍ ቁጥር 2103.2000 ላይ የተዘረዘሩት የቲማቲም ድልህና ሌሎች የቲማቲም ሶስ ምርቶች በተመሳሳይ አንቀፅ 21.03 ስር በታሪፍ ቁጥር 2103.1000 እንደተመደቡት የሶያ ሶስ ምርቶች በኪሎ ግራም 35 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ልክ ተጥሎባቸው እንደነበረ ይታወቃል፡፡

ሆኖም የገንዘብ ሚኒስቴር ታኅሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገር ውስጥ ያሉ አምራቾችና ገጣጣሚዎች ይበልጥ ተወዳዳሪ በመሆን ገቢ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን በሚል በተወሰኑ ግብዓቶችና ምርቶች ላይ ማሻሻያ ካደረገባቸው ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ የቲማቲም ድልህና ሌሎች የቲማቲም ሶስ ምርቶች ይገኙበታል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች