Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምደቡብ ኮሪያ የዘንድሮ አጀንዳ ያደረገችው ከሰሜን ኮሪያ የመዋሃድ ዕቅድ

ደቡብ ኮሪያ የዘንድሮ አጀንዳ ያደረገችው ከሰሜን ኮሪያ የመዋሃድ ዕቅድ

ቀን:

የኮሪያውያን አለመግባባት የሚመዘዘው ጃፓን እ.ኤ.አ. በ1910 የኮሪያ ባህረ ሰላጤን ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ ብላ ከያዘችበት ጊዜ አንስቶ ነው፡፡ ለአምስት ዓመታት ያህል የተካሄደው ሁለተኛው ዓለም ጦርነት በ1945 እስካበቃበት ጊዜ ድረስ ተከፋፍሎ የቆየው ቀጣናው በ1948 ነበር ሁለት መንግሥት ሆኖ ብቅ ያለው፡፡

ይህም አንድ የነበረውን የኮሪያ ሕዝብ ወደ ጦርነት ያስገባ ተቃርኖ ፈጥሯል፡፡ ልዩነቱና መገፋፋቱ ኮሪያውያን ከ1950 እስከ 1953 ጦርነት ውስጥ እንዲገቡም ምክንያት ነበር፡፡

በሰላም ስምምነት ሳይሆን በተኩስ አቁም ስምምነት በ1953 የተቋጨው የሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት ደግሞ ዛሬም ድረስ በአገሮቹ መካከል ውጥረት እንዲነግስ አድርጓል፡፡ ሁለቱም አገሮች የኮሪያን ባህረ ሰላጤና ደሴቶች ጠቅልሎ ከመግዛት ፍላጎታቸው ባለፈም ደቡብ ኮሪያ ከአሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ መወገናቸው አገሮቹ ወደ ሰላም እንዳይመጡ አንድ ምክንያት ሆኗል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አገሮቹ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ኢመደበኛ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከወታደራዊ ውጥረቱ ለመውጣት፣ ሰላማዊ ግንኙነት ለመፍጠርና ሕዝቡን መልሶ ለማዋሃድ ያስችላሉ የተባሉ ግንኙነቶችንም  አድርገዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙን ጂ ኢን ኮሪያ ከተከፋፈለች ከ55 ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ. በ2000 ሰሜን ኮሪያን መጎብኘታቸው ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ሰላማዊ ያደርጋል ያለችውን ‹‹ሰንሻይን ፖሊሲ›› ማውጣቷ፣ ጉብኝቱ በቀጣዩ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት እ.ኤ.አ. 2007 መደገሙም ተስፋ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ ኋላ ላይ ግንኙነቱ ዳግም መሻከሩ የሁለቱ አገሮች ግንኙነትን በቃላት ጦርነት የተሞላ አድርጎታል፡፡

በ2018 በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈረመው ‹‹ፖንሙንጀም ዲክላሬሽን ፎር ፒስ፣ ፕሮስፐሪቲ ዩኒፊኬሽን ኦፍ ኮሪያን ፔንስዌላ›› ለአገሮቹ ተስፋን የጣለ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ሰሜን ኮሪያ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የጦር መሣሪያ ሙከራዎችን እያደረገች ነው ተብላ በደቡብ ኮሪያም ሆነ በአሜሪካ ስትወነጀል ብትከርምም፣ ከሰሞኑ ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ሰላማዊ ለማድረግና ለመዋሃድ እንደምትሠራ አስታውቃለች፡፡

ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ለመፍጠር በዚህ ዓመት እንደምትሠራ ያስታወቀችውም በተገባደደው ሳምንት ነው፡፡

የደቡብ ኮሪያ ዩኒፊኬሽን ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ደቡብ ኮሪያ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለውን ግንኙነት መደበኛና ሰላም የሰፈነበት ለማድረግ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ለማድረግ የምትሠራ ይሆናል፡፡

ከሰሜን ኮሪያ ጋር ሰላማዊ ሰዎችን መቀያየርን ጨምሮ የተለያዩ ሰላማዊ ግንኙነቶችን ማድረግም የደቡብ ኮሪያ የ2023 ዋና አጀንዳ ነው፡፡

እንደ ሴኡል ሪዩኒፊኬሽን ሚኒስቴር፣ የሁለቱን ኮሪያዎች የውስጥ ጉዳዮች የሚዳሰሱት ሰባት የፖሊሲ ጉዳዮችን ዓላማ አድርጎ ሲሆን፣ ይህም ከሰሜን ኮሪያ ጋር ጠንካራና ሰላማዊ ግንኙነት ለመፍጠርና የሁለቱን ኮሪያዎች መዋሃድ ለማፋጠን የሚበጁ መሠረታዊ ሥራዎችን ለመሥራት ያግዛል፡፡

ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ የሚቃጣባትን ፀብ ማነሳሳት በሴኡልና ዋሽንግተን ጥምረት ወደ ትብብር ለመቀየር እንደሚሠራም የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ መንግሥት ዘንድሮ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ተቋርጦ የነበረውን ውይይት ዳግም ለመጀመር ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል ብሏል፡፡

ዩንሃፕ ኒውስ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው፣ ዓመቱ ደቡብ ኮሪያ በሰሜን ኮሪያ የሚቃጣባትን ወታደራዊ ትንኮሳ በሁለቱ አገሮች መካከል መተማመን በመፍጠር የምትቀይርበትም ይሆናል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ዩኒፊኬሽን ሚኒስትር ዎን ያንግ እንዳሉትም፣ ደቡብ ኮሪያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በማኅበራዊ፣ በባህላዊና በሰብዓዊ ድጋፎች ዘርፍ ከሰሜን ኮሪያ ጋ አቋርጠው የነበረውን ግንኙነት እንዲቀጥሉ ይሠራል፡፡

ሰሜን ኮሪያ የምግብ ዕርዳታም ሆነ ሌሎች ሰብዓዊ ድጋፎችን የምትፈልግ ከሆነ ደቡብ ኮሪያ ድጋፎቹን ለማድረግ ፈቃደኛ ናትም ብለዋል፡፡

ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ መንገዶችን በመጠቀምም በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል የሻከረውን ግንኙነት ለማርገብ የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ዕቅድ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡

በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ዳግም ውይይት ከተጀመረ ቀዳሚ አጀንዳ ይሆናሉ የተባሉትም ኮሪያውያንን ለመከፋፈል ካበቃቸው እ.ኤ.አ. ከ1950 እስከ 1953 በተካሄደው የኮሪያ ጦርነት ውስጥ የተለያዩ ቤተሰቦችን ማገናኘትና ከደቡብ ኮሪያ በሰሜን ኮሪያ በታሰሩ ዜጎች ዙሪያ መወያየት ይገኙበታል፡፡

ሁለቱን ኮሪያዎች ለማዋሃድም ‹‹ኒው ፊውቸር ኢንሽየቲቭ ኢን ዩኒፊኬሽን›› የሚል የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ለማዘጋጀት በደቡብ ኮሪያ በኩል መታቀዱ ተገልጿል፡፡

ደቡብ ኮሪያ ይዛ ለመጣችው አዲስ እይታ ዘንድሮ ባለሙያዎችና ማኅበረሰቡ ሐሳብ እንዲሰጡበት ካደረገች በኋላ ወደ ጠረጴዛ እንደምታመጣውም ታውቋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ አሁን ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ባትሰጥም፣ እ.ኤ.አ. በ1972 የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኪም ኢንግ ቀድሞም ይነሳ የነበረውን ብሔራዊ ውህደት ዕውን ለማድረግ ማንም ጣልቃ መግባት የለበትም፣ ሁለቱ አገሮች በማንም ላይ አይመረኮዙም፣ የውህደቱን አካሄድ ሁለቱ ኮሪያዎች ብቻ ማከናወን አለባቸው የሚል ምክረ ሐሳብ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...