Wednesday, March 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበለንደን ማራቶን በታሪክ በ2፡02 ውስጥ የሮጡ የሦስት ኢትዮጵያውያንና የኬንያዊ ፉክክር ይጠበቃል

በለንደን ማራቶን በታሪክ በ2፡02 ውስጥ የሮጡ የሦስት ኢትዮጵያውያንና የኬንያዊ ፉክክር ይጠበቃል

ቀን:

  • ሻምፒዮኗ ያለምዘርፍ ከኬንያዊቷ የዓለም ባለክብረ ወሰን ጋር እንዲሁ ይጠበቃል

በመጪው ሚያዝያ በሚካሄደው የ2023 የለንደን ማራቶን የወንዶች ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2፡02 ሰዓት ውስጥ የሮጡ ሦስት ኢትዮጵያውያን ቀነኒሳ በቀለ፣ ብርሃኑ ለገሰና ሞስነት ገረመው፣ ኬንያዊው ኬልቪን ኪፕቱም የሚፎካከሩበት ድንቅ አጋጣሚ ይሆናል ሲል የዓለም አትሌቲክስ ገልጿል።

የዓለም አትሌቲክስ የፕላቲነም ደረጃ በሰጠው የጎዳና ላይ ውድድር ላይ እንደሚሳተፍ ያረጋገጠው ቀነኒሳ፣ ከዚህ ቀደም የገባበት 2፡01፡41 ሁለተኛ የዓለም ፈጣኑ ሰዓት ነው፡፡ የእሱ ተከታይ የሆነው ኬንያዊው የ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን አሸናፊው ኬልቪን ኪፕቱም  የማራቶን ውድድር (2፡01፡53) ማስመዝገቡ ይታወቃል፡፡

በለንደን ማራቶን በታሪክ በ2፡02 ውስጥ የሮጡ የሦስት ኢትዮጵያውያንና የኬንያዊ ፉክክር ይጠበቃል | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊዎች ብርሃኑ ለገሰ (2፡02፡48) እና ሞስነት ገረመው (2፡02፡55) ያስመዘገቡ መሆናቸው የዘንድሮውን የለንደን ማራቶን በልዩነት ያስቀምጠዋል፡፡

በተጨማሪም የዓምናው ሻምፒዮን ኬንያዊው አሞስ ኪፕሩቶ፣ የዓለም ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ (2:03:39)፣ የበርካታ የዓለምና የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ሞ ፋራህና የሁለት ጊዜ የኒውዮርክ ማራቶን አሸናፊ ጄፍሪ ካምዎሮር ጋር በለንደኑ ማራቶን እንደሚወዳደሩም ታውቋል፡፡።ዓምና በኦሪገን የዓለም ሻምፒዮናን ያሸነፈውና በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው የ31 ዓመቱ ታምራት ቶላ፣ እ.ኤ.አ. በ2021 የአምስተርዳም ማራቶንን ያሸነፈና በ2022 የቶኪዮ ማራቶን የሦስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም ባለፈው ዓመት 2ኛ የወጣው ኢትዮጵያዊው ልዑል ገብረሥላሴ (2:04:02) ሌላው ተጠቃሽ አትሌት ነው፡፡ ከምርጥ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት ክንዴ አጥናው (2:03:51)፣ ሰይፉ ቱራ (2:04:29) ናቸው፡፡በተያያዘ ዜና፣ በዘንድሮው የለንደን ማራቶን በሴቶች ምድብ የዓምናዋ አሸናፊና የአለም የ10 ኪሎ ሜትር ሪከርድ ባለቤት ኢትዮጵያዊቷ ያለምዘርፍ የኋላው፣ የዓለም ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤቷ ኬንያዊቷ ብርጊድ ኮስጌና የኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ ፔሬስ ጄፕቺርቺር ጋር የሚደረገው ፉክክር ተጠባቂ አድርጎታል፡፡  በማራቶን የሩጫ ታሪክ ከዋክብት የሚወዳደሩበት የዘንድሮው የለንደን ማራቶን፣ የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮኗ አልማዝ አያና፣ ገንዘቤ ዲባባ እንዲሁም በማራቶን የመጀመሪያ ውድድርዋን የምታካሂደዋን የኦሊምፒክ 5,000 ሜ እና 10,000 ሜ. አሸናፊዋ ሲፋን ሀሰን የውድድሩ አካል መሆናቸውን የዓለም አትሌቲክስ ዘግቧል፡፡‹‹ባለፈው ዓመት የተቀዳጀሁትን የለንደን ማራቶን ድል መቼም ቢሆን የማልረሳው ቀን ነው፤›› ያለችው ያለምዘርፍ፣ ‹‹ወደ ለንደን ለመመለስና የዚህ አስደናቂ ውድድር አካል ለመሆን በጣም ጓጉቻለሁ፤›› ስትልም አክላለች፡፡አልማዝ አያና እና ገንዘቤ ዲባባ በ2022 በአምስተርዳም የማራቶን ውድድር ያደረጉ ሲሆን፣ የ2016 የኦሊምፒክ የ10,000 ሜ. ሻምፒዮን የሆነችው አልማዝ 2፡17፡20 በሆነ የቦታው ሪከርድ ስታሸንፍ፣ የዓለም የ1,500ሜ ሪከርድ ባለቤት ገንዘቤ ዲባባ በ2፡18፡05 ሁለተኛ መውጣቷ ይታወሳል፡፡ ዓምና በበርሊን ማራቶን 2፡15፡37 በሆነ ውጤት ያሸነፈችውና በማራቶን በታሪክ አምስተኛው ፈጣን ሯጯ ኢትዮጵያዊት ትዕግሥት አሰፋም በውድድሩ ተጠባቂ ናት፡፡በ2019 የዓለምን የ1,500 ሜ እና የ10,000 ሜ አሸናፊ የነበረችውና ለመጀመርያ ጊዜ ማራቶንን የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን፣ በ2018 በአውሮፓ የግማሽ ማራቶን 1፡05፡15 የፈጸመች ሲሆን በተከታታይም ተወዳድራለች።እንደ የዓለም አትሌቲክስ ዘገባ፣ በአጠቃላይ በ2023 የለንደን ሴቶች ማራቶን ከሚወዳደሩት አምስቱ በ2፡18፣ አሥሩ በ2፡19 የሮጡ ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ ግንባር ቀደምቱ ኢትዮጵያውያቱ ትዕግሥት አሰፋ (2:15:37)፣ አልማዝ አያና (2:17:20)፣ ያለምዘርፍ የኋላው (2:17:23)፣ ገንዘቤ ዲባባ (2:18:05)፣ ሱቱሜ አሰፋ (2:18:12)፣ ዓለም መገርቱ (2:18:32) ናቸው፡፡በዓለም አትሌቲክስ ዋና ዋና የማራቶን ውድድሮች የሚካሄድባቸው ተብለው የተቀመጡት ስድስቱ ከተሞች ለንደን፣ ቶኪዮ፣ ቦስተን፣ በርሊን፣ ቺካጎና ኒውዮርክ ናቸው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...