Wednesday, March 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት በ188 ሺሕ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ ዕርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

መንግሥት በ188 ሺሕ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ ዕርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

ቀን:

  • የወጪ ንግድ ገቢ አሽቆልቁሏል

ባለፉት ስድስት ወራት በሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ተሰማርተዋል ባላቸው 188 ሺሕ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ መወሰዱን፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነቱን በሚያባብሱ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ በየደረጃው በተዋቀረ የዋጋ ማረጋጋትና የሕገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ኃይል በተከናወነ ሥራ፣ በሕግ ከተፈቀደላቸው ተግባር ውጪ ተሰማርተው ከተገኙ ነጋዴዎች ውስጥ የተወሰኑት የንግድ ፈቀዳቸው መሰረዙንና የቀሩት ደግሞ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሆነ የተናገሩት፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ ናቸው፡፡

ሚኒስትሩ የተቋማቸውን የ2015 ዓ.ም. የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ፣ በፍርድ ቤት ከተፈረደባቸው ነጋዴዎች መካከል 27 ሚሊዮን ብር መገኘቱን አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል በሕገወጥ መንገድ ሸቀጦችን ሲያዘዋውሩ ከነበሩ ግለሰቦች ሸቀጦቹ ተወርሰው፣ 271 ሚሊዮን ብር ለመንግሥት ገቢ መደረጉን አክለው ገልጸዋል፡፡

በስድስት ወራት ውስጥ በመንግሥትና በፍራንኮ ቫሉታ አሠራር 47.9 ሚሊዮን ሊትር ዘይት፣ 4.5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር፣ 2.4 ሚሊዮን ኩንታል ሩዝ ከውጭ ገበያዎች ተገዝቶ ወደ አገር ቤት መግባቱ ተገልጿል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስተ ወራት የወጪ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል የታየበት መሆኑን፣ በዕቅድ ለማሳካት ተይዞ ከነበረው 2.29 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ማሳካት የተቻለው 1.75 ቢሊዮን ዶላር ብቻ እንደሆነ፣ ይህ አፈጻጸም፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ6.9 በመቶ ወይም በ131.9 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱ ሪፖርት ተደርጓል፡፡

ለወጪ ንግድ ገቢ መቀነስ እንደ ዋነኛ ምክንያት ተብሎ በሚኒስትሩ የተጠቀሰው ኮንትሮባንድ፣ ሕገወጥ ንግድ፣ የዓለም የምርት ፍላጎትና የዋጋ መቀዛቀዝ፣ በተለይም ከዋጋ አንፃር ቡና ላይ የተፈጠረ የዋጋ ማሽቆልቆል፣ ማሾ በሜትሪክ ቶን 1,700 ዶላር ይሸጥ ከነበረበት ወደ 1,250 መውረዱ ነው፡፡

  የተገኘው የኤክስፖርት ውጤት ከኮንትሮባንድ አዘዋዋሪዎች ጋር በግብግብና ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቆ በመሠራቱ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ናቸው፡፡

አቶ ካሳሁን አክለውም ሚኒስቴሩ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመግታትና ለመቆጣጠር ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከፌዴራል ፖለስ ጋር በመተባበር ሰፊ ሥራ ባይሠራ ኖሮ፣ አሁን የተገኘው ገቢ ላይታስብና ለግምገማ የሚቀርብ ነገር ላይገኝ ይችል እንደነበር አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...