- Advertisement -

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ለፋይናንስ ተቋማት አመራሮች አሳወቁ።

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በኋላ የፋይናንስ ተቋማትን የሚቆጣጠሩበት መንገድ ዓለም አቀፍ መሥፈርትን በተከተለ መመዘኛ እንደሚሆን ገልጸዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ ይህንን ያስታወቁት ከፋይናንስ ተቋማት የሥራ መሪዎች ጋር ባለፈው ረቡዕ ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በተዘጋጀ የትውውቅና የምክክር ፕሮግራም ላይ ነው፡፡ 

በእሳቸው አመራር ዘመን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትኩረት የሚያደርግባቸው ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸው፣ በተለይ የተረጋጋ ውጭ ምንዛሪ ገበያን ማስፈን ቀዳሚ የትኩረት ጉዳያቸው እንደሚሆን ገልጸዋል።

- Advertisement -

‹‹እንደ ብሔራዊ ባንክ የእኛ ትልቁ ትኩረታችን የሚሆነው የተረጋጋ የዋጋ፣ ውጭ ምንዛሪ ተመን ማስፈን፣ እንዲሁም ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት መፍጠር ይሆናል፤›› ያሉት አዲሱ ገዥ፣ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ማስፈን ትልቁ የትኩረት እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የፋይናንስ ሥርዓቱ ጤናማ፣ የተረጋጋና ተደራሽ ለማድረግ የሚሠሩ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

እነዚህ ሦስት ጉዳዮች የብሔራዊ ባንክ የትኩረት አቅጣጫዎች ስለመሆናቸው አጽንኦት ሰጥተው የገለጹት አቶ ማሞ፣ ‹‹እኔ እዚህ የመጣሁት ይህንን ሥራ ለመሥራት ነው፣ ትኩረቴም ይህ ነው፤›› በማለት ቀዳሚ አድርገዋለሁ ያሉትን ተግባራት ዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ብሔራዊ ባንክ በተቋቋመበት አዋጅ የተሰጠው ኃላፊነትም ይኼው በመሆኑ ኢኮኖሚ ዕድገትን ለማስቀጠል መሠረታዊ የሆነውን የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጡት ትልቁ አጀንዳ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡  

ከዚህ በኋላ ተግባራዊ የሚደረገው የገንዘብ ፖሊሲም ቢሆን አጠቃላይ የዋጋ ንረቱን እንዳያባብስ በተቻለ መጠን ጥረት የሚደረግበት እንደሚሆን፣ እንዲሁም ባንኮች የሚከተሉት የብድር ፖሊሲ አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚውን የሚደግፍና የግል ዘርፉን የሚያበረታታ እንዲሆን የሚሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ዋነኛ አጀንዳ ብለው ከገለጹት የትኩረት አቅጣጫዎች ባሻገር ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ፖሊሲው የውጭ ንግድን የሚያበረታታ፣ እንዲሁም ገቢ ምርቶችን ለመተካት የሚያግዝ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡ ‹‹የውጭ ምንዛሪ ክምችት በተገቢው ደረጃ ላይ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ በሰፊው የሚሠራ ይሆናል፤›› ያሉት አቶ ማሞ፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ከፍ ለማድረግ ብዙ ውይይቶችን ከባንኮች ጋር እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ከፍ ለማድረግ የተለያዩ መንገዶች ያሉት በመሆኑ፣ እንደ ብሔራዊ ባንክ ትኩረት ተደርጎበት የሚሠራበት ሥራ እንደሚሆን ከሰጡት ማብራሪያ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በአንድ ጊዜ ማሳካት እንደማይቻልና ሥራው ጊዜ የሚወስድ መሆኑን እንደሚረዱ፣ ነገር ግን በትብብር መንፈስ በጋራ በመሥራት የማክሮ ኢኮኖሚው የተረጋጋና ለዕድገት አመቺ ለማድረግ እንደሚሠሩ አመልክተዋል፡፡ 

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት ለሚታየው ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት የፊሲካል አስተዳደር ላይ ያለው ጉድለት መሠረታዊ ምክንያት መሆኑን አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አመልክተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በጀት ጉድለት አስተዳደር አንዱና ብሔራዊ ባንኩን ሥራ ላይ ከፍተኛ ደረጃ ተፅዕኖ ያሳደረ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህንን ለማስተካከል መንግሥት ብዙ ዕርምጃዎቸን እየወሰደ ሲሆን፣ ይህም በገቢና በወጪዎች ላይ የሚወሰዱ ዕርምጃዎችን ያካትታል ብለዋል፡፡ የታክስ ሥርዓቱን ለማሻሻልና ዲጂታላይዝ ለማድረግ፣ አስተዳደሩን ለማሻሻል፣ አዳዲስ የታክስ ምንጮችን ለመፍጠር ዕርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልጸው የተወሰኑትን በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ ለአብነት ከጠቀሷቸው መካከል አንዱ የንብረት ታክስን ተግባራዊ ለማድረግ የተወሰደው ዕርምጃ ይገኝበታል። በሌላ በኩል ወጪዎችን ለመቀነስና ለመቆጣጠር የድጎማ ሥርዓትን ከብክነት ነፃ ለማድረግ እየተወሰዱ ያሉ ዕርምጃዎች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ በፊት በምግብ ዘይት፣ በስኳርና በስንዴ አቅርቦት ላይ ሲደረጉ የነበሩ ድጎማዎች እንዲቀሩ መደረጉን፣ ይህም የፊሲካል አስተዳደሮችን ጠንካራ እንዲሆን ለማስቻል የተወሰደ ዕርምጃ እንደሆነ አውስተዋል፡፡ 

‹‹ነዳጅን በሒደት ከድጎማ እያወጣነው ነው፡፡ ይህም ወጪን ለመቆጣጠርና የፊሲካል አስተዳደራችንን ጠንካራ እንዲሆን ለማስቻል፣ በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚው የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ የተሠራ ነው፤›› ያሉት አቶ ማሞ፣ ጎን ለጎን ደግሞ ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣውን የውጭ ዕዳ ለመቀነስ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሻሻል የዕዳ ሽግሽግ ውይይት ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሰው፣ አሁንም የሁለትዮሽና የባለበዙ ወገን ውይይቶችን በማስፋፋትና በማጠናከር የአገሪቱን የውጭ ዕዳ ለማራዘምና ለማሸጋሸግ ሰፊ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡ የውጭ ዕዳ ጫናን የመቀነስ ሥራ አሁን እያጋጠመ ያለ አንደኛው መሠረታዊ ችግር መሆኑንም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ ሌላው ትልቁ ችግርና ማኅበረሰብን ያማረረው ጉዳይ የዋጋ ንረት በመሆኑ፣ ይህንንም ለመቀነስ እንደሚሠሩ አመልክተዋል። በ2015 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት በምግብ ነክ ምርት ላይ ያለው የዋጋ ንረት ከሰኔ 2014 ዓ.ም. ጋር ሲወዳደር ከ38 በመቶ፣ ወደ 32 በመቶ መውረዱን አስታውሰዋል፡፡ በአንፃሩ ከምግብ ነክ ምርት ውጪ ያሉ ምርቶች ግን በስድስት በመቶ ማደጉን ጠቁመዋል፡፡ በአጠቃላይ የዋጋ ንረቱ ባይባባስም መሠረታዊ በሆነ መልኩ ቀንሷል ለማለት ስለሚያስቸግር የዋጋ ንረትን መግታትና የዋጋ መረጋጋትን ማስፈን ትልቁ የቤት ሥራ እንደሚሆን ገልጸዋል።

በዚህ ውይይት መድረክ ላይ አቶ ማሞ ባንኮችን ከመቆጣጠር አኳያ በብሔራዊ ባንክ ይተገበራሉ ያሏቸውን ነጥቦችም አንስተዋል። 

‹‹ባንኮችና ለሌሎች የፋይናንስ ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ መመዘኛዎች መሠረት ሥራቸውን እየሠሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው፤›› በማለት ሥጋትን መሠረት ካደረገ ቁጥጥር ባለፈ ጠንካራ የሆነ የቁጥጥርና የክትትል ሥራ እንደሚኖር ጠቁመዋል፡፡ 

የፋይናንስ ተቋማትን የመቆጣጠርና የመከታተል ሥራን በተመለከተ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ የሆኑት አቶ ሰለሞን ደስታ በሰጡት ማብራሪያ፣ ባንኩ በቴክኖሎጂ በመታገዝ አሠራሩን እንደሚያዘምን ገልጸዋል።

 

በተለይ የባንክ ዘርፈ ለውጭ ኩባንያዎችም ክፍት ስለሚሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋይናንስ ዘርፉ ቁጥጥርና ክትትል ሥራ ጠበቅ እንደሚል የተናገሩት አቶ ሰለሞን፣ ይህ ቁጥጥር በቴክኖሎጂ የታገዘ ጭምር እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ 

ሕግን ከማስከበር አኳያ ሌሎች በርካታ ሥራዎች እንደሚሠሩ የጠቆሙት አቶ ሰለሞን፣ ‹‹ሕግን አክብሮ አለመሥራት ባንኮች ዘንድ ይሰማል፣ ነገር ግን ባንኮች የሕግ ጥሰት ውስጥ የሚገቡት ሆን ብለው ነው ወይስ ከአቅማቸው በላይ ሆኖ ነው የሚለውን በደንብ ለይተን ሕግ ማስከበሩ ላይ ወገባችንን አስረን እንሠራለን፤›› ብለዋል።

በተለይ ሆነ ብለው ሕግ የሚተላለፉት ላይ ጠበቅ ያለ ዕርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ መቀመጡንና ብሔራዊ ባንክም በዚህ ላይ ጠበቅ ያለ ዕርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል፡፡ 

‹‹ከዚህ በኋላ ዝም ብለን የምናልፈው ነገር የለም፤›› የሚሉት ምክትል ገዥው፣ በተለይ አንድ የሚሰጥ ብድር ለተባለው ዓላማ መዋል አለመዋሉን ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡ ይህን ጉዳይ ብሔራዊ ባንክ ከሩቅ ሆኖ ሳይሆን፣ የባንኮቹ ቦርድ፣ ሥራ አስፈጻሚና ማኔጅመንቱ በኃላፊነት መንፈስ መሥራት የሚኖርባቸው ይሆናል፡፡ ብድርን በቅርበት ተከታትለው ለተባለው ዓላማ መዋል አለመዋሉን ማረጋገጥ ካልቻሉ ግን በቦርዱም፣ በማኔጅመንቱና በሠራተኛው ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።

ሕግን ከማስከበር አኳያ ከዚህ በኋላ ከሕገ መንግሥቱ ጀምሮ የወጡ ሕጎችንና መመርያዎችን፣ እንዲሁም የንግድ ሕጉንና የብሔራዊ ባንክ መመርያን ተከትለው መሥራት አለመሥራታቸውን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚሠራም ጠቅሰዋል፡፡  

 

ብሔራዊ ባንክ በቀጣይ የክትትልና ቁጥጥር ሥራውን ከባንኮች ጠቅላላ ጉባዔ ጀምሮ፣ ቦርድ አባላትና በሥራ አስፈጻሚዎች ላይ ጭምር እንደሚያደርግ በመጠቆም፣ ባንኮች ነፃና ገለልተኛ የሆነ ቦርድ እንዲያቋቁሙ እንደሚደረግ ፍንጭ ሰጥተዋል። 

በሕግ ጥሰት ለሚፈጠር ችግር ከዚህ ቀደም የነበሩ የቅጣት መጠኖች የሚከለሱበት ሁኔታም ሊፈጠር እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ሰለሞን፣ ለምሳሌ ከዚህ ቀደም በአስተዳደራዊ ቅጣት አሥር ሺሕ ብር የሚያስቀጣ ጉዳይ የነበረ ሲሆን፣ ይህ የገንዘብ መጠን አሁን ካለው የብር የመግዛት አቅምና ምን ያህል አስተማሪ ነው? የሚለው ነገርም ሊታይ ይችላል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እንዲህ ያሉ ቅጣቶችን ማነው የሚከፍለው የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ በመሆኑ፣ ይህም አሠራር የሚፈተሽ ስለመሆኑ ከአቶ ሰለሞን ማብራሪያ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፋይናንስ ተቋማት በሚሊዮን ብር የሚቆጠር ቅጣት የሚቀጡ ሲሆን፣ ይህ ቅጣት ግን የሚከፈለው ከተቋሙ ካዝና በመሆኑ ይህ ሊለወጥ ይገባል ብለዋል፡፡   

የሚጣሉ ቅጣቶችን ከሕዝብ ገንዘብ እየዘገኑ መከፈል ተገቢ ባለመሆኑ፣ ወደፊት በቀጥታ ጥፋት ፈጻሚ ሆኖ የተገኘ የሥራ ኃላፊ በግሉ የሚቀጣበት ሁኔታ እንደሚፈጠርና በቀጣይ የብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር እንደሚጠብቅ አስታውቀዋል፡፡ 

አቶ ማሞ በዚህ የምክክር መድረክ ላይ በአንዳንድ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይም ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በተለይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን የተመለከተው ይገኝበታል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትንበያ በተያዘው 2015 ዓ.ም. ዓመት ኢኮኖሚ በ7.3 በመቶ ያድጋል ተብሎ የሚታመን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ዕድገት የተመዘገበ ሲሆን፣ በዚህ ዕይታ የፋይናንስ ዘርፉ የባንክ ዘርፉ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው አስታውሰዋል፡፡ የፋይናንስ ተቋማቱ አድርገዋል ብለው ከገለጹት ውስጥ፣ በ2015 ዓ.ም. የመጀመርያው ግማሽ ዓመት የባንክ ዘርፉ የገዛው የግምጃ ቤት ሰነድ 157 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን እንደ ምሳሌ አንስተዋል፡፡ የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት የፋይናንስ ዘርፉ አስተዋጽኦ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም አክለዋል፡፡ 

ባንኮች የሰጡት አዲስ ብድር ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ119 በመቶ ማደጉን በማስታወስም ይህ ዕድገት አስገራሚ የሚባል መሆኑንና ነገር ግን ይህ ዕድገት ብዙ አንድምታ እንዳለው ገልጸዋል። ባንኮች የ2015 የግማሽ ዓመት የብድር መጠናቸው በዚህን ያህል ሊያድግ የቻለው የብድር ገደብ በመነሳቱ፣ በመጠባበቂያ ገንዘብ (ሪዘርፍ ሪኳይሬመንት) ምጣኔ ከአሥር በመቶ ወደ ሰባት በመቶ መቀነሱና አዳዲስ ባንኮች ወደ ኢንዱስትሪው መቀላቀላቸው አዲስ የተሰጠው የብድር መጠን በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።

ሌላው በአኃዝ አስደግፈው የገለጹት ጉዳይ ከባንክ ውጪ ያለው የገንዘብ መጠን መጨመሩን ነው፡፡ ከባንክ ውጪ ያለው ገንዘብ ከአምናው ጋር ሲወዳደር በ27 በመቶ በማደግ በአሁኑ ወቅት ከ189 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ ይህ የሚያሳየው ባንኮች ተጨማሪ ሀብት ለማሰባሰብ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ነው ብለዋል፡፡ ስለዚህ ብዙ ገንዘብ በአሁኑ ሰዓት በሰው እጅ ስላለ ባንኮች ተቀማጭ ገንዘብን በማሰባሰብ ረገድ ብዙ ለመሥራት የሚያስችል አቅም እንዳለ ጠቁመዋል፡፡ 

- Advertisement -

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን

ከ ተመሳሳይ አምዶች

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ያለፉትን ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የተመለከተ ማብራሪያ...

የፋይናንስ ተቋማት ከመደበኛ ወጪያቸው ሁለት በመቶውን በትክክል ለአቅም ግንባታ እያዋሉ አለመሆኑ ተነገረ

የፋይናንስ ተቋማት ከዓመታዊ መደበኛ ወጪያቸው ሁለት በመቶ የሚሆነውን ለሥልጠናና ለአቅም ግንባታ እንዲያውሉ ቢገደዱም፣ ብዙዎቹ ይህንን ግዴታ በአግባቡ እየተወጡ አለመሆኑ ተገለጸ፡፡ ከፋይናንስ ተቋማት የአስተዳደር ውጪ ሁለት...

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መገልገል ላልቻሉ አርሶ አደሮች ዲጂታል የግብርና ኪዮስኮች ሊከፈቱ ነው

ዘመናዊ የስልክ ቀፎና የኢንተርኔት አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች፣ የግብርና ኤክስቴንሽንና የምክር አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ዲጂታል የግብርና ኪዮስኮች እንደሚከፈቱ ተነገረ፡፡ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ...

ቡና ላኪዎች የኮንቴይነር እጥረት እንደገጠማቸው ተጠቆመ

ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች በማነሳቸው የቡና ላኪዎች፣ ከሌላው ጊዜ በተለየ የኮንቴይነር እጥረት እየገጠማቸው እንደሆነ ታወቀ፡፡ በኮቪድ-19 ወረርሽኝን ወቅት በተወሰነ ደረጃ ቡና ላኪዎች የኮንቴይነር እጥረት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል ባንኮች ቁጥር ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ ከዜሮ ተነስቶ ዛሬ ላይ 29 መድረሱ አንዱ ነው፡፡...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ ኃላፊነት ኃላፊነት ተሰጥቶት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በመጀመሪያው ምዕራፍ ውጥኑ ሰባት ሺሕ ኪሎ ሜትር...

አዳዲስ ጽሁፎች

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ አባላቱ የተከበሩ ተብለው የሚጠሩት በምክንያት አይደለም እንዴ? ትክክል ነው። ምክንያቱም፣ ምክር ቤቱ ትልቁ የሥልጣን አካል ነው፣...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል መንግሥታት አመራሮችን ይዘው የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ግፊቱ እየጨመረ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣ የእለት ጉርሳቸውን ምፅዋት ለማግኘት ለወጪ ወራጁ እጃቸውን በሚዘረጉ፣ ኑሮ ይሁን ወይም የዘመኑ ሁኔታ አቅላቸውን አሳጥቷቸው...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ያለፉትን ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የተመለከተ ማብራሪያ...

የተዘነጋው የከተሞች ሥራ የመፍጠር ተልዕኮ

በንጉሥ ወዳጅነው አሁን አሁን የአገራችን የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ አንገብጋቢና ሊታሰብበት የሚገባ አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡ ከዓመት ዓመት እየተጠራቀመ ከመጣው ተምሮ ቁጭ ካለ ኃይል አንፃር ብቻ...

ሆድና የሆድ ነገር

(ክፍል ስድስት) በጀማል ሙሐመድ ኃይሌ (ዶ/ር) አቶ ባል - "ለዛሬ ገንፎ"    ወ/ሮ ሚስት - "ለልክህ ድፎ" ዜናዎች ወይም በአጠቃላይ መረጃዎች በጋዜጣ ላይ ከመታተማቸው፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ከመሠራጨታቸው በፊት...

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን