የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕሮፌሰር)፣ ከኢፒድ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የተናገሩት፡፡ ለብዙ ሰው ኮሚሽኑ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ይመስለዋል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተጀመረው ሰላም እየተጠናከረ ከሄደ በትግራይ ክልልም ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ቤቶችን እንከፍታለን ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ኮሚሽኑን ለመቀበል አስቸጋሪ እንደነበር፣ በሒደት በተሠሩ ሥራዎች ከ53 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ከ40 በላይ ከሚሆኑት ጋር ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉም አክለዋል፡፡