በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ማለትም በኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በነባሩ ክልል ለመቀጠል ወይም በአዲስ ክልል ለመደራጀት የሚያስችል ውሳኔ ሕዝብ (ሪፈረንደም)፣ ኅብረተሰቡ ድምፅ ሲሰጥ ውሏል፡፡ በየድምፅ መስጫ ጣቢያዎቹ ጊዜያዊ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ፎቶዎቹ በየአካባቢው የነበረውን የውሳኔ ሕዝብ ገጽታን በከፊል ያሳያል፡፡
- ፎቶ መስፍን ሰሎሞን