የዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ የሰጠው የ2023 የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ባለፈው ረቡዕ በፖላንድ ቶሩን ከተማ ሲካሄድ፣ በአንድ ማይል ውድድር የዓለም 5000 ሜትር ሻምፒዮኗ ጉዳፍ ፀጋይ፣ ሁለተኛውን ፈጣን ደቂቃ (4:16.16) በማስመዝገብ አሸንፋለች፡፡ የመጀመርያው ፈጣን ጊዜ በገንዘቤ ዲባባ በዓለም ክብረ ወሰንነት የተያዘው ደቂቃ (4:13.31) ነው፡፡ ፎቶው ጉዳፍ ምርጥ ጊዜ በማስመዝገቧ እንኳን ደስ ያለሽ መባሏን ያሳያል፡፡
- ፎቶ፡ የዓለም አትሌቲክስ