Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊግጭት በነበሩባቸው አካባቢዎች የሚተገበረው የስምንት ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት

ግጭት በነበሩባቸው አካባቢዎች የሚተገበረው የስምንት ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት

ቀን:

በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ወድመዋል፡፡ ሰዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው መሠረተ ልማቶች ደግሞ የጤናው ዘርፍ አንዱ ነው፡፡

በጤና ሥርዓቱ ብሎም በጤና ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎም የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የጤና ተቋማቱን መልሶ የማቋቋምና ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው ለመመለስ እየሠራ ይገኛል፡፡

ከሥራዎቹም ውስጥ አንዱ የእናቶችንና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል መተግበር የጀመረው ፕሮጀክት ነው፡፡ ግጭቶች በነበሩባቸው አካባቢዎች የሚተገበረውና የእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት ለማሻሻል የሚያግዘው የስምንት ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ሲደረግ፣ በጤና ሚኒስቴር የእናቶች ሕፃናትና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ መሠረት ዘላለም (ዶ/ር) እንደተናገሩት የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ተቋማቱን ሙሉ ለሙሉ ወደነበሩበት የአገልግሎት ደረጃ ለመመለስ አሁንም ተጨማሪ ሥራዎች መሥራት ያስፈልጋል፡፡

ይህንንም ታሳቢ በማድረግ የሕፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕዝብ ፈንድ (ዩኤኤፍፒኤ) እንዲሁም የዓለም የጤና ድርጅት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በግጭቶች በተጎዱ ክልሎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግና የጤና አገልግሎቱን ሊያሻሽል የሚችል ፕሮጀክት መቅረፃቸውን አክለዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚውለው ስምንት ሚሊዮን ዶላር ከቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የተገኘ ሲሆን ድጋፉ ጉዳት በደረሰባቸው ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 12 ሆስፒታሎች፣ 24 ጤና ጣቢያዎች፣ 48 ጤና ኬላዎችና ስድስት ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድኖችን ለመደገፍና የሚውል ይሆናል፡፡

ለሴቶች፣ ወጣቶችና ሕፃናት የተቀናጀ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን ለመደገፍና ከግጭት በኋላ የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥልም በዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ፣ የእናቶች ሕፃናትና ሥነ ምግብ ኃላፊ ፖል ማይኑካ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

አያይዘውም የፕሮጀክቱ ዓላማ በኢትዮጵያ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የእናቶችና የሕፃናት ጤና አገልግሎትን፣ የጤና ሥርዓትንና ቅንጅታዊ አሠራርን መደገፍ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከኅዳር 2015 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም. ለ18 ወራት የሚተገበር መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...