Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየወሰን ማስከበር ሥራዎች የመንገድ ፕሮጀክቶች እያስተጓጎሉ ነው

የወሰን ማስከበር ሥራዎች የመንገድ ፕሮጀክቶች እያስተጓጎሉ ነው

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሰን ማስከበር ሥራዎች የመንገድ ግንባታን እያስተጓጎሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

ከመንገድ ግንባታ የወሰን ክልል ውስጥ በመሆናቸው መፍረስ የሚገባቸው ቤቶች፣ የመብራትና የቴሌ ምሰሶዎች የመንገድ ግንባታውን እያስተጓጎሉ መሆኑን፣ በመንገዶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እያሱ ሰለሞን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አቶ እያሱ ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ ባለሥልጣኑ በ2015 በጀት ዓመት ከመንገድ ግንባታ የወሰን ክልል ውስጥ የሚገኙ ከ4,550 የሚሆኑ ቤቶችን የመብራትና የቴሌ ምሰሶዎችን ለማስነሳት አቅዶ ነበር፡፡

ባለሥልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከመንገድ ግንባታ የወሰን ክልል ውስጥ 99 ቤቶችን፣ 43 የመብራትና 69 የቴሌ፣ በአጠቃላይ 1,535 የወሰን ማስከበር ሥራዎች ከሚመለከታቸው የክፍለ ከተማና የወረዳ ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ማስነሳት እንደቻለ አቶ እያሱ ገልጸዋል፡፡

ቀሪ 3,015 የሚሆኑ ከመንገድ ግንባታ ወሰን ክልል ውስጥ የሚገኙ ቤቶችና ምሰሶዎች የግንባታ ሥራውን እያጓተቱት መሆኑን ተገልጿል፡፡

በመርካቶ አካባቢ መሳለሚያ የሚኘው የመንገድ ግንባታ በወሰን ማስከበር ችግር ተስተጓጎሉ አፈጻጸሙ 16 በመቶ መሆኑንም አቶ እያሱ ገልጸዋል፡፡

በመርካቶ መሳለሚያ አካባቢ የሚገኝ የመንገድ መጓተት ትራንስፖርት አገልግሎት ፍሰቱን እያስተጓጎለው መሆኑንም፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የግንባታው መጓተት ለከፍተኛ ወጪ እየዳረጋቸው መሆኑን ሲገለጽ፣ በተለይም ምሽት አካባቢ ታክሲዎች ከታሪፍ እጥፍ በላይ (ለአብነትም የ10.00 ብሩን ታሪፍ 25.00 ብር፣ የ15.00 ብሩን ታሪፍ 30.00 ብር) እያስከፈሉ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚሠሩ የማሳለጫ መንገዶችም ከሌሎች ጋር ሲነፃፀሩ የጎላ ባይሆንም ከወሰን ማካለሉ ጋር በተገናኘ መስተጓጎል እያጋጠማቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን፣ በተለይ በውስጠኛው የቀለበት መንገድ ላይ ያለውን አጠቃላይ የትራፊክ ፍሰት ለማሻሻል በሦስት የመንገድ መገጣጠሚያዎች ላይ (በለቡ፣ በኢምፔሪያልና በቦሌ ሚካኤል መንገድ) የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ እየተገነባ እንደሚገኝና ከወሰን ማስከበር ጋር በተገናኘ እየተስጓጎሉ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ለቡ ላይ ያለው የማሳለጫ መንገድ በአጠቃላይ 1.3 ኪሎ ሜርት ርዝመት ከ40 እስከ 46 ሜትር የጎን ስፋት ያለው መሆኑን ጠቅሰው፣ የግንባታ ወጪው 543 ሚሊዮን ብር በላይ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የድልድይ ተሸካሚ ምሰሶች ግንባታ ተጠናቆ የዋናውን ድልድይ የማስቀመጥ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ እያሱ አክለው ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ወደ 55 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲሆን፣ የመንገዱን ግንባታ የሚያከናውነውም ‹‹ቻይና ፈርስት ሃይዌይ ኢንጂነሪንግ›› የተባለ ተቋራጭ ነው ብለዋል፡፡ ኢምፔሪያል አካባቢ ያለው የተሽከርካሪ ድልድይ በስታዲየም ኢንጂነሪነግ አማካሪ ድርጅት አማካይነትና በቻይና ፈርስት ሃይዌይ ኢንጂነሪነግ ተቋራጭነት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፣ መንገዱም በአጠቃላይ 1.8 ኪሎ ሜትር እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

መንገዱ እስከ 40 ሜትር የጎን ስፋት እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ በዚሁ መንገድ እየተገነባ ያለው የማሳለጫ መንገድ ደግሞ ወደ 300 ሜትር ቁመት እንዳለው ተብራርቷል፡፡

‹‹በአሁኑ ጊዜ በቀኝ በኩል ያለው የተሽከርካሪ ድልድይ ክፍል ለትራፊክ ክፍት ይሆናል፤›› ያሉት አቶ እያሱ፣ ለግራ በኩል ያለው በቅርቡ እንደሚከፈትና አጠቃላይ አፈጻጸሙ ከ62 በመቶ በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡ የኤምፔሪያል መንገድ ግንባታ አጠቃላይ በጀት ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ሌላው በቦሌ ሚካኤል አካባቢ የሚገኘው የማሳለጫ መንገድ ቀደም ብሎ ውል ከተገባለት በቦሌ አየር መንገድ የጉምሩክ አቅጣጫ የሚመጣ መንገድን ጨምሮ በአጠቃላይ ወደ 5.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ማሳለጫ እየተገነባ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ 600 ሜትሩ ተሸጋጋሪ ድልድይ የሚያርፍበት ቦታ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በአንድ በኩል ያለው ማሳለጫ ለትራፊክ ፍሰት እንዲሆን ቀሪ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ የወሰን ማስከበር ተግባራትን ግን ለመንገድ ግንባታ መስተጓጎል እየፈጠሩ መሆናቸውን ተመላክቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...