Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበተመረጡ ዘጠኝ ፖሊስ ጣቢያዎች ነፃ የሕግ አገልግሎት መስጠት ሊጀመር ነው

በተመረጡ ዘጠኝ ፖሊስ ጣቢያዎች ነፃ የሕግ አገልግሎት መስጠት ሊጀመር ነው

ቀን:

የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተባለ ድርጅት በፖሊስ ጣቢያዎች ነፃ የጥብቅና አገልግሎት እንደሚጀምር ገለጸ፡፡ ድርጅቱ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ነፃ የሕግ አገልግሎቱን በተመረጡ ፖሊስ ጣቢያዎች እንደሚጀምር ተናግሯል፡፡ በአዲስ አበባ፣ በአዳማና በሐዋሳ ከተሞች በያንዳንዳቸው በተመረጡ ሦስት በድምሩ በዘጠኝ የፖሊስ ጣቢያዎች በወንጀል ለተጠረጠሩ ሰዎች ነፃ የሕግ አገልግሎቱን እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

ሥራውን ለመጀመር ተከታታይ ዓውደ ጥናቶች መካሄዳቸውንና ለአራት ወራትም ቅድመ ዝግጅት ሲካሄድ መቆየቱን፣ የድርጅቱ ፕሮግራም አስተባባሪና የሕግ ባለሙያ አቶ በላቸው ግርማ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

‹‹ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች  አሉ፡፡ የእኛ ግን ከፖሊስ ጣቢያ መጀመሩ የተለየ ያደርገዋል፤›› ብለዋል፡፡

በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የፍትሕ ሒደት የሚጀምረው አንድ ሰው በወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ እጅ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ አንደሆነ ያስታወሱት አቶ በላቸው፣ ብዙዎች ከታች ጀምሮ የሕግ አገልግሎት በቅርበት ባለማግኘታቸው በፍትሕ አደባባይ ችግር እንደሚገጥማቸው ጠቅሰዋል፡፡

‹‹ተጠርጣሪዎች ገና ከመጀመሪያው ከፖሊስ ጋር ከሚያደርጉት ግንኙነት ጀምሮ የሚያማክራቸውና የሚወክላቸው የሕግ ባለሙያ ቢያገኙ፣ በፍርድ ሒደቱ ፍትሕና ርትዕ ያለው ውሳኔ ለማግኘት ትልቅ ዕገዛ ያደርግላቸዋል፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

በፈረንሣይ የልማት ድርጅት (AFD) ፈንድ የሚደገፈው በሦስት ከተሞች በዘጠኝ የፖሊስ ጣቢያዎች የሚጀመረው ነፃ የሕግ አገልግሎት፣ የሙከራ (ፓይለት) ፕሮጀክት መሆኑንና እየሰፋ እንደሚሄድ አቶ በላቸው ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ በዘጠኙ የፖሊስ ጣቢያዎችም በዓመት እስከ 2‚000 ለሚሆኑ የሕግ አገልግሎት ለሚፈልጉ ዜጎች ነፃ ጥብቅናና የሕግ ድጋፍ ለመስጠት መታቀዱንም አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...