Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበጥቃት የታጀበው አክራሪነት በአፍሪካ

በጥቃት የታጀበው አክራሪነት በአፍሪካ

ቀን:

በአፍሪካ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው በጥቃት የታጀበ አክራሪነት በድህነትና በመገለል ምክንያት የሚቀጣጠል መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ድህነትና መገለል በስፋት በሚስተዋሉባቸው በተለይ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ሃይማኖት የሚያሳድረው ተፅዕኖም እንደ ምክንያት ተነስቷል፡፡

ዩኤንዲፒ እንደሚለው፣ በጥቃት የታጀበ አክራሪነት ባብዛኛው መሠረተ ልማት ባልተሟላላቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ደሃ፣ ያልተማሩና ተገልለናል የሚሉ ማኅበረሰቦች የሚሳተፉበት ነው፡፡

ድርጅቱ በ2021 ‹‹ዘ ጆርኒ ቱ ኤክስትሪሚዝም ኢን አፍሪካ›› በሚል የሠራውን ዳሰሳ ሰሞኑን ይፋ ሲያደርግ እንዳስታወቀው፣ በጥቃት በታጀበ አክራሪነት ከሞቱት ውስጥ ግማሽ ያህሉ የተመዘገበው ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ነው፡፡

ቀድሞ በጥቃት ከሚያምኑ አክራሪ ቡድኖች የተውጣጡ 1,000 ሰዎችን ጨምሮ ለ2196 ሰዎች ቃለመጠይቅ በማድረግ በአፍሪካ ከሰሃራ በታች በሚገኙት ቡርኪናፋሶ፣ ካሜሩን፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ናይጄሪያ፣ ሶማሊያና ሱዳን የተጠናው ጥናት ሰዎች ጥቃት ወደ ተሞላትበት አክራሪነት የሚገቡበትን ምክንያት አስቀምጧል፡፡

ሥራ አጥነት

በአጠቃላይ በሚባል ደረጃ ለአፍሪካውያን ችግር ሆኖ ዘመናትን ያስቆጠረው ሥራ አጥነትና ሰዎች ወደአክራሪነት ገብተው ጥቃት እንዲፈጽሙ ምክንያት ከሆኑ ችግሮች ይመደባል፡፡  

በወንጀል ውስጥ እንዲሳተፉ ገፊ ምክንያቱም ሥራ አጥ መሆናቸውና በመንግሥት  ባለሥልጣናት ተገልለናል ስለሚሉ ነው፡፡

በመንግሥት አለማመናቸውና መንግሥት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች አለመርካት አክራሪ ቡድኖች ራሳቸውን እንደ መንግሥትና አማራጭ አገልግሎት አቅራቢ አድርገው እንዲቆጥሩም አድርጓል፡፡

ደሃዎችንና የተገለሉ ሰዎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግም ለአክራሪ ቡድኖች ምልመላ ዋና መሣሪያ ነው፡፡ በተለይ ወንዶች ጥቃት የሚፈጽሙ አክራሪ ቡድኖችን ከመቀላቀላቸው በፊት ትንሽ ገንዘብ የሚያገኙ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

መገለል፣ ከከተማ አካባቢ ርቆ መኖር፣ ከሌሎች ጋር ለመገናኘት ይሁን ሌሎችን ለማወቅ ዕድል አለማግኘት ሰዎች በኋላ ላይ አክራሪ ቡድኖችን እንዲቀላቀሉም ምክንያት ሆነው ተገኝተዋል፡፡

ጥቃት የሚፈጽሙ አክራሪ ቡድኖችን የተቀላቀሉት አብዛኞቹ በጣም በገጠራማና ከማዕከላዊ ሥፍራዎች ከራቁ አካባቢዎች የመጡ፣ ከድኅነት ወለል በታች የሚኖሩና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መገለል የደረሰባቸው ናቸው፡፡

ከሌሎች ጎሳዎችና እምነት ተከታዮች ጋር የመገናኘት ዕድላቸው አናሳ መሆኑም አክራሪ ቡድኖችን ለመቀላቀል ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡

በልጅነታቸው ደስተኛ ሳይሆኑ ያደጉ፣ በአስተዳደጋቸው ውስጥ የወላጆቻቸው ተሳትፎ አነስተኛ መሆን ጥቃት  ከሚፈጽሙ አክራሪ ቡድኖች ጋር እንዲቀላቀሉ አድርጓል፡፡

የዩኤንዲፒ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በጥቃት የታጀበ አክራሪነትን ለማለዘብ ሰዎች ወደቡድኖቹ እንዲቀላቀሉ ምክንያት በሆኑ ችግሮች ላይ መሥራት ያስፈልጋል፡፡

በአክራሪ ቡድኖች ውስጥ የሚሳተፉ አብዛኞቹ ሰዎች በልጅነታቸው የእኔነት ስሜት እንዲያርባቸውና ከሌሎች ጋር ተገናግኝተው እንዲኖሩ ዕድል ያላገኙ ናቸው፡፡ ቤተሰብና አካባቢ ለልጆች ዕድገት ወሳኝ ቢሆንም ይህንን የማግኘት ዕድል አልነበራቸውም፡፡

ሃይማኖት

በጥናቱ ከተሳተፉት 17 በመቶ ያህሉ በሃይማኖታቸው ምክንያት ወደአክራሪ ቡድኖች የተቀላቀሉ ስለመሆናቸው ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ትምህርት

በጉልበት ተገደው ካልሆነ በስተቀር የተማሩ ሰዎች አክራሪ ቡድኖችን መቀላቀል የማይፈልጉ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ ትምህርት በበጎ ፈቃድ አክራሪ ቡድኖችን ለመቀላቀል የሚፈልጉ ልጆችን በ13 በመቶ የሚቀንስ መሆኑም ታይቷል፡፡

አዲስ የሰላም አጀንዳ

በአክራሪ ቡድኖች ውስጥ በመሳተፍ ጥቃት የሚያደርሱ ቡድኖችን ለማስቆም መንግሥት የሚሰጠው ማበረታቻና ምሕረት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ዩኤንዲፒ ይገልጻል፡፡

ከተቀላቀሉበት አክራሪ ቡድን ያፈነገጡ ሰዎችም ከቡድኑ ለመልቀቅ የወሰኑት፣ የመንግሥት ማበረታቻና ምሕረት ጫና አሳድሮባቸው ነው፡፡

በመሆኑም በዩኤንዲፒ አዲስ የሰላም አጀንዳ እየቀረፀ ነው፡፡ ይህም ሰዎች ወደ አክራሪነት የሚገቡባቸውንና ግጭት እንዳይበርድ ምክንያት የሆኑ ችግሮችን መቆጣጠርና መቅረፍ ላይ ያተኩራል፡፡ ዩኤንዲፒ እንደሚለው፣ በጥቃት የታጀበ አክራሪነት በአንድ አገር ወይም ቀጣና ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በመሆኑም ችግሩን ሁሉም ተጋርቶ ለመፍትሔው በጋራ መሥራት አለበት፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...