Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየቤት ውስጥ ሩጫ ድምቀት የሆኑት ኢትዮጵያውያንና የዓለም ባለክብረ ወሰኑ ለሜቻ ግርማ

የቤት ውስጥ ሩጫ ድምቀት የሆኑት ኢትዮጵያውያንና የዓለም ባለክብረ ወሰኑ ለሜቻ ግርማ

ቀን:

በፈረንሣይ ሊቨን ከተማ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ለአራተኛ ጊዜ ድል ቀንቶታል፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታት በ3,000 ሜትር ውድድሮች ላይ መካፈል ችሏል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2020 ከአንድ እስከ ሦስት ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ አልቻለም ነበር፡፡ በአንፃሩ በ2021 7፡27፡98 በመግባት የምንጊዜም ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ቻለ፡፡

የ3,000 ሜትር መሰናክል የአንድ ጊዜ የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮና የብር ሚዳልያ ባለቤቱ ለሜቻ ግርማ፣ በአትሌቲክስ ታሪኩ ላይ ሁሌም ሊዘከርበት የሚችልበትን አዲስ ክብረ ወሰን በፈረንሣይ ሊቨን ከተማ አስመዝግቧል፡፡ 

ለሜቻ የወርቅ ደረጃ በተሰጠው የ3,000 ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 7፡23፡81 በማጠናቀቅ የዓለም ክብረ ወሰን መጨበጥ ችሏል፡፡ ገና በወጣትነት ዕድሜው በርካቶችን እያስደመመ የሚገኘው ለሜቻ፣ ስሙን በታሪክ መዝገቡ ውስጥ ሊተክል የሚያስችልበትን ውጤት በፈረንሣይ ማኖር ችሏል፡፡ 

አትሌቱ በኬንያዊ አትሌት ዳንኤል ኮመን ለ25 ዓመታት ተይዞ የነበረውን 7፡24፡90 ሰዓት በማሻሻል ነው ክብረ ወሰን መጨበጥ የቻለው፡፡ 

‹‹በውጤቱ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ በተለይ ለሦስት ቀናት ይህንን ክብረ ወሰን እንዴት መስበር እንደምችል ሳሰላስል ነበር፡፡ ወንድሜ ነው አሠልጣኜ፡፡ እንደማሳካው ስነግረው ነበር፤›› ሲል፣ ለሜቻ ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ 

ጥሩ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበረ ያስረዳው ለሜቻ፣ በስታዲየሙ የነበረውን የአየር ንብረት እንዲሁም የተመልካች ሁኔታ እንዳስደሰተው ገልጾ፣ ክብረ ወሰኑ ለረዥም ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡

የ2,000 ሜትሩን ርቀት ለማጋመስ 4፡58፡38 የወሰደበት አትሌቱ፣ ለሩብ ምዕት ዓመት በኬንያዊው ኮመን ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ከሁለት ሰከንዶች በላይ ማሻሻል ችሏል፡፡ 

በውድድሩ ላይ አትሌቶች በአሯሯጮች ሲታገዙ የነበረ ቢሆንም፣ በአንፃሩ የኢትዮጵያዊው ለሜቻ አሯሯጥ እጅግ ፈጣን በመሆኑ ሊያሯርጥ የገባው ሊቋቋመው እንዳልቻለ ተጠቅሷል፡፡

ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ የቻለው መሐመድ ካቲር 7፡24፡68 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ከማጠናቀቁም በላይ የርቀቱን ሁለተኛ የዓለም ፈጣን ሰዓት መያዝ ችሏል፡፡

ለሜቻ በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ 3 ሺሕ ሜትር መሰናክል 8፡10፡33 የብር ሜዳሊያ ማሳካት ሲችል፣ በኦሊምፒኩ ያሳየውን ድንቅ ብቃት በ2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ቤልግሬድ ሰርቢያ ላይ የብር ሜዳሊያ እንዲሁም በኦሪገኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ3,000 ሜትር መሠናክል ወጥ አቋም ይዞ እንዲጓዝ አስችሎታል፡፡ በዚህ ትራክ ላይ አትሌቶች ቁጥር በተመናመነበት ወቅት በቤት ውስጥ ሻምፒዮና ድምቀት መሆን የቻሉ የለሜቻን ዓይነት ድንቅ ብቃት የሚያሳዩ አትሌቶች እንዲጠበቁ አስችሏቸዋል፡፡

በመካከለኛ ርቀት ስኬታማ ጊዜን እያሳለፉ ከሚገኙ አትሌቶች መካከል አንደኛው የሆነው ለሜቻ፣ በ3,000 ሜትር መሠናክል ብሔራዊ ክብረ ወሰን ባለቤት ከመሆኑም ባሻገር፣ የዓለም የምንጊዜም 12 ምርጥ ሰዓት ባለቤቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

በሌላ በኩል ረቡዕ የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በሌላው የአውሮፓ አገር ፖላንድ በተከናወነ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 1,500 ሜትር ውድድር ላይ ጉዳፍ ፀጋይ ሌላ ታሪክ ያስመዘገበችበት ዕለት ነበር፡፡

የ26 ዓመቷ ጉዳፍ 1,500 ሜትር ርቀቱን 4፡16፡16 በማጠናቀቅ፣ የምንጊዜም የዓለም ሁለተኛውን ሰዓት መያዝ ችላለች፡፡

እ.ኤ.አ. በ2021 በሊቨን በተካሄው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ የ1,500 ሜትር ውድድርን 3፡53፡09 ያስመዘገበችው ጉዳፍ፣ በ2016 በገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል ግብ አድርጋ ነበር፡፡

የወርቅ ደረጃ በተሰጠው የፖላንድ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና  በ1,500 ሜትር ሒደት የሩጫው ፍጥነት እየቀነሰ ቢመጣም፣ ጉዳፍ 800 ሜትሩን በ2፡07፡21 ማጋመስ የቻለች ሲሆን፣ 1,200 ሜትሩን 3፡11፡26 ሮጣዋለች፡፡

‹‹የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር ሐሳብ ነበረኝ፡፡ ግን አትሌቲክስ እንደዚህ ነው፡፡ በልምምድ ወቅት ጥሩ አቋም ላይ ያለህ ሊመስልህ ይችላል፡፡ በአንፃሩ ውድድር ውስጥ ስትገባ የፈለከውን ማሳካት ላትችል ትችላህ፤›› ስትል፣ ጉዳፍ ከውድድር በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡

እንደ ጉዳፍ አስተያየት ከሆነ በቀጣይ ክብረ ወሰኑን በእጇ ማስገባቷ አይቀርም፡፡ 

በሌላው የወርቅ ደረጃ በተሰጠው የ2023 የፈረንሣይ፣ የ3,000 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው መግባት ችለዋል፡፡

ድሪቤ ወልተጂ የግሏ ምርጥ ሰዓት በሆነ 8፡34፡84 አንደኛ፣ ለምለም ኃይሉ 8፡38፡15 ሁለተኛ ደረጃ ሆና ስታጠናቅቅ፣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ሚዛን ዓለም ሦስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቅቃለች፡፡

በተለያዩ የአውሮፓና አሜሪካ  አገሮች ላይ የተካሄደው የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ቀጣይ ማረፊያውን በአሜሪካ ኒው ዮርክ ላይ ያደርጋል፡፡

በዙር በሚከናወኑት በእነዚህ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች በየዕርከኑ በሚወጣው ደረጃ አማካይነት ነጥብ እየተሰጣቸው ይወዳደራሉ፡፡ 

የትራክ አትሌቶች ወደ ጎዳና ውድድሮች ፊታቸውን እያዞሩ በመጡበት በዚህ ወቅት በቤት ውስጥ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ማግኘት ቀላል እንደማይሆን ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሲሰነዝሩ ይስተዋላል፡፡

በተለይ በኢትዮጵያ የትራክ ዕጦት ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ በመካከለኛ ርቀት ላይ ኢትዮጵያን ወክለው መሳተፍ የሚችሉ አትሌቶች ወደፊት ማግኘት አገዳጋች ሊሆን እንደሚችል ይነሳል፡፡

ምንም እንኳን የአትሌቲክስ አጀማመሩ ከአጭር፣ ከመካከለኛ፣ እንዲሁም ረዥም የሚከናወን ቢሆንም፣ በአንፃሩ የጎዳና ሩጫ ገንዘብ የሚያስገኝ መሆኑና በኢትዮጵያ የመሮጫ ትራክ ባለመኖሩ በመካከለኛ ርቀቱ ተስፋ ማድረግ የሚቻል እንዳልሆነ የሚጠቅሱም አሉ፡፡

ከዚህም ባሻገር በየዓመቱ የጎዳና ውድድሮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ፣ አትሌቶች ወደ ጎዳና ውድድሮች እየተሳቡ መምጣታቸው በትራክ ላይ የሚኖረውን ገጽታ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...