Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትታላቁ ሩጫ የዓለም ምርጥ የአሥር ኪሎ ሜትር ውድድር ተብሎ ዳግመኛ ተመረጠ

ታላቁ ሩጫ የዓለም ምርጥ የአሥር ኪሎ ሜትር ውድድር ተብሎ ዳግመኛ ተመረጠ

ቀን:

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚከናወኑ ዓመታዊ የጎዳና ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሥር ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ተመረጠ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁ የስፖርት ጋዜጦች አንዱ የሆነው ራነር ወርልድ (Runner World) ባወጣው መረጃ መሠረት፣ በዓለም ላይ ከሚከናወኑ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድሮች አንዱ የሆነው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በምርጥነት ተመርጧል፡፡

ጋዜጣው የኢትዮጵያን ውድድር አንደኛ አድርጎ ሲመርጥ የለንደኑን ቪታሊታ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ሁለተኛ፣ እንዲሁም የፓሪሱን 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ሦስተኛ በማድረግ መምረጡን ይፋ አድርጓል፡፡

የታላቁ ሩጫ ዓመታዊ ውድድር መከናወን ከጀመረ 22 ዓመታትን የተሻገረ ሲሆን፣ ደማቅ ሕዝባዊ ውድድር ከመሆኑም በላይ፣ ለበርካታ አትሌቶች የውድድር ዕድል በመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ መድረክ ደምቀው እንዲታዩ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት ችሏል፡፡

ከዚህም ባሻገር በየዓመቱ የተለያዩ ውድድር ዓይነቶችን እያበዛ፣ በርካታ የውድድር ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር፣ ማኅበረሰቡ ስፖርትን የዘወትር እንቅስቃሴው አንዱ አካል እንዲያደርግ የራሱን አሻራ ማኖር ችሏል፡፡

ከዚህም ባሻገር በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያሰናዳቸው ውድድሮች ባሻገር በተለያዩ የክልል ከተሞች ውድድሮችን እያከናወነ ይገኛል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...