ከአንድ መቶ ሠላሳ ዓመታት በላይ ያስቆጠረችው አዲስ አበባ፣ በምልክትነት በዘመን አሻራነት ልታስቀምጣቸው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግ የሚገባትን የድሮ ሕንፃዎች በየጊዜው አጥታለች፡፡ አንዱ ከሚያዝያ 27 አደባባይ (አራት ኪሎ) ወደ ፒያሳ በሚወስደው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንገድ፣ የቀድሞው 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ የነበረው ሕንፃ ነው፡፡ ጥንታዊው ቤት በ‹‹ልማት ስም›› እስከሚፈርስ ድረስ የዶርዜ ሃይዞ የሽመና ባለሙያዎች ይጠቀሙበት ነበር፡፡
– ፎቶ ሂስቶሪካል ፎቶስ ገጽ