Wednesday, March 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምተቃዋሚ ፓርቲዎች አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ የጠየቁበት የናይጄሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ የጠየቁበት የናይጄሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ

ቀን:

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ናይጄሪያውያን ለአዲስ ፕሬዚዳንትና ለብሔራዊ ሸንጎ ምክር ቤቶች ሕግ አውጪዎችን የመረጡት የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ነበር፡፡

ምርጫው በ36 ግዛቶችና በናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ የተካሄደ ሲሆን፣ ምርጫው የመራጮች ጣልቃ ገብነትና አስገዳጅነት ነበረበት የሚሉና ማስረጃ ያልቀረበበት ክስ እየተነሳበት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ለፕሬዚዳንትነት 18 ዕጩዎች የተወዳደሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ቀዳሚዎቹ የቀድሞ የሌጎስ ገዥ የነበሩት ቦላ ቲኑቡ፣ ከኦል ፕሮግረሲቭ ኮንግረስ (ኤሲፒ)፣ የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት አቲኩ አቡበከር ከፒፕልስ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ፒዲፒ) የቀድሞ የአናምብራ ገዥ ፒተር ኦቢ ከሌበር ፓርቲ (ኤልፒ) እንዲሁም የቀድሞ የናይጄሪያ መከላከያ ሚኒስትር ራቢዩ ኩዋንኩዋሶ ከኒው ናይጄሪያ ፒፕልስ ፓርቲ (ኤንኤንፒፒ) ናቸው፡፡

ሆኖም የምርጫው ውጤት ሙሉ ለሙሉ ባይገለጽም፣ ገዥው ፓርቲ እየመራ እንደሆነ በምርጫ ኮሚሽኑ መገለጹት ተከትሎ የናይጄሪያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረባቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

‹‹በምርጫ ኮሚሽን እየተገለጸ ያለው ውጤት በጣም የተሽሞነሞነና በእጅ አዙር የተያዘ›› ነው ሲሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ፒዲፒ፣ ኤልፒ እና አፍሪካን ዴሞክራቲክ ኮንግረስ በጋራ በሰጡት መግለጫም፣ በአቡጃ በሚኖረው የፓርቲዎች ጥምረት ላይ እንደማይሳትፉም ገልጸዋል፡፡

በምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሐመድ ያኩቡ ላይ የነበራቸው እምነት መሸርሸሩን በማከልም፣ ለኮሚሽኑ አዲስ ሊቀመንበር በመሾም ዳግም ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በየካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የተካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ‹‹ምርጫ ኮሚሽኑ የሰጠው መግለጫ ትክክል እንዳልሆነ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይመልከትልን›› ያሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የምርጫ ሒደቱ ግልጽነት እንደሚጎድለውና ውዝግብ የበዛበት እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የምርጫው ውጤት ሲገለጽ ከአዳራሹ ለቀው በመውጣት ውጤቱ ችግር የበዛበት እንደነበር የገለጹት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች ብቻ አልነበሩም፡፡ የአውሮፓ ኅብረትን ጨምሮ በርካታ ታዛቢዎችም ምርጫው ሕዝቡ እንደሚጠብቀው እንዳልነበርና ግልጽነት እንደሚጎድለው ተናግረዋል፡፡

የገዥው ፓርቲ ዕጩ ቦላ አህመድ ቲኑቡ እየመሩ መሆናቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ትላንት ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. አስታውቋል፡፡

ከ36 ግዛቶች 23ቱ ውጤት ያሳወቁ ሲሆን፣ ከገዥው ፓርቲ ቀጥሎ የተቃዋሚ ፓርቲው ፒዲፒ አቲኩ አቡበከር በሁለተኛነት እየተከተሉ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ በበኩላቸው ተዓማኒነት ከጎደላቸው ምርጫ ጣቢያዎች የመጡ ውጤቶች እንዲሰረዙ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ መንግሥት ግን ኦባሳንጆ አነሳሽ የሆኑ ደብዳቤዎችን ከመጻፍ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...