Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለቀጣዩ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ቀድመው መግባታቸውን ያረጋገጡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

ለቀጣዩ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ቀድመው መግባታቸውን ያረጋገጡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

ቀን:

በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የተለያዩ የሜዳሊያ ደረጃ ተሰጥቷቸው በአውሮፓና በአሜሪካ ከተሞች ላይ ውድድሮች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡

ከጥር ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በዙር የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ ደረጃ ተከፋፍሎ ሲከናወን የቆየው ሻምፒዮናው፣ አብዛኛው ውድድር ተካሄዶ የመጨረሻ ዙር ላይ ደርሷል፡፡ በተለያዩ አውሮፓ ከተሞች ላይ 53 የሜዳ ተግባርና የመካከለኛ ርቀት ውድደሮች የተከናወኑ ሲሆን፣ የዙር ውድደሩ ሊጠናቀቅ አንድ ዙር ቀርቶታል፡፡ 

ሊጠናቀቅ አንድ ውድድር የቀረው የቤት ውስጥ ሻምፒዮናው ቅዳሜ የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በበርሚንግሃም ከተማ የተከናወነ ሲሆን፣ ምርጥ ሰዓት የተመዘገቡበት  ሆኖ አልፏል፡፡

የቤት ውስጥ ሻምፒዮናው የመጨረሻ ውድድር መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. የብር ደረጃ የተሰጠው ማጠናቀቂያ ውድድር በፈረንሣይ ይካሄዳል፡፡

የወርቅ ደረጃ ከተሰጠው የ2023 የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የዙር ውድድር በኋላ፣ የዓለም አትሌቲክስ ከወዲሁ በ2024 በሚከናወነው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ላይ በቀጥታ ማለፍ የቻሉ 11 አትሌቶችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ 

ከእነዚህም መካከል ሰባት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ስም ይፋ ሆኗል፡፡ ባለፉት ውድድሮች ላይ በ800፣ 1,500 እንዲሁም በ3,000 ሜትር ርቀቶች ላይ መካፈል የቻሉ  ኢትዮጵያውያት አትሌቶች ከወዲሁ አንድ ዓመት ለቀረው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ መካፈላቸውን ማረጋገጥ ችለዋል፡፡

ይህም ማለት እ.ኤ.አ. 2024 ላይ በሚከናወነው የግላስኮ ዓለም ሻምፒዮና ዝግጅት ብሔራዊ ቡድኖች በርካታ አትሌቶችን ማሳተፍ ያስችላቸዋል፡፡ 

አብዛኛውን ጊዜ በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የቡድን ምርጫ እያንዳንዱ አገር ሁለት አትሌቶች ብቻ ማስመረጥ የሚችል ሲሆን፣ በግል ውድድሮች ላይ ተጨማሪ ተወዳዳሪ ዕድል  ማግኘት የቻሉ ብሔራዊ ቡድኖች ሦስተኛ አትሌት እንዲያወዳድሩ ያስችላቸዋል፡፡ በአንፃሩ ብሔራዊ ቡድንን የሚወክሉ የመጨረሻ አትሌቶች መለየት ሥልጣን ያለው ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ ይፋ ካደረጋቸው አትሌቶች መካከል በ3,000 ሜትር ሴቶች ለምለም ኃይሉ፣ ሚዛን ዓለም፣ ጉዳፍ ፀጋይ፣ ድርቤ ወልተጂ፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ እጅጋየሁ ታዬና ዳዊት ሥዩም ይገኙበታል፡፡

 በዚህም ምርጫ መሠረት ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በብሔራዊ ቡድን ከምታስመርጣቸው ሁለት አትሌቶች በተጨማሪ ሰባቱ አትሌቶች በቀጥታ ማለፍ የሚያስችላቸውን ዕድል አግኝተዋል፡፡ 

በበርኒግሃም በተካሄደው ሻምፒዮና ላይ በ3,000 ሜትር ርቀት ጉዳፍ ፀጋይ ድንቅ ብቃቷን ከማሳየትም ባሻገር፣ የዓለም ምርጡን ሁለተኛ ሰዓት ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ጉዳፍ ርቀቱን ለማጠናቅ የወሰደባት ጊዜ 8፡16፡60 ከገባችበት ለክብረ ወሰን ሰዓት የተቃረበ ነው፡፡ 

ዘጠኝ ማይክሮ ሰከንዶች ዘግይታ የገባችው ጉዳፍ የዓለም ምርጡን ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት በእጇ መጨበጥ ችላለች፡፡ 

የ5,000 ሜትር እንዲሁም 1,500 ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤቷ ጉዳፍ፣ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡

በመካከለኛ ርቀት በተለይ በቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ1,500 ሜትር፣ 3,000 ሜትር ውድድሮችን በበላይነት የምታጠናቅቀው ጉዳፍ ጥሩ አቋም ላይ ትገኛለች፡፡

ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ800 ሜትርና በ3,000 ሜትር ርቀቶች ኢትዮጵያን ትወክላለች፡፡ ፍሬወይኒ በቤት ውስጥ የተለያዩ ሻምፒዮናዎች ላይ መካፈል ችላለች፡፡

አትሌቷ በ2021 በ800 ሜትር ርቀት 1፡57፡57 የገባችበት፣ 1,500 ሜትር 3፡56፡28 ያጠናቀቀችበት፣ እንዲሁም በ2,000 ሜትር 5፡25፡86 ብሔራዊ ክብረ ወሰን ሰዓት ባለቤት ነች፡፡

ፍሬወይኒ በዘንድሮ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ጀርመን ከርልሰሩሄ ላይ በተከናወነ የ800 ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 2፡00፡46 የገባችበት ሰዓት በ2024 ግላስጎው 2024 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ በቀጥታ መሳተፍ አስችሏታል፡፡

በቅርቡ በመካከለኛው ርቀት ላይ እየደመቀች የመጣችው ድርቤ ወልተጂ አንደኛዋ ስትሆን፣ ፈረንሣይ ላይ በተከናወነው የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 3,000 ሜትር ርቀቱን 8፡33፡44 በመግባት በቀጥታ ወደ ዓለም ሻምፒዮና እንድትገባ አስችሏታል፡፡

ድርቤ በ800 ሜትር 1፡57፡02 እንዲሁም በ1,500 ሜትር 3፡56፡91 ያጠናቀቀችበት ምርጥ ሰዓቷ ነው፡፡

በ2024 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ ከሚካፈሉ አትሌቶች መካከል ሚዛን ዓለም፣ እጅጋየሁ ታዬና ዳዊት ሥዩም ይገኙበታል፡፡   

በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ግላስኮው 2024 በግላስኮው ከተማ ምክር ቤት ከስኮትላንድ መንግሥት፣ ኢቨንት ስኮትላንድ፣ ዩኬ ስፖርትና ዮኬ አትሌቲክስ ጋር በመተባር በግላስኮ ይካሄዳል፡፡ ግላስኮው እ.ኤ.አ. በ2019 የአውሮፓ አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በተሳካ ሁኔታ ማስተናገድ ችላለች፡፡ ይህም በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን እንድታሰናዳ ዕድል ፈጥሮላታል፡፡

በተጨማሪም የ2024 ሻምፒዮናዎች ለፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጊዜ ውስጥ የሚገቡበት ጊዜ በመሆኑና አትሌቶች ለዚህ አስፈላጊ ዓመት ዝግጅታቸውን ሲያጠናቅቁ ከ130 በላይ አገሮች የተውጣጡ እስከ 700 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...