Saturday, September 30, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የሞተር ሳይክል ትራንስፖርት አገልግሎት ሊጀመር ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • 2‚500 በላይ ሞተር ሳይክሎች ተዘጋጅተዋል

ዛይ ራይድ የትራስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ከአዲስ ሞተር ታክሲ ጋር ለመሥራት መስማማቱንና በዚህ ሥራም በዓመት እስከ 100 ሚሊዮን ብር ትርፍ ለማግኘት ማቀዱን ገለጸ፡፡

የዛይ ራይድ ድርጅት መሥራችና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በሞተር ሳይክሎች ዕቃ ለማድረስና ሰዎችን ለማጓጓዝ ከ2‚500 በላይ ሞተሮች አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡

ከዚህም የሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አገልግሎት ከአሥር እስከ 12 በመቶ የኮሚሽን ክፍያ እንደሚገኝና ይህንንም ዛይ ራይድና አዲስ ሞተር ታክሲ በእኩል እንደሚካፈሉት አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል፡፡

ተገልጋዮች ሞተር ሳይክሎችን ለመጓጓዝና ዕቃ ለማድረስ አገልግሎት ለማግኘት በዛይ ራይድ የጥሪ ማዕከል እንዲሁም በአዲስ ሞተር ሳይክል መተግበሪያ አማካይነት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ዛይ ራይድ በመኪና እየሰጠ ለሚገኘው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚጠይቀው መነሻ ክፍያ 94 ብር ሲሆን፣ በኪሎ ሜትር ደግሞ ከ13 እስከ 14 ብር እንደሚያስከፍል ገልጸዋል።

አዲስ ለሚጀምረው የሞተር ሳይክል ትራንስፖርት አገልግሎት ደግሞ መነሻው 70 ብር፣ በተጨማሪም በሜትር እስከ 12 ብር እንደሚከፈልበት አቶ ሀብታሙ አስረድተዋል፡፡

በሁለቱ የትራንስፖርት ሰጪ ድርጅቶች ስምምነት መሠረት ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ ከተሞች ላይ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በክልል ከተሞች በሞተር ሳይክል ትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይም ባህር ዳርና ሐዋሳ ከተሞች ላይ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ገልጸዋል፡፡

ለአምስት ዓመታት የሚቆየው ስምምነት ከድርጅቶቹ የጋራ ጥቅም በተጨማሪ ለአሽከርካሪዎች ተጨማሪ ክፍያ እንደሚያስገኝ ገልጸዋል፡፡

የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የኋላ ታሪካቸውን ከማጣራት ጀምሮ እስከ ምዝገባ ድረስ ያለውን የሚሠራው ‹‹አዲስ ሞተር ታክሲ›› መሆኑን፣ የአዲስ ሞተር ታክሲ መሥራችና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፉአድ አብደላ ተናግረዋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት አዲስ ሞተር በዛይ ራይድ መተግበሪያ ሥር ካሉት የመጓጓዣ አማራጮች አንዱ እንደሚሆን አቶ ፉአድ ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሠረት ሁሉቱም ድርጅቶች ከሚገኘው ከአሥር እስከ 12 በመቶ ኮሚሸን እኩል እንደሚካፈሉ አስረድተዋል፡፡ አምስት ዓመታት የሚዘልቀው ስምምነት በዘርፉ ያለውን የትራንስፖርት ችግር የትራፊክ ፍሰት ምክንያት መዘግየትን ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች