Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአደይ አበባ ስቴዲየምን ሲገነባ የቆየው የቻይና ተቋራጭ ፕሮጀክቱን አስረክቦ እንዲወጣ ታዘዘ

አደይ አበባ ስቴዲየምን ሲገነባ የቆየው የቻይና ተቋራጭ ፕሮጀክቱን አስረክቦ እንዲወጣ ታዘዘ

ቀን:

  • ግንባታውን ለማጠናቀቅ በወጣው ጨረታ የአውሮፓ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል

የአደይ አበባ ስቴዲየምን ተረክቦ ግንባታ ሲያከናውን የነበረው የቻይናው ኮንስትራክሽንና ዲዛይን ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን አስረክቦ እንዲወጣ መታዘዙ ተገለጸ፡፡ የቻይናው ተቋራጭ በውሉ መሠረት ክፍያዎች ለመፈጸም ቀሪ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነና በግንባታው ወቅት ተቋራጩ ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የግንባታ ማሽኖችን እንዲያወጣ መታዘዙ፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ፋሲሊቲ ዳይሬክተር አቶ አዝመራው ግዛው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

እንደ አዲስ ይፋ በሆነው ጨረታ የአውሮፓ ኩባንያዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ የቱርክና የጣሊያን ኩባንያዎች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በመንግሥት ከፍተኛ አካላት አማካይነት ውስን ጨረታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ የቻይናው ተቋራጭ ለሠራው ሥራ ተሰልቶ እንደሚከፈለው የተብራራ ሲሆን፣ በስምምነቱ መሠረት ተቋራጩ ሥራዎቹን በጊዜው ስላላጠናቀቀ፣ እንዲሁም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ክፍያው በጊዜ ባለመከፈሉ የሚያቀርበው ቅሬታ ባለመኖሩ፣ ውሉን ለማቋረጥ ስምምነት ላይ መደረሱን አቶ አዝመራው አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሠረት የቻይናው ኮንስትራክሽን ዲዛይን ኮርፖሬሽን የሚጠይቀው የክፍያ ገንዘብ እንደሌለና ይልቁንም ከዚህ ቀደም የገዛው ቁሳቁስ ካለ በጊዜው ዋጋ ክፍያ ተፈጽሞለት፣ ለቀጣይ ግንባታ ግብዓት እንዲውል ይደረጋል ሲሉ አቶ አዝመራው አክለዋል፡፡

‹‹የመጡ የግንባታ ቁሳቁሶቹ አሉ፡፡ ከዚህ ቀድም በተገዙበት የዋጋ ተመን  አማካይነት ለተቋራጩ ክፍያ እንዲፈጽም ይደረጋል፤›› በማለት አቶ አዝመራው ገልጸዋል፡፡

 ቀጣይ ጨረታውን የሚያሸንፈው ተቋራጭ በቻይናው ኮንስትራክሽንና ዲዛይን ኮርፖሬሽን ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን ያጠናቅቃል ተብሏል፡፡

በአንፃሩ በአገር ውስጥ የሚገኙ ተቋራጮች ሊሠሩ የሚችሉዋቸው ሥራዎች ለእነሱ እንደሚሰጡ፣ ነገር ግን ቴክኖሎጂ ነክ ሥራዎችን ጨረታውን የሚያሸንፈው የውጭ አገር ተቋራጭ ሙሉ በሙሉ የሚያከናውነው ይሆናል ተብሏል፡፡

ጨረታው በሒደት ላይ እንደሆነ የሚያስረዱት አቶ አዝመራው፣ ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ቀርበው እየተገመገሙ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ በአገር ውስጥ ከተሳተፉት ተጫራቾች መካከል ሌሎች የቻይና ተቋራጮች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡

በቅርቡ የቻይና ተቋራጭ ባቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ ላይ መግባባት ባለመቻሉ፣ ከተቋራጩ ጋር የተገባው ውል እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወሳል፡፡ የተገባው  ውል በቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ መሠረት የሥራ ወጪ ላይ 225 በመቶ የክፍያ ማስተካከያ በማድረግ 12.5 ቢሊዮን ብር ለመክፈል ስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስረድተው ነበር፡፡

ተቋራጩ ግን የተከፈለውና በመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፍ ውስጥ የሚገኙ ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን አንድ ላይ ለማከናወን ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲከፈለው ጥያቄ በማቅረቡ መስማማት ስላልተቻለ፣ በስምምት ውል ለማቋረጥ መወሰኑ አይዘነጋም፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...