የግብርና ምርምር መሪ ተመራማሪ አዱኛ ዋቅጅራ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ግብርና በአሠራሩም ሆነ ውጤት በማምጣቱ ረገድ የተፈለገውን ያህል አልሆነም ለማለታቸው መንስዔውን ሲገልጹ የተናገሩት፡፡ ከኢፕድ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት መሪ ተመራማሪው፣ የትምህርቱ ሥርዓት አገር በቀል ሳይሆን ከሌላ ተወስዶ ነው የተቀመጠው ብለዋል፡፡ የሚያስፈልው አገር በቀል ትምህርት፣ አገር በቀል ባህላዊ አስተዳደር ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ ለማደግ የራስን የግብርና አሠራር ዕውቅና ሰጥቶ መነሳት አለበትም ብለዋል፡፡