- Advertisement -

[ክቡር ሚኒስትሩ ተቋቋመ ስለተባለው የሽግግር መንግሥት ከአማካሪያቸው መረጃ እየጠየቁ ነው]

  • እኛ ሳንፈቅድ እንዴት ሊያቋቁሙ ቻሉ? ስምምነታችን እንደዚያ ነው እንዴ?
  • በስምምነታችን መሠረትማ እኛ ሳንፈቅድ መቋቋም አይችልም። የእኛ ተወካዮችም በአባልነት መካተት አለባቸው።
  • ታዲያ ምን እያደረገ ነው? ስምምነቱን መጣሳቸው ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር እነሱ እንደዚያ አላደርግንም፣ የፌዴራል መንግሥት ሳያጸድቀው የሽግግር መንግሥት አይመሠረትም እያሉ ነው።
  • ታዲያ ምንድነው የሠሩት?
  • ረቂቁን ነው የሠሩት።
  • ረቂቅ ምን?
  • ረቂቅ መንግሥት።

[ክቡር ሚኒስትሩ ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው የከተማ አስተዳደሩን ኃላፊ እየገመገሙ ነው]

  • ባለፈው በተገናኘንበት ወቅት የተለያዩ ማሳሰቢያዎችን ሰጥቼ ነበር።
  • አዎ። ትክልል ነው ክቡር ሚኒስትር
  • ለምሳሌ በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች በ90 ቀን መፈጸም የሚችሉ ፕሮጀክቶች ተለይተው እንዲተገበሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቼ ነበር።
  • አዎ።
  • እኮ ከምን ደረሰ?
  • በሁሉም የከተማው ክፍሎች ተጀምሯል። በተለይ በአዲሱ ክፍለ ከተማ አመቺ ቦታ በመኖሩ የተለያዩ የ90 ቀን ፕሮጀክቶችን እየተገበርን እንገኛለን።
  • ለምሳሌ ምን ተተገበረ?
  • የጓሮ አትክልቶችና መመገቢያ ማዕከላትን አጠናቀናል በተጨማሪም የከብት ዕርባታ ፕሮጀክት…
  • ከብት ዕርባታ በ90 ቀን?
  • ከብቶቹ በ90 ቀን እንደማይደርሱ የተረዳነው ፕሮጀክቱን ከጀመርን በኋላ ነው።
  • ስለዚህ ፕሮጀክቱ ታጠፈ?
  • አልታጠፈም። መፍትሔ አበጅተንለታል።
  • ምን አደረጋችሁ?
  • የደረሱ ከብቶችን ለይተን አስገብተናል።
  • ለምን የደረሱ?
  • ለመታለብ።
  • ማሳሰቢያ የሰጠሁት ግን ለአንድ ክፍለ ከተማ ብቻ አይደለም።
  • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር።
  • አመራሩ ቢሮ መዋልና በቪኤይት መንፈላሰስ ከዚህ በኋላ አይችልም። ፒክአፕ እየነዳ ፕሮጀክቶችን ይከታተል ብዬ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቼ እንዴት እስካሁን አይጀመርም?
  • በማሳሰቢያው መሠረት የከተማ አመራሩ ቪኤይት እንዳይነዳ ከልክለን ጎን ለጎን የጀመርነውን ጨረታ ሰሞኑን አጠናቀናል።
  • የምን ጨረታ?
  • የፒክ አፕ።
  • ምን?
  • አመራሩ ፒክ አፕ እየነዳ ፕሮጀክቶችን እንዲከታተል በሰጡት ማሳሰቢያ መሠረት የተፈጸመ ነው።
  • አመራርነት በቪኤይት መንፈላሰስ አይደለም ብል ፒክ አፕ ገዛችሁ?
  • በግልጽ እኮ ነው የገዛነው?
  • በግልጽ ማለት?
  • በግልጽ ጨረታ።
  • እሺ ሌላስ ምን ገዛችሁ?
  • አመራሩ ፒክ አፕ ቢመደብለትም ቢሮ መዋሉን ሊተው ባለመቻሉ ይህንን የሚያስቀር ግዥ እንዲፈጸም ወስነናል።
  • የምን ግዥ?
  • ለእያንዳንዱ አመራር በደረጃው ልክ ዘመናዊ ላፕቶፕና ሞባይል ስልክ እንዲገዛ።
  • ምን?
  • አዎ። ከዚህ በኋላ ቢሮ ለመዋል ምክንያት አይኖራቸውም። ባሉበት ሆነው በስልካቸው ወይም በላፕቶፕ መገልገል ይችላሉ።
  • እኔ ያልኩት ሕዝብ እንድታገለግሉና ቢያንስ የአቅመ ደካሞችን ቤት እንድታድሱ፣ እንድትጠግኑ እንጂ …
  • ክቡር ሚኒስትር ስለእሱም ተወያይተን ወስኔ አሳልፈናል።
  • ምን?
  • አመራሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ እንዲነሳሳ ይጠቅማል ያልነውን ወሳኔ አሳልፈናል።
  • ምን ወሰናችሁ?
  • ቤት ለሌለው አመራር ቤት እንዲሰጥ ቤት ላለው ደግሞ…
  • እሺ… ቤት ላለው ምን?
  • ቤቱን የሚያድስበት ወጪ በአስተዳደሩ እንዲሸፈን ወስነናል።
  • ወሰናችሁ?
  • አዎ። ከዚህ በኋላ የአቅመ ደካሞችን ቤት ላለማደስ ማቅማማት አይችሉም፣ ምክንያትም አይኖራቸውም።
  • እኔም ሳላቅማማ አድሰዋለሁ!
  • ምኑን?
  • ካቢኔውን!

[የከተማ አስተዳደሩ ኃላፊ ከስብሰባው ከወጡ በኋላ ወደ ሚኒስትሩ ስልክ ደወሉ]

  • ክቡር ሚኒስትር ቅድም የተናገሩት የምርዎትን እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ?
  • የሕዝብ ሀብት እየባከነ እንዴ እቀልዳለሁ?
  • ክቡር ሚኒስትር ሀብት እያባከንን አይደለም።
  • ታዲያ ሌላ ምን ሊባል ነው?
  • ቅድም ብቻዎትን ስላልነበሩ ተቆጥቤ እንጂ ምክንያቱ ሌላ ነው።
  • ሌላው ምክንያት ምንድነው?
  • ክቡር ሚኒስትር እኔ ፍርኃት አለኝ፣ ሥጋት አለኝ!
  • የምን ሥጋት?
  • አመራሩ ልቡ ሸፍቷል የት ቦታ እንደቆመ አይታወቅም። ይኼ አስፈርቶኛል።
  • ስለዚህ?
  • ሥጋት ስላለኝ ነው ፈጥኜ እስከ ወረዳ ያለውን አመራር በጥቅማ ጥቅም ለመያዝ የወሰንኩት።
  • እንደዚያ ነው?
  • አዎ። ፍርኃት ስላለኝ ነው። ሥጋት አለኝ።
  • እንደዚያ ከሆነ ገብቶታል ማለት ነው።
  • ምኑ?
  • ፕሮጀክቱ።
  • የቱ ፕሮጀክት?
  • የ90 ቀን!
- Advertisement -

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን

ከ ተመሳሳይ አምዶች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር? እርሶዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም። ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል፣ አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል። ይንገሩኝ...

[የባለሥልጣኑ ኃላፊ የቴሌኮም ኩባንያዎች የስልክ ቀፎ የመሸጥ ፈቃድ እንዳላቸው ለማረጋገጥ ክቡር ሚኒስትሩ ጋር ደወሉ]

ክቡር ሚኒስትር ዕርምጃ ከመውሰዳችን በፊት አንድ ነገር ለማጣራት ብዬ ነው የደወልኩት። እሺ ምንን በተመለከተ ነው? የቴሌኮም ኩባንያዎችን በተመለከተ ነው። የቴሌኮም ኩባንያዎች ምን? የቴሌኮም ኩባንያዎች የሞባይል ቀፎ እንዲሸጡ በሕግ...

[የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመመካከር በሚኒስትሩ ቢሮ ተገኝተው ውይይታቸውን ጀምረዋል]

ክቡር ሚኒስትር ባላንጣዎቻችን የእኛኑ ስልት መጠቀም የጀመሩ ይመስላል። እንዴት? ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? እስከዛሬ እኛ የምንሰጣቸውን አጀንዳ ተቀባይ ነበሩ። በዚህም በውስጣቸው ልዩነትንና አለመግባባትን መትከል ችለን ነበር። አሁን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ጠዋት ወደ ቢሯቸው ሲገቡ ጸሐፊያቸው ሰሞኑን በአባቶች መካከል ስለተደረገው ስምምነት ጠየቀቻቸው።]

ደህና አደሩ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም። ልታወሪኝ የፈለግሽው ነገር ያለ ይመስላል? አዎ። እንዲያው ነገሩ ግርም ቢለኝ ልጠይቅዎ አስቤ ነው ክቡር ሚኒስትር። ምንድነው? ሰሞኑን አባቶችን አስማምታችሁ አልነበርም እንዴ? ልክ ነው። ቤተ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፓርቲያቸው የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ቢገናኙም፣ ውይይቱ ከዚህ ቀደም ባልለመዱት መልኩ ሙግት የቀላቀለ ሆኖባቸዋል]

ክቡር ሚኒስትር ፖለቲካውን የምንመራበት መንገድ ትክክል አልመሰለኝም፣ መንገድ እየሳትን ነው። እንዴት፣ ለምን እንስታለን? ምክንያቱም ከሁሉም ጋር እየተጋጨን ነው። ሥልጣን ስንይዝ የነበረን የማኅበረሰብ ድጋፍ ተሸርሽሮ እያለቀ ነው። አይምሰልህ።...

[ክቡር ሚኒስትሩ ስለፖለቲካ ማርኬት ፕሌስ ጽንሰ ሐሳብ አጥንተው ከፍተኛ አመራሮችን ሲያሠለጥኑ ቢሰነብቱም ዛሬ ከባለቤታቸው የተነሳውን ጥያቄ ለመመለስ ተቸግረዋል]

እኔ ምልህ ክቡር ሚኒስትር? ክቡር ሚኒስትር ካልሽኝ ችግር አለ ማለት ነው። ችግርማ አለ። እሺ ... እኔ ምልህ ያልሽው ለምን ነበር? ልጠይቅህ ነዋ። ምን? ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስትሰብኩት የነበረው ነገር የውሸት...

አዳዲስ ጽሁፎች

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ያለፉትን ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የተመለከተ ማብራሪያ...

የተዘነጋው የከተሞች ሥራ የመፍጠር ተልዕኮ

በንጉሥ ወዳጅነው አሁን አሁን የአገራችን የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ አንገብጋቢና ሊታሰብበት የሚገባ አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡ ከዓመት ዓመት እየተጠራቀመ ከመጣው ተምሮ ቁጭ ካለ ኃይል አንፃር ብቻ...

ሆድና የሆድ ነገር

(ክፍል ስድስት) በጀማል ሙሐመድ ኃይሌ (ዶ/ር) አቶ ባል - "ለዛሬ ገንፎ"    ወ/ሮ ሚስት - "ለልክህ ድፎ" ዜናዎች ወይም በአጠቃላይ መረጃዎች በጋዜጣ ላይ ከመታተማቸው፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ከመሠራጨታቸው በፊት...

የረቂቅ ሙዚቃ ፈር ቀዳጇ እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ (1916-2015)

‹‹...የሙዚቃ ሥራዎቼን ለአድማጭ የማድረስ ፍላጎቴን እኔ ከመረጥኩት መንገድ በተለየ ጎዳና ተጉዤ እውን እንዳደርግ የፈቀደልኝ የፈጣሪ ጸጋ ነው። የተከተልኩት ጎዳና ‹መጀመሪያ የእግዚአብሔርን መንገድ ፈልግ፤ ከዚያም...

የልብ ቀዶ ሕክምና አላቂ ዕቃዎች አለመኖር ባለሙያዎችን ወደውጭ አገር እንዲኮበልሉ ይዳርጋቸው ይሆን?

የልብ ቀዶ ሕክምና ቅንጦት ሳይሆን መሠረታዊ፣ ከሕይወት ጋር የተያያዘና እጅጉን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንንም በጥሩና በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን የበኩሉን ዕገዛ ያደርጋል ተብሎ የታመነበት የኢትዮጵያ...

ወጣቶችን ከሱስ የመታደግ ክዋኔ

በኢትዮጵያ ጫት፣ ሲጋራ፣ አልኮልና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆችን የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ይታመናል፡፡ በተለይ ወጣቶች የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ ሆነዋል፡፡ ከሁሉም በላይ...

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን