Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትብሔራዊ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የለገጣፎ ለገዳዲ ክለብን በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ

ብሔራዊ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የለገጣፎ ለገዳዲ ክለብን በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ

ቀን:

  • ለመቻል የተሰጠው ፎርፌ ተሸሯል
  • የሊግ ካምፓኒ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል

የለገጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማኅበር ላይ ያቀረበው የክስ አቤቱታ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ ሲመረምር ከቆየ በኋላ ውሳኔ ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡

ዲስፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ ያስተላለፈው የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ሲሆን፣ የለገጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለብ በአቤቱታው ላይ ከሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በነበረው ጨዋታ ክለቡን በማስገደድ መብቱ ተጥሶ እንዲጫወት መደረጉን ያብራራል፡፡

በዚህም መሠረት የጨዋታው ውጤት እንዲታይለት ቅሬታ ያቀረበ ቢሆንም፣ ስለመገደዱ በማስረጃ ያላረጋገጠና ሙሉ ተጫዋቾችን ወደ ሜዳ ይዞ ገብቶ ጨዋታውን ባደረገበት ሁኔታ ከጨዋታ በኋላ የተገኘውን ውጤት (ሽንፈት) በመንተራስ የቀረበ ተገቢነት የሌለው ጥያቄ በመሆኑ፣ ኮሚቴው እንዳልተቀበለው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ባቀረበው ሪፖርት ተመልክቷል፡፡

ክለቡ ሁለተኛውንም ክስ ለዲስፕሊን ኮሚቴ ያቀረበ ሲሆን፣ ከመቻል እግር ኳስ ክለብ ጋር በነበረው ጨዋታ ተጫዋቾችን ይዞ ከቀረበ በኋላ በሁለተኛ ዙር የዝውውር መስኮት ለመጫወት ውል የፈጸሙ ተጫዋቾች አዲስ ለሚገቡበት ክለብ መጫወት የሚችሉት በሁለተኛው ዙር ወይም (ከ16ኛው ሳምንት) ጀምሮ ነው በማለት የሰጠውን መመርያ መሠረት ያደረገ ነበር፡፡

በዚህም መሠረት በዕለቱ የዳኞች ቡድን ክለቡ አዲስ ያስፈረማቸውን ተጫዋቾች ለጨዋታ ወደ ሜዳ ይዞ መግባት እንደማይችል የተገለጸለት በመሆኑ፣ ክልከላው እንደተፈጸመ የዲስፕሊን ኮሚቴው ማረጋገጡን ገልጿል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማኅበር የውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ ከመቻል ቡድን ጋር ባደረገው 15ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ቡድኑ ባለመቅረቡ ጨዋታው ሳይካሄድ ስለመቅረቱ ሪፖርት መቅረቡ ተጠቅሷል፡፡

በሪፖርቱም መሠረት የለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ ቡድን በፎርፌ ተሸናፊ ሆኖ ዜሮ ነጥብና ሦስት የግብ ዕዳ እንዲመዘገብበትና ተጋጣሚው መቻል በፎርፌ አሸናፊ ሆኖ 3 ነጥብና 3 ተደማሪ ግብ እንዲመዘገብለት በማለት ውሳኔ መስጠቱን አቅርቧል፡፡

ሆኖም የዳኞች ሪፖርት ላይ አምስት ቋሚ ተሠላፊ ብቻ ይዞ በመቅረቡ በሚል ከተገለጸው ጋር እንደሚጋጭ ኮሚቴው አንስቷል፡፡

በዚህም መሠረት በሪፖርቱ የቀረበውን በመመልከት፣ የኮሚቴ ውሳኔ ፌዴሬሽኑ ኮሚንኬው እንዳይፀድቅና በዲስፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ባገደበት ሁኔታ የተሰጠ መሆኑን አረጋግጦ፣ ተገቢነት የሌለው መሆኑን ተገንዝቤያለሁ ሲል አቅርቧል፡፡

በመሆኑም የፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ ላይ የሰጠው የፎርፌ ተሸናፊነትና መቻል እግር ኳስ ክለብ በፎርፌ አሸናፊ እንዲሆን በማለት የሰጠው ውሳኔ መሻሩን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በቀጣይ አወዳደሪው አካል በሚወስነው ቀን የለገጣፎ ለገዳዲ ቡድን በሁለተኛ ዙር የዝውውር መስኮት ያስፈረማቸውን ተጫዋቾች አካቶ የማሠለፍ መብቱ ተጠብቆ ጨዋታው እንዲደገም ወስኗል፡፡

ፌዴሬሽኑ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ፣ የለገጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለብ ያቀረበው አቤቱታ በፌዴሬሽኑ ዲስፕሊን ኮሚቴ ተመርምሮ ተገቢው ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የአክሲዮን ማኅበሩ ውድድርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ኮሚኒኬውን እንዳያፀድቅና ውሳኔ እንዳይሰጥ የሰጠውን ትዕዛዝ የፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበሩ ያላከበረ መሆኑን አንስቷል፡፡

በዚህም መሠረት የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ለዲስፕሊን ኮሚቴ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ውጤቱን ማፅደቅ ራሱን የቻለ በተናጠል የፍትሕ አካላትን ውሳኔ በመተው፣ ማፅደቅ መሆኑ እያታወቀ ከፍትሕ አካሉ ውጪ ውጤት ፀድቆ የማያውቅና ውጤት ማፅደቁ መዘግየት የነበረበት ቢሆንም፣ ውጤቱ የፀደቀ ስለሆነ የሊጉ ውሳኔ አብሮ እንዲታይና የዕርምት ዕርምጃ እንዲወሰድ በማለት አሳስቧል፡፡

በመሆኑም የፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበሩ በሁለት ተግባሮች ማለትም የተጫዋቾች ተገቢነት የፌዴሬሽኑ ሥልጣን (የሥራ ድርሻ) መሆኑ እየታወቀ፣ ተገቢ ያልሆነ ሰርኩላር ለክለቦች ማስተላለፉ እንዲሁም የፌዴሬሽኑን ዲስፕሊን ኮሚቴ ትዕዛዝ ጥሶ የካቲት 23 ቀን ውጤቱን ማፅደቁን በኮሚኒኬው የተረጋገጠ በመሆኑ የፌዴሬሽን የዲስፕሊን መመርያ አንቀጽ 89/1/ለ መሠረት አክሲዮን ማኅበሩና በውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ላይ ቅጣት ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት አክሲዮን ማኅበሩ የተጫዋቾች ተገቢነትና ዝውውር በተመለከተ ሥልጣኑ የፌዴሬሽኑ መሆኑ በማኅበር ውድድር ደንብ ላይ የተገለጸ ሆኖ ሳለ፣ ባልተሰጠው ሥልጣን ሰርኩላር ማስተላለፉ የደንብ ጥሷል ሲል ያትታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በለገጣፎ ለገዳዲና በመቻል መካከል ሊካሄድ የነበረው ጨዋታ ላይ ውጤት እንዳይፀድቅ በተከለከለበት ሁኔታ ክልከላውን ጥሶ ኮሚኒኬውን ማፅደቁ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ፣ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን መልካም የሥራ ግንኙነት የሚያበላሽና በመግባባት ወደፊት መሥራት የሚለውን የውል ስምምነት የሚጥስ በመሆኑ፣ የሊግ ካምፓኒው ከመሰል ድርጊቶቹ እንዲቆጠብ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በፌዴሬሽኑ በኩል እንዲሰጥ መወሰኑ አብራርቷል፡፡

በመጨረሻም ፌዴሬሽኑ በዲስፕሊን መመርያው አንቀጽ 81/ሸ ከዲስፕሊን ኮሚቴ የተሰጡ ውሳኔዎችን እንዲያስፈጽም ሲል አዟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...