Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየተደራጁ ኃይሎች ሥልጣንን በሕገወጥ መንገድ ለመያዝ  አዲስ አበባ ገብተው አድንደነበር  አስተዳደሩ አስታወቀ

የተደራጁ ኃይሎች ሥልጣንን በሕገወጥ መንገድ ለመያዝ  አዲስ አበባ ገብተው አድንደነበር  አስተዳደሩ አስታወቀ

ቀን:

  • አብን የአዲስ አበባ ከንቲባ ስልጣናቸውን ለቀው በሕግ ይጠየቁ ሲል ተቃውሞውን አሰማ

የአደባባይ መደበኛ ሁኔታዎችን በመጠቀም በሕገወጥ መንገድ ሥልጣን ለመጨበጥ የተደራጁ ኃይሎች ከክልል ወደ መዲናዋ ገብተው እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት በተከበረው የዓደዋ በዓል ላይ ለዚሁ ተግባር ቀደም ብለው ወደ ከተማዋ ከገቡት ውስጥ፣ 64 ከመቶው ከአማራ ክልል እንዲሁም 21 ከመቶው ከደቡብና 14 ከመቶዎቹ ከኦሮሚያ ክልል እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውና የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ትናንት ማክሰኞ ለከተማዋ ምክር ቤት ሪፖርታቸውን ሲያቀርቡ በተመሳሳይ ቁጥሮቹን የጠቀሱ ሲሆን፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ይኼ ከመደበኛው ፍልሰት የተለየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹በከተማዋ ውስጥ ባላቸው ኔትወርክ፣ በሚዲያ፣ በአክቲቪስት፣ በጥቅምና በፖለቲካ ትርፍ ተጠርተው የገቡ ኃይሎች ናቸው፡፡ የመንግሥት ሥልጣንን በሕጋዊ መንገድ ያላገኙ ኃይሎች እነዚህን አካላት ከክልል ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ አድርገዋል፡፡ ሆ ብለህ አራት ኪሎ ግባ ተብለው ነው የመጡት፡፡ የታቀደው ትልቅ ነበር፡፡ የተያዘው ስትራቴጂ ከባድ ነበር፡፡ የፀጥታ አካላት ባያቆሙት ኖሮ ዛሬ እዚህ ቁጭ ብለን አናወራም ነበር፤›› ሲሉ ከንቲባዋ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

በ127ኛው የዓድዋ የድል በዓል ቀን በምኒልክ አደባባይ አንድ ፖሊስ በገጀራ መገደሉንም ኮሚሽነር ጌቱ አስረድተው፣ 16 ፖሊሶች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል ብለዋል፡፡

በሪፖርቱ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባያቀርበውም በበዓሉ ቀን በጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በዓሉን ለማክበር በወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ዕርምጃ አንድ ወጣት መገደሉ ይታወሳል፤›› ከከተማ ውጪ ተያዙ የተባሉት ሰዎች ጉዳይ በምርመራ ላይ መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች ‹‹ይታወቃሉ›› ከማለት ውጪ ባለሥልጣናቱ የሰጡት ፍንጭ የለም፡፡

‹‹ጥቂት ፖለቲከኞች ሃይማኖትን እንደሽፋን እየተጠቀሙ ነው፡፡ በዓድዋ በዓል ቀን ቤተ ክርስቲያን ተጠግተው ድንጋይ ሲወረውሩ ነበር፡፡ በሲኖዶስ ውስጥ ችግር ሲፈጠርም አዲስ አበባን ለመበጥበጥ ሲዘጋጁ ነበር፡፡ አጀንዳ ተሰጥቷቸው ፋይናንስ ተደርገው ነው ቀደም ብለው አዲስ አበባ የሚገቡት፤›› ሲሉ ኮሚሽነሩ አክለዋል፡፡ ‹‹በሰላማዊ ምርጫ ያልተሳካላቸው ኃይሎች›› ናቸውም ብለዋል፡፡ ወ/ሮ ሊዲያ በበኩላቸው እነዚህን ኃይሎች በአራት ከፍለዋቸዋል፡፡ በፖለቲካ የተደራጁ ኃይሎች፣ በሃይማኖት፣ በብሔር የተደራጁና በመደበኛ ወንጀል የተደራጁ አራት ኃይሎች፣ ለአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ከፍተኛ ተግዳሮት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በተለይ በፖለቲካ የተደራጁት ከፍተኛ አደጋ ደቅነዋል ብለዋል፡፡

‹‹አገር መቆጣጠር እፈልጋለሁ የሚል ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ በከተማዋ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ለፖለቲካ ዒላማ ሲባል የፀረ ሰላም ኃይሎችን ወደ አዲስ አበባ የሚያስገባ አካል አለ፡፡ በተደራጀ ሁኔታ ከክልል ወደ አዲስ አበባ እያስገቡ ነው፡፡ በተለይ በበዓላት ሰሞን፤›› ብለዋል ወ/ሮ ሊዲያ፡፡

ኃላፊዎቹ ከሰሞኑ ከሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ባጃጆች ጋር የተፈጠረውንም ችግር ከዚሁ ጋር አያይዘውታል፡፡ እንደ ኃላፊዎቹ ገለጻ የባጃጅ ባለንብረቶችንም በእነዚሁ ኃይሎች የተደራጁና የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የጉራጌ በሚል አዲስ ባለንብረት እንደ አባል ለማስገባት እስከ 100 ሺሕ ብር የሚያስከፍሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች እነዚህ ኃይሎች የሚያቀርቡት ‹‹የሚመስሉም የማይመስሉም ጥያቄዎች አሉ፤›› ያሉ ሲሆን፣ ግን በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን መፈታት መቻል አለባቸው ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቴባ አዳነች አበቤ  ለከተማው ምክርቤት ያቀረቡት ሪፖርት ላይ “ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግስትን በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር ነው፡፡ ወደ ከተማዋ ከሦስት ክልሎች ማለትም ከአማራ ክልል 64 በመቶ፣ከደቡብ ክልል 21 በመቶና ከኦሮሚያ ክልል14 በመቶ ወደ አዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ ይገቡ ነበር ” መባሉን፣ አብን “ንግግሩ አደገኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ነው” ከለ በኋላ፣ከንቲባዋ የሪፖርታቸው አካል አድርገው ማቅረባቸው ከፋፋይና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ መሆኑንና አገረ መንግስቱን አደጋላይ የሚጥል በመሆኑ ከስልጣናቸው ተነስተው ለፍርድ እንዲቀርቡ በማሳሰብ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ ንግግራቸው በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት የሌለውና ዓለም አቀፍ የወንጀል ጥሪና ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶችን፣ ድንጋጌዎችንና በሥራ ላይ ያለውን ሕገመንግስት ጭምር የሚጥስ መሆኑን አብን ባወጣው አስቸኳይ መግለጫው አስታወቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...