Friday, April 19, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[የባለሥልጣኑ ኃላፊ የቴሌኮም ኩባንያዎች የስልክ ቀፎ የመሸጥ ፈቃድ እንዳላቸው ለማረጋገጥ ክቡር ሚኒስትሩ ጋር ደወሉ]

 • ክቡር ሚኒስትር ዕርምጃ ከመውሰዳችን በፊት አንድ ነገር ለማጣራት ብዬ ነው የደወልኩት።
 • እሺ ምንን በተመለከተ ነው?
 • የቴሌኮም ኩባንያዎችን በተመለከተ ነው።
 • የቴሌኮም ኩባንያዎች ምን?
 • የቴሌኮም ኩባንያዎች የሞባይል ቀፎ እንዲሸጡ በሕግ ተፈቅዶላቸዋል?
 • ቴሌኮም ኩባንያዎች የሞባይል ቀፎ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ሕግ ያለ አይመስለኝም። ግን ደግሞ በአንድ ነገር እርገጠኛ ነኝ።
 • በምን ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዳይሸጡ የሚከለክል ሕግ አለመኖሩን!
 • ስለዚህ መሸጥ ይችላሉ ማለትዎ ነው?
 • አላልኩም፡፡
 • ታዲያ ምን እያሉኝ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • የሚከለክል ሕግ እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ ነው ያልኩት።
 • በእኛ ባደረግነው ማጣራት ደግሞ የሞባይል ቀፎ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ሕግ የለም። ስለዚህ…
 • እ… ስለዚህ ምን?
 • የሚከለክል ሕግ ከሌለ እንደተፈቀደ ይቆጠራል ማለት እንችላለን ማለት ነው?
 • ከሕግ ትርጓሜ አኳያ ከተመለከትነው እንደዚያ ማለት ነው። ግን ለምንድነው ማጣራት የፈለጋችሁት?
 • በዚህ ሥራ ፈቃድ ያወጡ አስመጪዎች እያሉ አንድ የቴሌኮም ኩባንያ ሰሞኑን ውድ ስልኮችን አስመጥቶ ለገበያ እያስተዋወቀ ስለሆነ ነው።
 • ውድ ስልኮችን ስትል ምን ያህል የሚያወጡ ናቸው?
 • ትንሹ ዋጋ 95,000 ብር ነው።
 • ትልቁ ዋጋስ?
 • ትልቁ ዋጋ 140,000 ነው።
 • የትኛው የቴሌኮም ኩባንያ ነው?
 • የእኛው ነው።
 • ነው? ገባኝ፣ ገባኝ!
 • ምን ገባዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ለማን ሊያቀርብ እንደሆነ፡፡
 • ለማን ሊያቀርብ ነው?
 • ለከተማ አስተዳደሩ።
 • የትኛው ከተማ አስተዳደር?
 • ለአመራሮቹ የ140,000 ብር ስልክ እንዲገዛ የወሰነው አስተዳደር።
 • ለአመራሩ በጥቅማ ጥቅም መልክ እንዲሰጥ ነው የተወሰነው ክቡር ሚኒስትር?
 • አዎ። እንደዚያ ነው የተባለው።
 • የጥቅማ ጥቅም ውሳኔ መባሉ ግን ትክክል አይመስለኝም።
 • ታዲያ ውሳኔው ምን መባል ነበረበት?
 • ጋላክሲ ኤስ 23!
 • ኪኪኪኪ… የአስተዳደሩን ውሳኔ እንደዚያ ካልክ የቴሌኮም ኩባንያውን ውሳኔም ምን ልትለው ነው?
 • የድርሻዬን!

[የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ በስንዴ ምርት ግዥ ላይ ግር ያላቸውን ለማጥራት ለፌዴራሉ አቻቸው ጋ ስልክ ደወሉ]

 • በመኸር ወቅት የተሰበሰበው ስንዴ ለገበያ የሚቀርብበትን መንገድ የተመለከተ መመርያ ከገንዘብ ሚኒስቴር ደርሶን ነበር።
 • እሺ፡፡
 • እርስዎ ደግሞ ሰሞኑን ለሚዲያ የተናገሩትና ማሳሰቢያ አዘል መግለጫ አለ።
 • እሺ፡፡
 • እርስዎ የሰጡት ማሳሰቢያና ከገንዘብ ሚኒስቴር የደረሰን መመርያ የሚጣረሱ በመሆናቸው ነገሩን ለማጥራት ብዬ ነው።
 • ከገንዘብ ሚኒስቴር የደረሳችሁ መመርያ ምን ይላል?
 • የተመረተውን ስንዴ መግዛት የሚችሉት ከመንግሥት ጋር በትብብር የሚሠሩ ማኅበራትና ዩኒየኖች ብቻ ናቸው ይላል።
 • ትክክል ነው።
 • ማኅበራትና ዩኒየኖቹ ስንዴ መግዣ እንዳይቸገሩም ለክልሉ 1.3 ቢሊዮን ብር መላኩን ይገልጻል።
 • አዎ። ለሁሉም ሰንዴ አምራች ክልሎች በጀት መመደቡን አውቃለሁ፡፡
 • የደረሰን መመርያ የስንዴ መሰብሰቢያ ዋጋንም ያካተተ ነው።
 • መሰብሰቢያ ማለት?
 • አርሶ አደሩ የትርፍ ህዳግን ጨምሮ ስንዴ የሚሸጥበት ከፍተኛ ዋጋ ብር 3,200 መሆኑን አሳውቆናል።
 • ትክክል ነው።
 • እኛም በዚህ መሠረት ማንኛውም ዱቄት ፋብሪካና ነጋዴ ስንዴ እንዳይገዛ አግደናል። ምክንያቱም የዩኒየኖቹ የስንዴ ፍጆታ እንዳይጎድል በማሰብም።
 • ትክክል ነው፣ ምክንያቱም የዩኒየኖቹ የስንዴ ፍጆታ መሟላት አለበት።
 • ነገር ግን እርስዎ ሰሞኑን የሰጡት መግለጫ ችግር ፈጥሮብናል።
 • የትኛው መግለጫ?
 • አርሶ አደሩ ከ3,200 ብር በላይ የሚገዛው ካገኘ ስንዴውን መሸጥ ይችላል፣ የከለከለው የለም ብለው የተናገሩት።
 • እሱን የተናገርኩት የዩኒየኖቹ የስንዴ ፍጆታ ለማስተጓጎል አይደለም።
 • ታዲያ ለምንድነው?
 • ለሚዲያ ፍጆታ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...