- Advertisement -

የታክሲ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ የሚያደርጋቸው መመርያ ሊነሳ ነው

የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆኑ ሲሠራበት የነበረውን መመርያ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሊያነሳው መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት ወጥቶ የነበረውና ባለፈው ዓመት የተሻሻለው መመርያ፣ በታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ባለንብረቶች ከቀረጥና ታክስ ነፃ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች እንዲያስገቡ ይፈቅዳል፡፡

በዚህም አሮጌ ተሽከርካሪዎችን በመተካት ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ፣ ለቱሪዝም መስፋፋት ምቹ ሁኔታን እንዲፈጥሩና በአገር ውስጥ ተገጣጣሚ ተሽከርካሪዎች እንዲስፋፋ ዓላማ ይዞ የወጣው መመርያ፣ በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ፀድቆ የተዘጋጀውን የአንድ ገጽ መመርያ ይሽረዋል፡፡

የመመሪያውን መሰረዝ አስፈላጊነት በሚመለከት ሪፖርተር የገንዘብ ሚኒስቴር የሥራ ክፍል ኃላፊዎችን ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

- Advertisement -

የሚሰረዘው መመርያ የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበራትና የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች በሚያስመጧቸውና በሚገጣጥሟቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ነፃ የታክስና ቀረጥ ታሪፍ ዕድል በመስጠት ተጠቃሚ ያደርጋቸው ነበር፡፡

ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ያላቸው ፋብሪካዎች ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተገነጣጠሉ ተሽከርካሪዎችን ሲያስመጡ ከሚያገኟቸው ጥቅሞች መካከል፣ የታክስና የቀረጥ ክፍያዎችን በቅድሚያ ከፍሎ በ30 ቀን ውስጥ የሚገጣጥሙዋቸው ተሽከርካሪዎች ለተጠቃሚ እንደሚተላለፍ ማረጋገጫ ከቀረበ፣ የከፈሏቸው የቀረጥና የታክስ ወጪ እንደሚመለስ ያዛል፡፡ በተጨማሪም እነዚህን ተሽከርካሪዎች አስገብተው በጉምሩክ መጋዘን ውስጥ ካለክፍያ ማስቀመጥ አንደኛው የሚያገኙት ጥቅም ነው፡፡

የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበራት አሮጌ ተሽከርካሪዎቻቸውን ለመተካት ወይም አዲስ ለመግዛት ይህን ዕድል የሚጠቀሙበት ሲሆን፣ የክልልና የከተማ መስተዳድሮች ማኅበራቱ ለሚጠይቋቸው የታክስ ነፃ ዕድል ዕውቅና መስጠት ይኖርባቸው ነበር፡፡

የሚኒስቴሩ ኃላፊዎች መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሚኒስቴሩ የሰረዘውን መመርያ በሌላ ይተካ፣ አልያም የታክሲ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ድርጅቶች በዚህ ዕድል መጠቀምን አስቁመው እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም፡፡ 

- Advertisement -

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን

ከ ተመሳሳይ አምዶች

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል ባንኮች ቁጥር ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ ከዜሮ ተነስቶ ዛሬ ላይ 29 መድረሱ አንዱ ነው፡፡...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ ኃላፊነት ኃላፊነት ተሰጥቶት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በመጀመሪያው ምዕራፍ ውጥኑ ሰባት ሺሕ ኪሎ ሜትር...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላማዊ...

ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ይፋ ሊያደርግ ነው

የፋይናንስ ዘርፉን ለማረጋጋት የሚረዳ ሪፎርም ማጠናቀቁን የገለጸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ሪፎርም በሦስት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣...

ጉራጌን በክላስተር ለመጨፍለቅ የሚደረገውን ጥረት እንደሚቃወም ጎጎት ፓርቲ አስታወቀ

ለጉራጌ ሕዝብ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር እንደሚታገል የሚናገረው አዲሱ ጎጎት (ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ) የጉራጌ ሕዝብን ክላስተር በሚባል ክልል አወቃቀር የመጨፍለቅ ጥረት እንደሚቃወም ተናገረ፡፡ ፓርቲው...

‹‹ኢኮኖሚው ላይ የሚታዩ ውጫዊ ጫናዎችን ለመቀልበስ የፖሊሲ ሪፎርሞች ያስፈልጋሉ›› ዓለም ባንክ

በዓለም ደረጃ ከተፈጠረው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ጋር በተገናኘ፣ በኢትዮጵያ ውጫዊ የሆኑና ኢኮኖሚውን የሚገዳደሩ ጫናዎችን ለመፍታት፣ የማክሮ ፖሊሲ ሪፎርም እንደሚያስፈልግ የዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ምክትል...

አዳዲስ ጽሁፎች

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል ባንኮች ቁጥር ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ ከዜሮ ተነስቶ ዛሬ ላይ 29 መድረሱ አንዱ ነው፡፡...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ ኃላፊነት ኃላፊነት ተሰጥቶት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በመጀመሪያው ምዕራፍ ውጥኑ ሰባት ሺሕ ኪሎ ሜትር...

‹‹ልክ እንደ ሕክምና በፖለቲካውም ቅድመ ጥናት ተደርጎ ግጭቶችን መከላከል ያስፈልጋል›› ዶ/ር ተስፋዬ መኮንን፣ የሕክምና ባለሙያና ደራሲ

ዶ/ር ተስፋዬ መኮንን የተወለዱት በጅማ ከተማ ቢሆንም፣ ዕድገታቸውንና የልጅነት ጊዜያቸውን ያሳለፉት ሐረር ነው፡፡ ‹‹ወታደር አንድ ቦታ ስለማይቀመጥና የወታደር ልጅ በመሆኔ ዕትብቴ በተቀበረበት ጅማ ከተማ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላማዊ...

ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ይፋ ሊያደርግ ነው

የፋይናንስ ዘርፉን ለማረጋጋት የሚረዳ ሪፎርም ማጠናቀቁን የገለጸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ሪፎርም በሦስት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣...

ግልጽነትና ተጠያቂነት የጎደለው አሠራር ለአገር አይበጅም!

ሰሞኑን የአሜሪካና የኢትዮጵያ መንግሥታት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የጦር ወንጀሎች መግለጫ ላይ አልተግባቡም፡፡ አለመግባባታቸው የሚጠበቅ በመሆኑ ሊደንቅ አይገባም፡፡ ነገር ግን...

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን