የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ኮንትሮባንድ ከጊዜ ወደጊዜ አደጋው እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ ባለፉት ስድስት ወራት የታየው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ “በጣም አስደንጋጭ ነው” ብለዋል።
ኮሚሽነሩ ይህን የተናገሩት በውጨ ጉዳይ ሚንስትር አዘጋጅነት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ፣ የክልል ፕሬዝዳንቶችና ሚንስትሮች በተገኙበት በሸራተን አዲስ ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓም እየተካሄደ በሚገኘው በኢንቨስትመንት እና ኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ያተኮረ ጉባኤ ላይ ነው።