Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተቋም ደረጃ ተቋቋመ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለፈው ዓመት ያስጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፣ ከዚህ በኋላ በፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ደረጃ ተቋቁሞ አገራዊ የኢንዱስትሪ ንቅናቄ ሆኖ ይቀጥላል ተባለ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በንቅናቄ የጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴ  “የኢትዮጵያ ታምርት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት” ተብሎ ራሱን የቻለ አደረጃጀት፣ የሰው ኃይል ተቋማዊ የሆነ ክላስተር ያለው ሆኖ ተቋቋሟል።

የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ አምስት የሚደርሱ ክላስተሮች ያሉት ሲሆን፣ ከእነዚህም የፋይናንስና ጉምሩክ ክላስተር፣ የግልና ኢንቨስትመንት ክላስተር፣ የግብርናና መሠረተ ልማት፣ የክልልና የከተማ መስተዳደር ክላስተሮች ይጠቀሳሉ። ክላስተሮቹን የየዘርፎቹ ሚኒስትርና ሚኒስትር ደኤታዎች እንደሚሰበስቡት አቶ ታረቀኝ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ታምርት የሚለውን አጠቃላይ ጽሕፈት ቤት ደግሞ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር በበላይነት በየሦስትና ስድስት ወራት ያለውን አፈጻጸም እየገመገመው እንደሚሄድ ሚኒስትር ደኤታው አክለዋል።

ንቅናቄው የጀመረበትን አንደኛ ዓመት ምሥረታ ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ ታምርት የሚል ኤክስፖ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚሊንየም አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው አገራዊ ኤክስፖ ከዓውደ ርዕይ በተጨማሪ የአምራች ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ላይ የዘርፉ ዋነኛ ተዋንያንና ፖሊሲ አውጪዎች ውይይቶችን እንደሚያደርጉ የኢንዱስትሪ  ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀ የማስታዋወቂያ መድረክ ላይ ተናግረዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች